ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ ከሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ስደተኞችን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ ከሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ስደተኞችን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ‘እኔም የስደተኛ ቤተሰብ ልጅ ነኝ’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፓናማ ላጃስ ብላንካስ ለተሰበሰቡ የስደተኞች ቡድን መልእክት ማስተላለፋቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞቹን “የክርስቶስ ፊት” በማለት ቤተክርስቲያን በፍቅር “እፎይታ እና ተስፋ” ልትሰጣቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጋቢት 11/2016 ዓ.ም ባስተላለፉት መልእክት በላጃስ ብላንካስ፣ ፓናማ ለተሰበሰቡ የስደተኞች ቡድን ንግግር አድርገዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመንፈስ ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው መሄድ እንደሚፈልጉ ተናግረው ስለሁኔታቸውም ያላቸውን ግንዛቤ ገለጸዋል።

“እኔም የተሻለ የወደፊት ሁኔታ ፍለጋ የወጣሁ የስደተኞች ልጅ ነኝ” ብሏል።

በማገልገል ላይ ያሉትን ጳጳሳት እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አመስግነዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቿ ጋር የምትሄድ፣ የክርስቶስን ፊት የምታውቅ እና እንደ ቬሮኒካ በፍቅር የስደት መንገድ ላይ እፎይታ እና ተስፋ የምትሰጥ እናት ቤተክርስቲያን ፊት” እንደሚወክሉ ተናግሯል።

ቅዱስ አባታችን አክለውም “ስደተኞች ከአገራቸው ለመውጣት፣ የከባድ ጉዞ አደጋና መከራ ለመጋፈጥ፣ ሌላ መውጫ በማያገኙበት ወቅት የሚሠቃየውን የክርስቶስ አካል ይወክላሉ ያሉ ሲሆን ስደተኞቹ ሰብአዊ ክብራቸውን ፈጽሞ እንዳይረሳ እና “የሌሎችን ዐይን ማየት እንዳይፈሩ” “የማይጣሉ” ስለሆኑ ተማጽኗል።

እነሱም “የሰው ቤተሰብ አባላትና የአምላክ ልጆች ቤተሰብ” መሆናቸውን አረጋግጦላቸዋል።

21 March 2024, 15:57