ፈልግ

2023.09.03 Viaggio Apostolico in Mongolia - Santa Messa

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ‘ጸሎት በጦርነት በሚታመሰው ዓለም የእምነት እስትንፋስ ነው’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ዛሬ መጸለይ፣ የመሸነፍ ፈተና” በተሰኘው የብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ አዲስ መጽሐፍ መቅድም ላይ ባሰፈሩት የመግቢያ ጽሑፍ ክርስቲያኖች በግጭት ለተከበበችው ዓለማችን ልባዊ ጸሎት በማድረግ እ.አ.አ ለ2025 ኢዮቤልዩ እንዲዘጋጁ ጋብዘዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማክሰኞ ጥር 14/2016 በታተመው መጽሐፍ መቅድም ላይ በዓለም ዙሪያ የሚደረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ አጥብቆ መጸለይ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ መቅድም ከጸሎት ዓመት ጋር በተያያዘ በቫቲካን ማተሚያ ቤት (LEV) የታተመውን የብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ "ዛሬ መጸለይ። የመሸነፍ ፈተና" የተሰኘውን መጽሐፍ ያስተዋውቃሉ።

"ጸሎት የእምነት እስትንፋስ ነው፣ በጣም ትክክለኛው አገላለጽ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጽሐፉ መቅድም ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል።

የጸሎትን ምስጢር ለመግለፅ ቃላት ማግኘት ቀላል አይደለም ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ በመቅድም ጽሑፋቸው ውስጥ ያሰፈሩ ሲሆን በመቀጠል ከቅዱሳን እና መንፈሳዊ ሊቃውንት ብዙ ትርጓሜዎች ቢሰጡም "ይህንን በሚኖሩት ሰዎች የዋዕነት ብቻ ሊገለጽ ይችላል" ብለዋል።

ወደ ኢዮቤልዩ ስንሄድ የሚተቅሙን ጽሑፎች

የብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ መጽሃፍ በጸሎቱ አመት በሙሉ እንዲታተሙ ከተቀመጡት ተከታታይ አጫጭር ጽሑፎች ውስጥ የመጀመሪያው ሲሆን ይህም እ.ኤ.አ. ከ2025 ኢዮቤልዩ በፊት በእሁድ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መጽሐፍ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህ ተከታታይ ትምህርት “ይህን የጸሎት ዓመት ለማስተዋወቅ” እና ክርስቲያኖች “ወደ ተለያዩ የጸሎት ዘርፎች እንዲገቡ” ለመርዳት እንደሚፈልጉ ገልፀውበታል።

“እያንዳንዱ ሰው በትህትና እና በደስታ ለጌታ የመስጠትን ውበት እንደገና እንዲናገኝ እነዚህን 'ማስታወሻዎች' በእጃችሁ አስገባቸዋለሁ” በማለት የተለያዩ ተከታታይ ጸሃፊዎችን ላበረከቱት አስተዋጽዖ አመስግኗል።

እንዲያውም እ.አ.አ “የ2025 መደበኛ ኢዮቤልዩ በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚንገኘው” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቅድመ ጽሑፋቸው ያስፈሩ ሲሆን በመቀጠል “በጸሎት ካልሆነ በስተቀር ለቤተክርስቲያን ሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ለዚህ ዝግጅት እንዴት መዘጋጀት እንችላለን?” ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።

የምንኖረው በጸሎት ጥሪዎች ውስጥ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዘመናችን ያለውን አስፈላጊነት ሲገልጹ “በሕይወታችን ውስጥ በየቀኑ ለሚነሱት ታላላቅ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚችል እውነተኛ መንፈሳዊነት በእርግጥም የተረጋጋ ባልሆነ የዓለም ሁኔታ የተነሣሣ ነው” ያሉ ሲሆን ከዚያም “በቅርብ ጊዜ በተከሰተው ወረርሽኝ ተባብሶ በነበረው ሥነ-ምህዳራዊ-ኢኮኖሚ-ማህበራዊ ቀውስ ላይ ብርሃን በማብራት ይህንን የዓለም ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል። ጦርነቶች በተለይም በዩክሬን ውስጥ ሞትን፣ ውድመትንና ድህነትን የሚዘሩ ናቸው፤” እና “የግድየለሽነት ተወርዋሪ ባህል ያመለክታሉ፣ “እነዚህ ክስተቶች ብዙ ሰዎች በደስታ እና በእርጋታ እንዳይኖሩ የሚከለክለው ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ” ብለዋል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፡ “ስለዚህ አብ እንዲሰማ ጸሎታችን አብዝተን ከፍ አድርገን ለማቅረብ  እንፈልጋለን። መልስ እንደሚያገኙ በመተማመን ወደ እርሱ የሚመለሱ ሰዎች ድምፅ እግዚአብሔር ይሰማል ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው በመቅድም ጽሑፋቸው ውስጥ አስፍረዋል።

የተለያዩ የሐዋርያዊ አገልግሎቶች ተነሳሽነቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጸሎት አመት በተለይ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚደረጉትን የሐዋርያዊ እንክብካቤዎች ጅምር መሸርሸር የለበትም ብለዋል።

ይልቁንም አመቱ “የተለያዩ የሐዋርያዊ አገልግሎቶች እቅዶች መጎልበት ያለባቸውን መሰረት ለማስታወስ እና ወጥነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ ይፈልጋል። ወቅቱ በግልም ሆነ እንደ ማህበረሰብ በተለያዩ ቅርጾች እና አባባሎች የጸሎትን ደስታ እንደገና የሚያገኙበት ጊዜ ነው" ብለዋል።

“ከመንፈስ ቅዱስ ለሚፈሰው ጸሎት” ቦታ እንድንሰጥ ሁሉም ሰው ትሕትናን እንዲቀበል ቅዱስ አባታችን ጋብዟቸዋል፣ “ትክክለኛውን ቃል በልባችን እና በከንፈሮቻችን እንዴት እንደሚያኖር የሚያውቅ እርሱ ነውና አባታችን የሆነውን እግዚአብሔር መማጸን ይኖርብናል” ብለዋል።

የቀሳውስት እና የደናግላን አስተዋጾ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተጨማሪም ለኤጲስ ቆጶሳት፣ ለካህናት፣ ዲያቆናት እና ካቴኪስቶች ይጸልያሉ፣ እርግጠኞች መሆናቸውን በማረጋገጥ “በዚህ ዓመት ኢዮቤልዩ እ.አ.አ 2025 ድምፁን ከፍ ሊያደርግ ባለው የተስፋ አዋጅ መሠረት ጸሎቱን ለማኖር ተስማሚ መንገዶችን ያገኛሉ። በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት ማቅረብ ይኖርብናል” ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ቀሳውስት እና ደናግላን በተለይም የአስተንትኖ ወይም የማሰላሰል ህይወት የሚኖሩትን የማህበረሰብ ክፍሎች አስተዋፅዖ “እጅግ ዋጋ ያለው” እንደሆነ ያጎላሉ።

ተስፋቸውን ሲገልጹ “በሁሉም የአለም መቅደሶች፣ የጸሎት ልዩ ቦታዎች፣ እያንዳንዱ መነፈሳዊ ተጓዢ የመረጋጋት ቦታ አግኝቶ ማጽናኛ በተሞላበት ልብ እንዲሄድ ተነሳሽነቶች ይጨምራሉ።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሁሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲስፋፋ እና ፍቅር ለሚለምን ሁሉ ወንጌል እንዲዳረስ እንደ ጌታ ኢየሱስ ፈቃድ የግላዊና የማኅበረሰብ ጸሎት ባለማቋረጥ ልናደርግ ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የመቅድም ጽሑፋቸውን አጠናቀዋል።

24 January 2024, 15:01