ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሃንጋሪው ፕሬዝዳንት ታማሽ ሱልዮክ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸውን የምያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሃንጋሪው ፕሬዝዳንት ታማሽ ሱልዮክ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸውን የምያሳይ ምስል  (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሃንጋሪውን ፕሬዝዳንት ተቀብለው አነጋገሩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሃንጋሪው ፕሬዝዳንት ታማሽ ሱልዮክ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ከሃናጋሪ ፕሬዚዳንት ጋር የተገናኙት ሐሙስ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም እንደሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የሃንጋሪው ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ታማሽ ሱልዮክ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ከተገናኙ በኋላ በመቀጠል የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ከሆኑት ከካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ጋር እና ቫቲካን ከሌሎች አገራትና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽህፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገርን አነጋግረዋል።

በቅድስት መንበር እና በሃንጋሪ መካከል ያለው መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት መልካም መሆኑን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገለጸ ሲሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለሃንጋሪ ማህበረሰብ እድገት ላሳየችው ቁርጠኝነት ምስጋና ቀርቧል።

መግለጫው በተጨማሪም አንዳንድ የጋራ ጥቅም ጉዳዮች ግምት ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል፣ በተለይ ለቤተሰቦች፣ ለወጣቶች እና ለዓለማችን በጣም ተጋላጭ ለሆኑ የክርስቲያን ማህበረሰቦች ትኩረት በመስጠት ደረጃ አብረው እንደሚሠሩ የተናገሩ ሲሆን ከዚያም በዩክሬን ስላለው ግጭት በተለይም ሰብአዊ መዘዞቹን እና ሰላምን ለማስፈን የተደረጉ ጥረቶች ተጠቅሰዋል።

 

25 April 2024, 18:05