ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስኮላስ ኦኮሬንቴስ ማሕበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስኮላስ ኦኮሬንቴስ ማሕበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለስኮላስ ተማሪዎች፡ የሕይወትን ጣፋጭ ገጽታ መልሳችሁ ማግኝት አለባችሁ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስኮላስ ኦኮሬንቴስ በመባል በሚታወቀው ድርጅት ከየላቲን አሜሪካ የልማት ባንክ ጋር በመተባበር በቫቲካን በተዘጋጀው የመጀመርያው ‘ዓለም አቀፍ የትርጉም ስብሰባ’ ላይ መሣተፋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ለአራት መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ መስጠታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ስኮላስ ኦኮሬንቴስ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችሶስ የሚመራ ህዝባዊ አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ከመንግስት እና ከግል ትምህርት ቤቶች እና ከሁሉም ሀይማኖታዊ እና ዓለማዊ ትምህርት ቤቶች ጋር በመሥራት ከትምህርት ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር የትምህርት ስምምነትን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚሰራ ድርጅት ነው። እንደ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሰላምን የማስፈን ባህልን በትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ፍላጎት ካላቸውን አካላት ጋር በትብብር የሚሥራ ድርጅት ነው።

"የመጀመሪያው ትውስታዎ ምንድን ነው?" የተሰኘው ጥያቄ በቫቲካን ከግንቦት 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም በተዘጋጃው  የመጀመሪያው ‘ዓለም አቀፍ የትርጉም ስብሰባ’ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና ተሳታፊዎች መካከል የተደረገውን ውይይት የቀሰቀሰው ጥያቄ ነበር።

በቫቲካን በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ዝግጅት መዝጊያ ላይ ተሳታፊዎቹ ለቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሥራቸውን መደምደሚያ አቅርበው በስፓኒሽ ቋንቋ ደማቅ ውይይት አድርገዋል።

ለሶስት ቀናት ያህል ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ዳይሬክተሮች፣ የባህል፣ የፖለቲካ እና የቴክኖሎጂ አለም ግለሰቦች፣ በማኅበረሰባቸው ውስጥ ተደማጭነት ያላቸው ወጣቶች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለ‹ዩኒቨርሲቲ ትርጉም› ተግዳሮቶች ተጨባጭ መፍትሄዎችን ፈለጉ። ተማሪዎችን ቅዱስነታቸው ለሊቃውንት አደራ ሰጥተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመጀመሪያው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በሌሎች አጋጣሚዎች እንዳደረጉት፣ አያታቸው ወደ ቤት ወስዳ ቀኑን እስከ ምሳ ድረስ አብረው ሲያሳልፉ እና በሰሜን ኢጣሊያ የሚገኘውን የፒዬድሞንቴ ቋንቋ እንዴት መናገር እንደ ጀመሩ አስታውሰዋል። 'ፒዬድሞንቴዝ' የመጀመሪያ ቋንቋዬ ነው፣  በመቀጠልም "ከዚያም ስፓኒሽ ቋንቋ ተማርኩ" ሲሉ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ለተስፋ ቦታ ይስጡ

ብዙ መከራ የደረሰበት ሰው እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ስንመለከት፣ እንዲህ ዓይነት መከራ ቢደርስባቸውም ልባቸውን ክፍት እንዲያደርጉ ቅዱስ አባታችን አሳስበዋል።

"በህይወት ውስጥ ሊከሰት ከሚችለው በጣም የከፋው ነገር ክፉ ነገር ሲደርስባችሁ ራሳችሁን ዝግ ማድረጉ ከሕመም በላይ የሆነ ሕመም ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ልክ እንደ ጥርስ ሕመም ነው፣ ሕመም ወዳጅ እንዳይኖራችሁ ያደርጋል” ብለዋል። በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሕመም መንከባከብን ይጠይቃል፣ ሕመሙ ይህንን ይጠይቃል” በማለት “ለመንከባከብ ቦታ እንድንሰጥ አበረታተውናል። ለተስፋ ቦታ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጊዜ በኋላ የሥነ ጥበብ ሥራ በትርጉም ግንባታ ውስጥ ስላለው ሚና ሲወያዩ፣ “ሥነ ጥበብ አድማስን ይከፍታል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን የሌሎችን የትምህርት ዘርፎች አስተዋፅዖ አበርክተዋል።

ጥበብ ልብህን ያሰፋል

"የሒሳብ ትምህርት ጽኑ ፅንሰ-ሀሳቦችን እንድታዳብር እና እድገት እንድታመጣ ይረዳሃል። ፍልስፍና የተለያዩ የአስተሳሰብ መንገዶችን ይከፍታል" ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ጥበብ ወደ ፊት ይገፋሃል፣ ነፃ ያወጣሃል እና ልብህን ያሰፋል ሲሉ ተናግሯል።

ቅዱስ አባታችን ልጅ በነበሩበት ወቅት በቤት ውስጥ አንዳንድ ምሽቶች አባታቸው ከኤድመንዶ ደ አሚቺስ ኮራዞን (ልብ) ከተሰኘው መጽሐፍ እንዴት ያነቡላቸው እንደነበረ አስታውሰዋል።

"ይህ ከሥነ ጽሑፍ ጋር አስተዋውቆኛል" ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ጥበብ የሚከፍትህ ብቻ ሳይሆን "ያዛምዳል እና ልብህን ያቀልልሃል" ሲሉ ጠቁሟል።

በመጨረሻው የስብሰባው ተሳታፊዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን 'የዩኒቨርሲቲ ትርጉም' ምን እንደ ሆነ ጠይቀዋል።

ለዚህም ቅዱስነታቸው ሲምለሱ “ትምህርትን” ከ“መመሪያ” ጋር ማደናገር ያለውን አደጋ የገለጹ ሲሆን 'የዩኒቨርሲቲ ትርጉም' "በሶስቱ ቋንቋዎች" ማለትም "እጅ፣ ልብ እና አእምሮ" በተቀናጀ መልኩ ወደ ሥራ ይመራል ብለዋል።

ደስታን ማቀፍ

ከዚህም በላይ ቅዱስ አባታችን ‘የመጫወት ችሎታ’ እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበው “አንድ ሰው የመጫወት ችሎታውን ሲያጣ እና በጣም ከባድ በሚሆንበት ጊዜ የሕይወትን ትርጉም ያጣል” ብለዋል ።

በዚህ መንገድ እርሳቸው ልጅ በነበሩበት ወቅት የቆዳ ኳሶች በጣም ውድ ስለነበሩ በልጅነታቸው በጨርቃ ጨርቅ በተሰራ ኳስ ይጫወቱ እንደነበር ገልጿል። "ልጆች፣ ሲጫወቱ፣ ነገሮችን ሲፈጥሩ፣ ሁለት ወይም ሶስት ትናንሽ እንጨቶች ጨዋታውን ለመስራት በቂ ናቸው ምክንያቱም ትክክለኛው የጨዋታው ገጽታ ፈጠራ ነው" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስብሰባው ላይ የተገኙትን በማመስገን ታላቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው በመግለጽና ቡራኬያቸውን በማካፈል የዕለቱን ስብሰባ አጠናቀዋል።

24 May 2024, 14:27