ፈልግ

2019.03.29 Celebrazione Penitenziale

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በክህነት አገልግሎት ማዕከል ውስጥ ትብብር እና አገልግሎት አለ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ሀገረ ስብከት ለክህነት ለሚዘጋጁ ዲያቆናት ባደረጉት ንግግር ታማኝ ትብብርን፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማገልገል እና በመንፈስ ቅዱስ መመራት በክህነት አገልግሎት ውስጥ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን አጉልተው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሲመተ ክህነት ለሚዘጋጁ ዲያቆናት በተዘጋጀው ንግግር ላይ በሲመተ ክህነት  ሥርዓት ላይ ጎላ አድርገው የተገለጹትን የክህነት አገልግሎት ሦስት ገጽታዎች ማለትም ከኤጲስ ቆጶስ ጋር በታማኝነት መተባበርን፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማገልገል እና በመንፈስ ቅዱስ የመመራት አስፈላጊነት ላይ አተኩረው ተናግረዋል።

በጳጳሱ ጤንነት ምክንያት ሊደረግ የታቀደው ስብሰባ ቢዘገይም፣ የቅዱስ አባታችን ንግግር ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዕለት በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ታትሞ ይፋ ሆኗል።

ታማኝ ተባባሪዎች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጀመሪያ ደረጃ፣ ቤተክርስቲያን በዋናነት መሪ እንድትሆኑ አትጠይቃቸውም፣ ከጳጳሳት ጋር ተባብራችሁ እንድትሠሩ እንጂ። ካህናት በተለይም በወንድማማችነት፣ በታማኝነት እና ለመማር ዝግጁ በመሆን፣ የቤተክርስቲያን ለሆነው “የኅብረት ምስጢር” ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል ሲሉ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ባጭሩ ካህናት የመዘምራን ቡድን አባላት እንዲሆኑ እንጂ “ብቸኛ ዘማሪ እንዲሆኑ አልተጠሩም” ብሏል ። በክህነት ሕይወት ውስጥ ያሉ ወንድሞች እና ካህናት፤ ለተወሰነ ቡድን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ወንድሞች እንዲሆኑ ነው የተጠሩት ሲሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገልጿል።  

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማገልገል

ሁለተኛው የክህነት አገልግሎት ገጽታ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እዳሉት ከሆነ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማገልገል ነው። ክህነት በዲያቆንነት ውስጥ የተመሰረተ ነው፣ ይህም ከክህነት ሹመት በኋላ የማይቋረጥ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል። ካህናት “ለማገልገል እንጂ ለመገልገል አልተመረጡም” ያለውን ኢየሱስን እንዲመስሉ ተጠርተዋል ብሏል።

ይህ አገልግሎት፣ ረቂቅ ሊሆን አይችልም፣ ነገር ግን ተጨባጭ መሆን አለበት፡- “ማገልገል ማለት መገኘት፣ እንደራስ አጀንዳ መኖርን መተው፣ ለእግዚአብሔር መገረም ዝግጁ መሆን ማለት ነው… ርኅራኄ የተሞላበት ሕይወት መኖር ማለት ነው" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

በመንፈስ ቅዱስ መመራት።

በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ ካህናት በእነርሱ ላይ ለሚወርድ ለመንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ “ቅድሚያ” መስጠት አለባቸው ሲሉ አጥብቀው አሳስበዋል። “ይህ ከሆነ፣ ሕይወታችሁ… ወደ ጌታ እና በጌታ ላይ ያተኮረ ይሆናል፣ እናም እናንተ በእውነት ‘የእግዚአብሔር ሰዎች’ ትሆናላችሁ ብለዋል።

ይህ የሚመጣው በኢየሱስ “በየቀኑ ቅባት” በኩል “በፊቱ ስንቆም፣ እርሱን ስናመልክ፣ ከቃሉ ጋር ስንቀራረብ” ነው። እናም ይህ፣ በተራው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ “ስለ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች፣ ስለ ሰው ልጆች፣ በየቀኑ ስለምናገኛቸው ሰዎች በፊቱ እንድንማለድ ያስችለናል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ለሲመተ ክህነት የሚዘጋጁትን ዲያቆናትን ለእግዚአብሔር ስለሰጡት "አዎንታዊ ምላሽ" በማመስገን እና በየቀኑ ለእርሳቸው እንዲጸልዩ ከጠየቁ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

26 February 2024, 11:24