ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዮርዳኖስን ንጉሥ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዮርዳኖስን ንጉሥ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ!  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዮርዳኖስን ንጉሥ በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከስመተ ርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ጊዜ ጀምሮ የሚያውቋቸውን የዮርዳኖሱን ንጉሥ አብዱላህ ዳግማዊን ሐሙስ ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም ዕለት በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ማለዳ ላይ ንጉሥ አብዱላህ ዳግማዊ እና አጃቢዎቻቸውን በቫቲካን ሐዋርያዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።

የቅድስት መንበር የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ማትዮ ብሩኒ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለ20 ደቂቃ በፈጀው የግል ስብሰባ ላይ "በጣም ልባዊ ውይይት" ተደርጎ ነበር ብለዋል።

ሐሙስ ጠዋት ካደረጉት ውይይት እና ከዮርዳኖስ ልኡካን ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ በመሪዎች መካከል የተለመደው የስጦታ ልውውጥ ተካሄዷል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጳጳሱን ቡራኬ፣ የቫቲካን ሞዛይክ ስቱዲዮን ሥራ፣ ለዓለም ቀን ያስተላለፉትን መልእክት ጨምሮ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጡ ልዩ ልዩ ሰነዶችን የያዘ ሞዛይክ ምስል ለንጉሥ አብዱላሂ አበርክተዋል፣ የ2024 የዓለም የሰላም መልእክትን ጨምሮ ማለት ነው።

ንጉስ አብዱላህ 2ኛ በአረብኛ ፊደላት የተሰራ የብረት ቅርፃ ቅርጽ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስጦታ መልክ ማበርከታቸው ተገልጿል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና የሐሺማይት መንግሥት ሉዓላዊ ግዛት ፕሬዚዳንት የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንችስኮስ የጵጵስና ዘመን ከጀመረበት ወቅት አንስቶ ይተዋወቃሉ።

የመጀመርያው ስብሰባቸው እ.አ.አ በ2014 የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ቅድስት ሀገር ያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ ምክንያት በማድረግ ወደ ዮርዳኖስ ዋና ከተማ አማን በተጓዙበት ወቅት ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት።

03 May 2024, 11:34