ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ሁሉም ሰው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን መዋጋት አለበት ማለታቸው ተገለጸ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
"እኔ ራሴን በሙሉ ልቤ በአለም ዙሪያ ለምትገኙ በተለይም ይህን አለም አቀፋዊ መቅሰፍትን ለመዋጋት ከምትሰሩት ወጣቶች ጋር አቆራኝቻለሁ" በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት እና ለማጥፋት ይህንን አበረታች ተማጽኖ በሰጡበት መልዕክታቸው ሀሙስ ጥር 29/2016 ዓ.ም በተከበረው 10ኛው የአለም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የፀሎት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት “እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አልረፈደም” ሲሉ ደጋግመው ተናግረዋል።
የቤተክርስቲያኗ የዘንድሮው ቀን መሪ ሃሳብ "በክብር የሚደረግ ጉዞ፡ አዳምጥ፣ አልም፣ ተግብር” የሚለው መሪ ቃል እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ማሸነፍ የምንችለው በጋራ ብቻ ነው።
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ ክብረ በአል ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ቀኑም እ.አ.አ. በ2015 ዓ.ም እንደ ነበረና የቅድስት ጆሴፊን ባኪታ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት ወቅት እንደ ነበረም ይታወሳል።
እ.ኤ.አ. በ2000 ስዕመተ ቅድሳን የተሰጣቸው ቅድስት ባኪታ የሱዳን አገር ተወላጅ የነበሩ ሲሆን ከህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተረፉ ቅድስት ናቸው። ትውልደ ሱዳናዊቷ ለትውልደ ጣሊያናዊ ካኖሲያን መነኩሴ (1869-1947) በልጅነቷ ለባርነት የተሸጠች ሲሆን ጣሊያን እስክትደርስ ድረስ የሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ሰለባ ነበረች፣ ከዚያም በኋላ የካኖሲያን የእህቶች ማሕበር አባል ሆነች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰዎች ላይ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚከላከል የራሱን የአለም ቀን በነሐሴ 30 ላይ በተናጠል ያከብራል።
በክብር የተሞላ ጉዞ፣ አዳምጥ፣ አልም ተግብር
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ሁሉም ሰው የቅድስት ባኪታን ፈለግ እንዲከተል አሳስበዋል።
"የደረሰባትን በደል፣ ስቃይዋን እናስታውስ፣ ነገር ግን ጥንካሬዋን እና የነጻነት እና አዲስ ህይወት ጉዞዋን እናስታውስ" ሲሉ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "የቅድስት ባኪታ ሕይወት የማይታዩትን ለማየት እና ድምጽ የሌላቸውን ለመስማት ዓይኖቻችንን እና ጆሯችንን እንድንከፍት ያበረታታናል፣ ለእያንዳንዱ ሰው ክብር እውቅና ለመስጠት እና ህገወጥ ዝውውርን እና ሁሉንም ዓይነት ብዝበዛዎችን ለመዋጋት" ያነሳሳናል ብለዋል።
ሕገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ብዙውን ጊዜ የማይታይ ነው ሲሉ በቁጭት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ዘመናዊ የባርነት ዓይነቶችን ወደ ብርሃን ያመጡትን ሚዲያዎች እንዲሁም በዙሪያው ያለውን የግዴለሽነት ባህል የምያገልጡን ቅዱስነታቸው አመስግነዋል።
“እርስ በርሳችን እንረዳዳ” ሲሉ አሳስቧል፣ “የበለጠ ምላሽ እንድንሰጥ፣ ህይወታችንን እና ልባችንን ለወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዲከፍቱ፣ አሁንም ለባርነት እየተገዙና እየተሸጡ ይገኛሉ። እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አልረፈደም” ብለዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አያይዘውም የዕለቱን ተግዳሮት ለተወጡት በርካታ ወጣቶች እግዚአብሔርን አመስግነዋል፤ ጉጉታቸውና ቁርጠኝነታቸው "መንገዱን ያሳየን" ሲሉ አስበዋል፣ “የተጠራነው ሕገወጥ የሰዎች ማዘዋወርን ለመከላከል እንድንሰማ፣ እንድናልም እና እንድንተገብር ነው" ብለዋል።
የመከራውን ጩኸት ማዳመጥ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተጎዱትን ሰዎች እንዲያዳምጡ ተማጽነዋል። "በጦርነት እና በግጭት የተጎዱትን፣ በአየር ንብረት ለውጥ የተጎዱትን፣ ለመሰደድ የተገደዱትን እና በተለይም ሴቶች እና ህጻናት በፆታዊ ወይም በስራ ቦታ የሚበዘብዙትን ሁሉ ማሰብ ይኖርብናል ብለዋል።
"የእርዳታ ጩኸታቸውን ሰምተን የሚነግሩን ታሪኮች ተግዳሮት ይሁነን” ብለዋል።
መቅሰፍትን ለመዋጋት ተጨባጭ እርምጃ ያስፈልጋል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ህገወጥ ዝውውርን ለመዋጋት ሁሉም ሰው እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል ።
በየደረጃው “በጸና እንጸልይ እና ለዚህ ዓላማ፣ የሰውን ክብር ለመጠበቅ በንቃት እንስራ” ሲሉ አሳስበዋል።
ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚደረገውን ትግል “ማሸነፍ እንደሚቻል” ብናውቅም፣ “የችግሩን ምንጭ ማወቅና መንስኤዎቹን ማስወገድ ያስፈልጋል” ሲሉም ጠቁመዋል።
የድርጊት ጥሪ እና ውስብስብነትን ያስወግዱ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቅድስት ባኪታን አርአያነት በመከተል ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት ሁሉ አበረታተዋል።
“ሕገወጥ የሰዎች ማዘዋወርን በመታገል እና ሙሉ ክብራችንን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለንን አቅም ሁሉ በማሰባሰብ እርምጃ እንድንወስድ ጥሪ አቀርባለሁ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን የእዚህ ተግባር ተባባሪ ደግሞ ጥፋተኛ ይሆናል" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ ቀን አከባበር ላይ ለተሳተፉት ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን በመግለጽ እና ህገወጥ ዝውውርን እና ሁሉንም አይነት ብዝበዛን ለመዋጋት ቁርጠኛ የሆኑትን ሁሉ ባርከዋል።
“ሕገወጥ የሰዎች ማዘዋወርን በመዋጋት ኃይላችንን ሁሉ ለማሰባሰብ እና የጥቃት ሰለባ ለሆኑት ሰዎች ሙሉ ክብራችንን ለመመለስ እርምጃ እንድንወስድ ጥሪ አቀርባለሁ። ዐይናችንን እና ጆሯችንን ከጨፈንን፣ ምንም ነገር ካላደረግን በድርጊቱ ጥፋተኞች እንሆናለን” ካሉ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።