ር.ሊ.ጳ ለካቶሊካዊ ምግባር ንቅናቄ አባላት እርስ በእርስ ተቃቀፉ፣ ጦርነትን አውግዙ ማለታቸው ተገልጿል!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቁጥር 50,000 የሚጠጉ የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ሥነ-ምግባር ንቅናቄ አባላት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሐሙስ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም በወላጆች፣ በአያቶች እና በልጆች መካከል በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ሰላምታ አቅርበው ንግግር አድርገዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በተከፈተ ክንድ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የስብሰባውን መሪ ቃል በተመለከተ ባደረጉት ንግግር “መተቃቀፍ የሰው ልጅ ገጠመኝ ከሚያሳዩት በጣም ድንገተኛ መግለጫዎች አንዱ ነው” እናም ሕይወት የሚጀምረው በመተቃቀፍ ነው ብለዋል።
በዚህ ምክንያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሶስት የማስተያያ ነጥቦችን ያስተዋውቃሉ፣ ሶስት ዓይነት እቅፍ አለ፣ ጠፍቶ የነበረውን ማቀፍ፣ የምያድን እቅፍ እና ህይወትን የሚቀይር እቅፍ እንደ ሆኑም ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
ጠፍቶ የነበረውን ማቀፍ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ ጠፍቶ የነበረውን ሰው ማቀፍ በተመለከተ በመጀመሪያ ሲናገሩ አንዳንድ ጊዜ “በአሁኑ ጊዜ በደስታ የምትገልጹት ጉጉት በአለማችን ተቀባይነት የለውም” ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ፣ “መዘጋትና ተቃውሞ ያጋጥመዋል፣ የወንድማማችነት መንፈስ መፍጠሪያ መሣሪያ ሳይሆን ውድቅ እና ግጭት፣ ብዙ ጊዜ ሁከት ይፈጥራል” ያሉት ቅዱስነታቸው ብዙ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደሚሉት “ጦርነቶች የሚመነጩት እቅፍ ከማጣት የተነሳ ነው” እናም ይህ ደግሞ ወደ ጭፍን ጥላቻ እና አለመግባባት ያመራል፣ ይህም ሌላውን እንደ ጠላት እንድትመለከቱ ያደርጋችኋል። ይህንን በዓለም ሁሉ እናያለን” ያሉ ሲሆን ነገር ግን "በእናንተ መገኘት እና የሥራችሁ የእቅፉ መንገድ የህይወት መንገድ እንደሆነ ለሁሉም ሰው መመስከር ትችላላችሁ” ብለዋል።
የማዳን እቅፍ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ የማዳን እቅፍ ሲናገሩ “በሰው ዘንድ መተቃቀፍ ማለት እንደ ፍቅር፣ ግምት፣ እምነት፣ ማበረታቻ እና እርቅ ያሉ አወንታዊ እና መሠረታዊ እሴቶችን መግለጽ ማለት ነው” ነገር ግን ይህ “በእምነት ስፋት ሲለማመድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕይወታችን ማእከል ላይ “በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው የቸሩ አባት እቅፍ በእያንዳዱ ምልክቱ የሚገለጥበት የቸር አባት እቅፍ ነው” በማለት የሚያድነው የእግዚአብሔር እቅፍ እንዳለ ጠቁመዋል።
ይህን ለእኛ የሚያሳይበት ምክንያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት ከሆነ "እኛም እንዲሁ ማድረግን እንድንማር" ነው ያሉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በጌታ እቅፍ ውስጥ ሌሎችን ማቀፍ እንማራለን" በማለት እኛን ራሳችንን ጌታ እንዲቀበለን እንፍቀድለት ብለዋል።
ሕይወትን የሚቀይር እቅፍ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሦስተኛው እቅፍ፣ ሕይወትን የሚለውጥ እቅፍ በተመለከተ ሲናገሩ ሐሳባቸውን ወደ ቅዱሳን አዙረዋል፣ ብዙዎቹ ሕይወታቸው “በመተቃቀፍ ወሳኝ ወቅት ተቀይሯል” ያሉ ሲሆን “ይህ ለእነሱ የሚሠራ ከሆነ ለእኛም ጭምር የሚሠራ ነው” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ሊቀ ጳጳሱ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ለተሰበሰቡት ሁሉ እነርሱ ራሳቸው የክርስቶስ መገኘትን እንደሚወክሉ ተናግረው “እያንዳንዱን የተቸገረ ወንድም እንዴት መሐሪና ሩኅሩኅ በሆኑ ክንዶች እንዴት ማቀፍ እና መደገፍ እንዳለባችሁ ባወቃችሁ መጠን” ኢየሱስ እናንተንም ልያቅፋችሁ ዝግጁ ነው ብለዋል። በዚህ መንገድ እናንተ ተጨባጭ የለውጥ ምልክቶችን ማድረግ ትችላላችሁ ብለዋል።
ሲኖዶስ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቀደም ሲል ያነሷቸውን ሦስት ነጥቦች ተናግረው የጨረሱ ቢሆንም፣ በመጨረሻው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሲኖዶሱን በተመለከተ ሐሳባቸውን ለማንሳት መርጠዋል። " ሁላችሁንም በአንድ ላይ ማየቴ ሲኖዶሱን ያስታውሰኛል" ብሏል። በሲኖዶሳዊ ጉባኤ ውስጥ ለመራመድ "በመንፈስ የተቀረጹ ሰዎች ያስፈልጋሉ" እና በዚህ ምክንያት "በምትኖሩባቸው አህጉረ ስብከት እና አድባራት ውስጥ የሲኖዶሳዊ ሂደት አራማጆች እና ሲኖዶሳዊ ሂደቱን ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተራማጆች ትሆኑ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ ፣ ለትግበራው ሙሉ በሙሉ ከእናተ ጋር ነን” ብለዋል።
በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ ከእነርሱ ጋር አብራቸው ትጓዝ ዝንድ ከመማጸናቸው በፊት እያንዳንዱን ሰው “እያበረከተ ለሚገኘው መልካም ተግባር አመሰግናለሁ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።