ፈልግ

በጋዛ ሰጥ የሚገኘው የቅድስት ቤተሰብ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጋዛ ሰጥ የሚገኘው የቅድስት ቤተሰብ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ፒዛባላ በጦርነት ለሚሰቃዩ ሰዎች ቅርበት ስላላቸው አመስግነዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በስልክ ባደረጉት ንግግር በጋዛ የሚገኘው የቅዱስ ቤተሰብ ካቶሊካዊ ምእመናን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ተጠልለው የሚገኙበት ሥፍራ ጥቃት እንዳይደርስበት ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከብፁዕ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ጋር በስልክ ተነጋግረው የሀማስ እና የእስራኤል ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለህዝቡ ላሳዩት ቅርበት የላቲን የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ አመስግነዋል።

በስልክ በተደርገው ንግግር  ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጋዛ ውስጥ ላሉ የቅዱስ ቤተሰብ ካቶሊካዊ ሰበካ ያላቸውን የማያቋርጥ እንክብካቤ አመስግነዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከደብሩ ቄስ አባ ገብርኤል ሮማኔሊ እና ከምክትላቸው አባ ዮሴፍ አሳድ ጋር በየቀኑ ማለት ይቻላል ሁኔታውን ሲጠይቁ ቆይተዋል።

የቅድስት ቤተሰብ ቁምስና በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የሚገኝ ብቸኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ነው።

በመላ ጋዛ እንደታየው ሰበካው የምግብ፣ የውሃ እና የመድኃኒት እጥረት ያጋጥመዋል።

ቢሆንም፣ ትምህርት ቤትን የሚያጠቃልለው የሰበካ ግቢ በጦርነቱ ውስጥ ሁሉንም ነገር ያጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማስጠለሉን ቀጥሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኋላም በሳምንታዊው የጠቅላላ አስተምህሮ ማብቂያ ላይ ምእመናን በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱትን ጦርነቶች እንዳይረሱ አሳስበዋል በተለይም በቅድስት ሀገር እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሚሠቃዩትን ብቻ ሳይሆን ዩክሬንን እና ሮሂንጋዎችን "ሰማዕታት" ብለዋል። በምያንማር ያሉ ሰዎች እና “በሁሉም ቦታ” እየተካሄዱ ያሉት “ብዙ፣ ብዙ ጦርነቶች” አውግዘዋል።

“ለሰላም እንጸልይ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማከል፣ “ጦርነት ምንጊዜም ሽንፈት ነው። ለሰላም እንጸልያለን። ሰላም እንፈልጋለን” ማለታቸውም ተገልጿል።

07 February 2024, 14:03