ፈልግ

በጋዛ ለፍስልስጤማዊያን የሚደርገ የጤና ክብካቤ በቂ አለመሆኑ የሚያሳይ ምስል በጋዛ ለፍስልስጤማዊያን የሚደርገ የጤና ክብካቤ በቂ አለመሆኑ የሚያሳይ ምስል  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በቅርብ ጊዜ ያቀረቡትን ተማጽኖዋቸውን በድጋሚ ያቀረቡ ሲሆን የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነትን ለማስቆም “ያለሰለሰ ጥረት” እንዲደረግ በሲቪል ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ እጅግ እንደሚያሳዝናቸው ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በጋዛ ሰርጥ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረቡትን የቅርብ ጊዜ ጥሪያቸውን አድሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅድስት ሀገር ጦርነት ላይ በማሰላሰል ከመካከለኛው ምስራቅ እየመጣ ስላለው አሳዛኝ ዜና በቁጭት ተናግረዋል ።

“ደግሜ እላለሁ” ሲሉ ቅዱስ አባታችን ይግባኝ ጠይቀዋል፣ “በጋዛ ሰርጥ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያለኝ ጽኑ ጥያቄ እንደ ሁልጊዜም ጠንካራ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው "በጋዛ ሰርጥ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጽኑ ጥያቄዬን በድጋሚ አቀርባለሁ" ብለዋል።

መጋቢት 24/2016 ዓ.ም ማክሰኞ የእስራኤል የአየር ድብደባ በጋዛ ሰባት የረድኤት ሰራተኞችን ገድሏል፣ መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው የአለም ሴንትራል ኪችን ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመሆን ለተከበበው የፍልስጤማውያን ሕዝብ ምግብ ሲያደርሱ ነበር። ከተገደሉት ውስጥ ሶስት የእንግሊዝ ዜጎች፣ አንድ አውስትራሊያዊ፣ የፖላንድ ዜጋ፣ አንድ አሜሪካዊ-ካናዳዊ ባለሁለት ዜጋ እና አንድ ፍልስጤማዊ ይገኙበታል።

በጦርነት እና በስቃይ ለደከሙ ስቪሎች የቀረበ ጥሪ

"ያቀረብኩትን ጥሪ በድጋሚ አድሳለሁ" ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው "ለደከመው እና በስቃይ ላይ ለነበረው ሰላማዊ ህዝብ ሰብአዊ ርዳታ እንዲፈቀድላቸው እና ታጋቾቹም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተማጽኖዬን አቀርባለሁ፣

ለደከሙት እና ለሚሰቃዩ ሲቪሎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲፈቀድላቸው እና ታጋቾቹም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ከእዚህ በፊት ያቀርብኩትን አቤቱታዬን አደግሻለሁ" ብለዋል።

"በቀጣናው ያለውን ግጭት ለማባባስ የሚደርገውን ምንም ዓይነት ኃላፊነት የጎደላቸው ሙከራዎችን እናስወግድ" ሲሉም አክለው "ይህን እና ሌሎች በብዙ የአለም ክፍሎች ላይ ሞትና ስቃይ እያደረሱ ያሉ ጦርነቶችን ለማስቆም ያላሰለሰ ጥረት እናድርግ" ብለዋል።

03 April 2024, 15:42