ፈልግ

በታይዋን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በታይዋን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ   (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በታይዋን የመሬት መንቀጥቀጥ የተጎዱ ሰዎችን በጸሎት አስታውሰዋል!

ረቡዕ እለት መጋቢት 25/2016 ዓ.ም በታይዋን ሁሊያን ከተማ የተከሰተውን በርደ መሬት መለኪያ መሣሪያ 7.4 ንዝረት ያስቆጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለታይዋን የቻይና ክልል ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሐዘን መግለጫ ቴሌግራም ልከዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "በታይዋን በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰው ህይወት እና በመሰረተ ልማት ላይ የደረሰውን ጉዳት በሰሙበት ወቅት እጅግ አዝነው እንደ ነበረ በመልክታቸው ገልጸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐሙስ ዕለት መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ሐዘናቸውን ለታይዋን ሕዝብ ልከዋል፣ በቴሌግራም በተላከውን እና የቫቲካን ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ፊርማ ያረፈበት የሐዝን መግለጫ መልእክት ለታይዋን የቻይና ክልል ጳጳሳት ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንት ጳጳስ ጆን ባፕቲስት ሊ ኬ-ሚን በተላከ መልእክት በሁኔታው እጅግ ማዘናቸው ቅዱስነታቸው አክለው ገለጸዋል።

ረቡዕ መጋቢት 25/2016 ዓ.ም በርደ መሬት መለኪያ መሣሪያ 7.4 ያስመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጡ ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከ1,000 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ600 በላይ ሰዎችን ለመርዳት እየሰሩ ሲሆን አሁንም በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ጠፍተዋል ተብሏል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቴሌግራም “በዚህ አደጋ የተጎዱትን” “ከልብ የመነጨ አብሮነት እና መንፈሳዊ ቅርበት” አረጋግጦላቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለሞቱት፣ ለተጎዱት እና ለተፈናቀሉት ሁሉ እንዲሁም በማገገም ላይ  ላሉ ሰዎች እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች” ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል።

ቴሌግራሙ የቅዱስ አባታችንን ጥሪ “ለሁሉም የመጽናናት እና የጥንካሬ መለኮታዊ በረከቶች ላይ” በማሳየት ይጠናቀቃል።

05 April 2024, 18:22