ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 'በጦርነት የታወጀው ዓለም ውስጥ የፍቅር ሽታ ያስፈልጋል' ማለታቸው ተገለጸ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መዕመናን ዘንድ በግንቦት 25/2016 ዓ.ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ሥጋው እና ክቡር ደሙ የሚታወስበት በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ስግደት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። በወቅቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህ ክብረ በዓል በቅዱስ ዮሐንስ ላተራን ባዚሊካ ውስጥ በእርሳቸው መሪነት በተካሄደ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስበከት የቅዱስ ቁርባንን አስፈላጊነት በልባችን እና በጦርነት በተመሰቃቀለው ዓለማችን ሰላም ለማምጣት ያለውን አስፈላጊነት አንፀባርቀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"እግዚአብሔር አይተወንም፤ ነገር ግን ሁል ጊዜ ይፈልገናል፣ ይጠብቀናል፣ እናም እራሱን እንደ አቅመ ደካማ አድርጎ በእጃችን እስከማስገባት ድረስ ይጠብቀናል" ማለታቸው ተገልጿል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን እርግጠኝነት በቅዱስ ዮሐንስ ላተራን ባዚሊካ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም በዓል ስታከብር መስዋዕተ ቅዳሴውን ቅዱስነታቸው መምራታቸው የተገለጸ ሲሆን ከመስዋዕተ ቅዳሴው በመቀጠል በሮም ከተማ ውስጥ እስከሚገኘው የቅድስት ማርያም ሜጀር ባዚሊካ በተደረገ የቅዱስ ቁርባን ዑደት በዓሉ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የቅዱስ ቁርባን አመለካከት አድናቆትን ያስተምራል።

ቅዱስ አባታችን በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ ባደረጉት ስብከት፣ በቅዱስ ቁርባን ኅብስት ላይ አተኩረው ስለ “ምስጋና፣ መታሰቢያ እና መገኘት” መሪ ሃሳቦች ተናግረው ነበር።

እንጀራው ራሱ ወደ እኛ የቀረበበት የዕለት ተዕለት ሕይወት ምግብ እንደሆነ ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አክለውም ቅዱስ ቁርባን ተሰጥኦዎቻችንን እና ክህሎቶቻችንን በአግባቡ በመጠቀም በህይወታችን ላደረገልን ብዙ ስጦታዎች አመስጋኝ እንድንሆን ያስተምረናል ያሉ ሲሆን “ማመስገን ይህ የእኛ ተልእኮ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል፣ "የምስጋና መንገዶችን ልንጨምር ብንችልም እነዚህ ጠቃሚ 'የቅዱስ ቁርባን' አመለካከቶች እኛ የምናደርገውን እና የምናቀርበውን ነገር ዋጋ እንድናደንቅ የሚያስተምሩን ናቸው" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በአገልግሎት ውስጥ እውነተኛ ነፃነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የክርስቶስን ፍቅር፣ ሞት እና ትንሳኤ ወደ ማስታወስ አስፈላጊነት ዞረዋል።

ሥጋውን እና ደሙን ሲሰጠን፣ ኢየሱስ ለተቸገሩ ሰዎች እና በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ራሳችንን እንድንሰጥ አስተምሮናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እውነተኛ ነፃነት ማለት ስለ ራሳችን ብቻ ማሰብ፣ የፈለግነውን ለሌሎች ሳናደርግ እና ሳናስብ በሕይወታችን መደሰት ማለት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። ይህ ነፃነት ሳይሆን ድብቅ ባርነት ነው። እውነተኛ ነፃነት የሚገኘው “በፍቅር ብቻ ተነሳስተን” ሌሎችን ለማገልገል ጎንበስ ስንል ነው ብሏል።

ጎዳናዎች በፍቅር እንጀራ ተሞልተዋል።

በቅዱስ ቁርባን ውስጥ የክርስቶስን እውነተኛ መገኘት በማሰላሰል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማይተወን ይልቁንም በእንጀራ መልክ እንድንቀበለው እንደሚጠብቀን ጠቁመዋል።

“የእሱ እውነተኛ መገኘት ፍቅር በሚጠራን ቦታ ሁሉ ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር እንድንቀራረብ ይጋብዘናል” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ።

ዓለማችን የቅዱስ ቁርባንን እንጀራ አጥብቃ ትፈልጋለች፤ ይህም በፍርስራሾች የተሞሉ መንገዶች እና የጦርነቱ ውድመት ወደ ሰላማዊ ቦታዎች በአዲስ የተጋገረ እንጀራ ጠረን ተሞልተው እንዲመለሱ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው "ጥላቻ የሚያጠፋውን ተስፋ ለማድረግ እና እንደገና ለመገንባት ሳንታክት ለመቀጠል መልካም የሆነውን የፍቅር እንጀራን መልካም መዓዛ ወደ አለማችን ልንመልሰው ይገባል" ብሏል።

ሌሎች ክርስቶስን እንዲከተሉ መጋበዝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጠቃለያው ከቅዱስ ዮሐንስ ላተራን እስከ ቅድስት ማርያም ሜጀር የተደረገው የቅዱስ ቁርባን የጉዞ ዑደት ደማቅ የእምነት መግለጫ አይደለም ብለዋል።

“ይህን የምናደርገው ለመግለፅ ወይም እምነታችንን ለማሳየት አይደለም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው በቅዱስ ቁርባን እንጀራ፣ ኢየሱስ በሰጠን አዲስ ሕይወት ውስጥ እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ነው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

03 June 2024, 13:59