ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን እ.አ.አ በሕምሌ 23/2023 ዓ.ም የአረጋዊያን እና የአያቶች አመታዊ በዓል ባከበሩበት ወቅት የምያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን እ.አ.አ በሕምሌ 23/2023 ዓ.ም የአረጋዊያን እና የአያቶች አመታዊ በዓል ባከበሩበት ወቅት የምያሳይ ምስል   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለ4ኛው የአያቶች ቀን ይሆን ዘንድ ያቀረቡት ሐሳብ 'ብቸኝነት' የሚለው ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ ለ2024 ዓ.ም የአለም የአያቶች እና አረጋውያን ቀን “በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር በማስታወስ ባስተላለፉት መልእክት እ.አ.አ እሑድ ሐምሌ 28/2024 በዓለም ዙሪያ ያሉ ካቶሊኮች አያቶቻቸው እና አረጋውያን ያስተላለፉትን ታላቅ ቅርስ እና ጥበብ ላይ እንዲያሰላስሉ ይጋበዛሉ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለአያቶች እና አረጋውያን 4ኛው የአለም ቀን ዝግጅት የምእመናንን፣ የቤተሰብን እና የሕይወት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት እ.አ.አ የ2024 የአረጋዊያን እና የአያቶች ቀን መሪ ሃሳብ ይፋ አውጥቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ጕልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ” የሚለውን መሪ ሐሳብ መርጠዋል (መዝሙር 71፡9)።

በቅድስት መንበር የምዕመናንን፣ የቤተሰብን እና የሕይወት ጉዳዮችን የሚመለከተው ጽሕፈት ቤት አማካይነት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጸው ይህ ማለት “በሚያሳዝን ሁኔታ የብቸኝነት ስሜት በብዙ አረጋውያን ሕይወት ውስጥ መራራ ጉዳይ በመሆኑ ብዙውን ጊዜ ተጠቅሞ የመጣል ባህል ሰለባዎች መሆኖን ትኩረት ለመሳብ ታስቦ የተደረገ ነው ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው የእግዚአብሔርን ወዳጅነት ታሪክ የሚያንፀባርቁ አረጋውያን ያቀረቡትን ልመና የሚገልጸውን የመዝሙር 71 ጥቅስ በድጋሚ ያቀርባሉ።

“የአያቶችን እና የአረጋውያንን ውለታ በመንከባከብ እና በቤተክርስቲያኗ ህይወት ውስጥ የሚያደርጉትን አስተዋጾ በመንከባከብ የአለም ቀን እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ማህበረሰብ በትውልዱ መካከል ትስስር ለመፍጠር እና ብቸኝነትን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ይፈልጋል። - ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት - "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" (ዘፍ 2: 18) በጋዜጣዊ መግለጫው መሠረት ይህ ትኩረት የተሰጠው ነጥብ ሆኖ አልፏል።

የክርስቲያን ማህበረሰብ ብቸኝነት እና ርህራሄ

የምእመናን ፣ቤተሰብ እና ሕይወት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኬቨን ፋረል ብዙ አረጋውያንን የሚያሠቃየውን ብቸኝነት በማጉላት በእዚህ ረገድ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።

“ከዚህ እውነታ ጋር በተያያዘ ቤተሰቦችና የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች የመገናኘት ባህልን በማስተዋወቅ፣ ለማጋራት፣ ለመደማመጥ፣ ለመደጋገፍና ለመወደድ ግንባር ቀደም እንዲሆኑ ተጠርተዋል፡ ስለዚህም የወንጌል ፍቅር ተጨባጭ ይሆናል” ሲሉ አስምረው ተናግረዋል።  

ብቸኝነት የማይቀር የሰው ሕይወት ሁኔታ፣ እንዲሁም መጽናኛ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር አብ እንድንቀርብ ግብዣ የሚያቀርብልን ሁኔታ ነው ያሉት የምእመናን ፣ቤተሰብ እና ሕይወት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኬቨን ፋረል ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ለአያቶች እና ለአረጋውያን የተዘጋጀው የዓለም ቀን ተጠቅሞ የመጣል ባህላችንን ወደ ጎን በመተው በጣም ደካማ ለሆኑ የማህበረሰባችን አባላት “ርኅራኄ እና ፍቅር የተሞላበት ትኩረት እንድንሰጥ” ጥሪ ያቀርብልናል ብለዋል።

16 February 2024, 16:03