ፈልግ

የሮም ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ሕንጻ የሮም ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ሕንጻ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለሮም ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ ለመሾም በቂ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሮም ሀገረ ስብከት የጳጳሳት ምክር ቤት አባላትን ሰኞ መጋቢት 30/2016 ዓ. ም. በቫቲካን ተቀብለው ተወያይተዋል። እንደ ጎርጎርሳውያኑ ከ 2017 ዓ. ም. ጀምሮ የሮም ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ በመሆን ቤት ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የቆዩት ብጹዕ ካርዲናል ዴ ዶናቲስ ከቅዳሜ መጋቢት 28/2016 ዓ. ም. ጀምሮ የምስጢረ ንስሐ ሐዋርያዊ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ለሀገረ ስብከቱ ተተኪ ረዳት ጳጳስ እስከሚመደብ ሕጋዊ ውክልናን ጨምሮ ሁሉም የሀረስብከቱ ተግባራት እና ስልጣኖች ምክትላቸው በሆኑት በብጹዕ አቡነ ባልዳዛር ሬይና እንደሚመራ ተገልጿል።

እንደ ከ2017 ጀምሮ የሮማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ደ ዶናቲስ የምስጢረ ንስሐ ሐዋርያዊ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ተጠሪ ሆነው ከተሾሙበት ከጥቂት ቀናት በኋላ የለፈው ቅዳሜ መጋቢት 28/2016 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰኞ መጋቢት መጋቢት 30/2016 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ ከሮም ሀገረ ስብከት የጳጳሳት ምክር ቤት አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

በሀገረ ስብከቱ ድረ-ገጽ ላይ የተሰራጨው ዜና እንዳስታወቀው፥ በካርዲናልነት ማዕረግ የሚቀርብ የረዳት ጳጳስ ሚና ጥንቃቄ የተሞላበትን ሃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ አዲስ ጳጳስ ለመመደብ ጊዜን እንደሚጠይቅ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለብጹዓን ጳጳሳቱ እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው አሳውቀው፥ ይህንን ሚና በሚረከብ ጳጳሳ ላይ ትክክለኛ የምርጫ ሂደት ሊደረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በረዳት ጳጳስ የሚከናወኑ ተግባራት እና ስልጣኖች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለብጹ ዓን ጳጳሳቱ እንደተናገሩት፣ በሽግግር ምዕራፉ ወቅት ከዚህ ቀደም ሲል የተጀመሩ ሐዋርያዊ አገልግሎት እና አስተዳደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲቀጥሉ በማለት ጳጳሳቱን አደራ ብለዋል። በጥር 6 ቀን 2023 የታተመውን የሮም ሀገረ ስብከት አደረጃጀት አስመልክቶ በአንቀጽ 14 እዝባር 3 ላይ በተደተነገገው መሠረት ለሀገረ ስብከቱ አዲስ ተተኪ ጳጳስ እስከሚመደብ ድረስ ሕጋዊ ውክልናን ጨምሮ ሁሉንም የሀገረ ስብከቱ ተግባራትን እና ስልጣንን ምክትላቸው የሆኑት ብጹዕ አቡነ ባልዳዛር ሬይና እንደሚመሩ ተገልጿል።

 

 

 

09 April 2024, 17:36