ፈልግ

ሃይቲ በፖርት-አው-ፕሪንስ ውስጥ ሁከትን ለመቋቋም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች። ሃይቲ በፖርት-አው-ፕሪንስ ውስጥ ሁከትን ለመቋቋም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች። 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሄይቲ ሰላም እና ዓለም አቀፍ አንድነት ጸለዩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የዩክሬን እና የቅድስት ሀገር ህዝቦችን በማሰብ ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም የከፋ የጸጥታ ሥጋት ላለባት ለሄይቲ ህዝብ ጸሎታቸውን አድርሰዋል። አክለውም ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የረመዳን ጾም በመጀመራቸው ለእነርሱ ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሄይቲ የእርስ በርስ ጦርነት አፋፍ ላይ ነች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ መጋቢት 1/2016 ዓ.ም ያደረጉትን የመላከ እግዚአብሕእር ጸሎት ተከትሎ ባስተላለፉት መልእክት በካሪቢያን ሀገር የተከሰተውን ከባድ ቀውስ በቅርብ ቀናት ውስጥ በስፋት በተከሰተባት የሄይቲ ህዝብ በልዩ ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን አስታውሰ እዚያ ላለው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እና ለዓመታት ሲሰቃዩ ለነበሩት የሄይቲ ሰዎች ሁሉ ቅርብ እንደሆነ ተናግሯል። ሁከትና ብጥብጥ ይቆም ዘንድ ሁሉም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲጸልይ ጠይቀዋል። በሀገሪቱ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያላሰለሰ ድጋፍ በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲያበረክት አሳስበዋል።

ለሙስሊም ወንድም እና እህቶች ያላቸው ቅርበት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱም በዛሬው እለት ምሽት ማለትም በመጋቢት 1/2016 ዓ.ም ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የረመዳን መባቻን እንደሚያከብሩ አስታውሰው ወቅቱን በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋትና በጋራ ስግደት ሲያከብሩ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

ስለ ሰላም ጸሎቶች

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለመጡ የሮም የካቶሊክ ማህበረሰብ አባላት ሰላምታ አቅርበዋል፣ የተሠቃየችውን ዩክሬንን እና ቅድስት ሀገርንም በማስታወስ ለአገራቸው ሰላም ጸሎታቸውን አቅርበዋል።

በሲቪል ሕዝብ ላይ ይህን ያህል ስቃይ እየፈጠረ ያለው ጠብ በፍጥነት እንዲያቆም ቅዱስ አባታችን ጸሎተ ፍትሐት ሰጥተዋል።

11 March 2024, 11:48