ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የኢዮቤልዩ ዓመት የውጭ ዕዳን የመሰረዝ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው አሉ! ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የኢዮቤልዩ ዓመት የውጭ ዕዳን የመሰረዝ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው አሉ! 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የኢዮቤልዩ ዓመት የውጭ ዕዳን የመሰረዝ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በደቡባዊ የዓለማችን ክፍል በሚገኙ አገራት ላይ ባለው የዕዳ ጉዳይ ላይ በቫቲካን በተካሄደው ጉባኤ ተሳታፊዎችን ባነጋገሩበት ወቅት መጪው የኢዮቤልዩ ዓመት ድሃ አገሮች የተበደሩት ዕዳ የመሰረዝ ወይም የመቀነስ ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እሮብ ጠዋት ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ጳጳሳዊ የሳይንስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተዘጋጀው “የዕዳ ቀውስ በአለምአቀፉ ደቡብ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1፡45 ላይ ስለተካሄደው የስብሰባው ጅምር ቀልድ ሲናገሩ ተሳታፊዎችን “ከአልጋችው ውስጥ በጥዋቱ ስላስወጣዋችሁ” ይቅርታ ጠይቃለሁኝ በማለት ታዳሚዎችን አስደምመዋል።

ሚሊዮኖች የወደፊት ጊዜያቸውን ማለም አቆሙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የችግሩን ስፋት በማሳየት ስለ ዕዳ ቀውስ መወያየት ጀመሩ።

“በመጥፎ አመራር የተመራ ግሎባላይዜሽን (ሉላዊነት)፣ ወረርሽኞች እና ጦርነቶች ካለፉ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ በደቡብ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙትን አገሮችን የሚጎዳ፣ መከራና ጭንቀት የሚፈጥር የእዳ ቀውስ ገጥሞናል” ብሏል። ይህ ሁኔታ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጥሩ የወደፊት ዕድል” ያሳጣቸዋል ብለዋል ።

“ደፋር እና ፈጠራ ችሎታ የተሞሉ” መፍትሄዎች

በችግሩ ላይ ምን ሊደረግ ይችላል?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት የቀውሱ መጠን ደፋር እርምጃዎችን ይጠይቃል - “ደፋር እና በፈጠራ ችሎታ የተሞላ አዲስ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ያስፈልጋል "እያንዳንዱ ሰው ለራሱ" ከሚለው አስተሳሰብ ለመራቅ - የሚሸነፍበት "ሁልጊዜ በጣም ደካማው ነው" - የሚፈለገው ያሉ ሲሆን ነገር ግን ጳጳሱ በአገሮች መካከል ዕዳን ለመቆጣጠር "ብዝሃ-ተኮር ዘዴ" ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህ ዘዴ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ "የችግሩን ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታ እና ኢኮኖሚያዊ፣ የገንዘብ እና ማህበራዊ አንድምታ" ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት ያሉ ሲሆን አላማው “በሚሰጡ እና በሚቀበሉት መካከል የጋራ ሃላፊነት” ላይ የተመሰረተ የእዳ መሰረዝ ስርዓት ነው ብሏል።

ዕዳ መሰረዝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በንግግራቸው ማብቂያ ላይ ስለ መጪው የ2025 ዓ.ም ኢዮቤልዩ ዓመት ተወያይተዋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በየሩብ ምዕተ-ዓመት አንድ ቅዱስ ዓመት ታከብራለች፣ ይህ ልማድ ከጥንታዊው የአይሁድ የኢዮቤልዩ ወግ፣ ባሪያዎች ነፃ የሚወጡበት እና ዕዳ የሚሰረይበት ነው።

እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም ባለፈው ኢዮቤልዩ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የውጭ ዕዳ እንዲቀንስ አልፎ ተርፎም ይቅር እንዲባል አበረታተው እንደነበር በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስም ይህንን ትንቢታዊ ጥሪ ማስተጋባት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

“እኛ የገንዘባችን ጠባቂዎች እና አስተዳዳሪዎች ብቻ ነን” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ነገር ግን እኛ የገንዘባችን “ጌቶች አይደለንም” ብሏል።

ማጠቃለያ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዕዳ ስረዛ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች “ለጋራ ቤታችን መሻሻል እንዲመኙ እና እንዲተባበሩ” በመጋበዝ ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል። "የምትሰሩት ሥራ ጠቃሚ ነው፣ ለእናንተ እጸልይልሃለሁ፣ እናንተም ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ተሰናብተዋል።  

05 June 2024, 14:49