ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከወጣት ካህናት ጋር ተገናኝተዋል "መልካም ለማድረግ አትታክቱ" ማለታቸው ተገለጸ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሀገረ ስብከታቸው ቀሳውስት ጋር የሚያደርጉትን ተከታታይ ስብሰባ በመቀጠል በቅርቡ ከተሾሙ ካህናት ጋር ስለ ሐዋርያዊ እንክብካቤ ጉዳዮች ንግግር አድርገዋል። ባለፈው ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ለ40 ዓመታት እና ከዚያም በላይ በአገልግሎት ላይ ከቆዩ ካህናት ጋር የተደረገው የጳጳሱ ሁለተኛው ስብሰባ በመቀጠል በሮም ከተማ ውስጥ ከሚኖሩ ወጣት ካህናት ጋር የተደረገ ስብሰባ ነው።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዐሥር ዓመት ላላነሰ ጊዜ ያገለገሉትን እና አዲስ የተሾሙ ካህናትን ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ያነጋገሩ ሲሆን ስብሰባው የተስተናገደው በመለኮታዊ መምህር ደግ ደቀ መዛሙርት፣ ገዳማዊያት ማሕበር አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከመነኮሳቱ በፍቅር አቀባበል፣ ሰላምታ፣ ስጦታዎች እና በረከቶች መካከል በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ከዚያም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በጸሎት የጀመረው ስብሰባው ከእዚያም በመቀጠል ከካሕናቱ ጋር የተደረገ ስብሰባ በዝግ የተደረገ ውይይት ነበር።
በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ስብሰባዎች
የዛሬው ስብሰባ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ከሀገረ ስብከት ካህናት ጋር ያደረጉት ሁለተኛው ስብሰባ ነው።
እ.አ.አ ከመስከረም ከ2023 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር መጀመሪያ ድረስ፣ የሰበካ ካህናትን እና አስተዳዳሪዎችን ለማግኘት እና የሥራቸውን ተግዳሮቶች፣ ችግሮች፣ ውበት እና እርካታ ከነሱ ለመስማት በተለያዩ የሮም ግዛቶች ተዘዋውረው ጎብኝቷል።
31 May 2024, 13:09