ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ‘በቼንቲስሙስ አኑስ’ (መቶ አመት) በተሰነኘው የቫቲካን  ፋውንዴሽን በተዘጋጀው ስብሰባ ላ ሲሳተፉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ‘በቼንቲስሙስ አኑስ’ (መቶ አመት) በተሰነኘው የቫቲካን ፋውንዴሽን በተዘጋጀው ስብሰባ ላ ሲሳተፉ   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ AI፡ ለሰው ልጅ ለሚሰጠው ጥቅም አመስግነው፣ ነገር ግን የሚያስከትላቸውን አደጋዎች ቀንሱ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ ‘በቼንቲስሙስ አኑስ’ (መቶ አመት) በተሰነኘው የቫቲካን  ፋውንዴሽን ባዘጋጀው 'የጄኔሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ቴክኖክራሲያዊ ፓራዳይም' (Generative AI ማለት ለሰው ውይይት በተፈጥሮ ምላሽ መስጠት እና ለደንበኞች አገልግሎት እና የደንበኛ የስራ ፍሰቶችን ለግል ማበጀት እንደ መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ፣ ለደንበኞች የመጀመሪያ ግንኙነት መፍታት የበለጠ በትክክል ምላሽ የሚሰጡ በ AI የሚንቀሳቀሱ ቻትቦቶችን፣ የድምጽ ቦቶችን እና ምናባዊ ረዳቶችን መጠቀም ይችላሉ፥ ቴክኖክራሲያዊ ፓራዳይም የሚከተሉትን ሊያመለክት ይችላል፡ ከሶስቱ የኮምፒውተር ሳይንስ ምሳሌዎች አንዱ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ ‘ላውዳቶ ሲ' በተባለው ጳጳሳዊ መልእክታቸው ላይ ነቀፌታ ያቀረቡበት ቴክኖሎጂ ሲሆን ማህበረሰቡ ሁሉንም ችግሮች ለመፍታት በቴክኖሎጂው ላይ መደገፍ አለበት የሚል አስተሳሰብ ያለው ነው) በእነዚህ መርህ ሐሳቦች ላይ ባጠነጠነ መልኩ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ሸንጎ ላይ የተሳተፉትን ተሳታፊዎችን በማመስገን ‘ሰው ሰራሽ አብርኾት’ የሰውን ልጅ ለመጥቀም ብቻ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት በድጋሚ ተንግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያን ባሪ ከተምስ በተካሄደው የG7 ስብሰባ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ንግግር ካደረጉ ከሳምንት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ኃያል የቴክኖሎጂ ግስጋሴው በሥነ ምግባር፣ የሰውን ልጅ ለማገልገል፣ እና በተፈጥሮ ያለውን አደጋ መቀነስ እንዳለበት ቅዱስ አባታችን እያረጋገጡ ነው።

ላቲን ቋንቋ ‘በቼንቲስሙስ አኑስ’ (መቶ አመት) በተሰነኘው የቫቲካን  ፋውንዴሽን ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ‘የጄኔሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ቴክኖክራሲያዊ ፓራዳይም’ ላይ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ተሳትፈው እንደነበረም ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ውስጥ AI እንዴት የሰውን ክብር ለማጎልበት እና የተቸገሩትን በማገልገል ላይ መሆኑን ለመፈተሽ ቁርጠኝነትን በማሳየታቸው የስብሰባውን አዘጋጆች አመስግነዋል።

ጥረታችሁን "አደንቃለሁ" ሲሉ ገልጿል "ቼንቴሲሙስ አኑስ ለዚህ ርዕሰ ጉዳይ ሰፊ ቦታ ሰጥቷል፣ ከተለያዩ ሀገራት እና የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ ምሁራንን እና ባለሙያዎችን በማሳተፍ ከ AI ልማት እና አጠቃቀም ጋር የተያያዙ እድሎችን እና አደጋዎችን በመተንተን ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጓል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም እንዲሁ መሣሪያው በራስ ገዝነት ስለሚሠራ ፣ AI በሰው እጅ ቁጥጥር ውስጥ ያለ “መሣሪያ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ከዚህም በላይ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ‘ተጠቅሞ የመጣል ባህል’ እንዳይሠራ፣ እኩልነትን ከመደገፍ እና ከአመለካከታቸው ውጪ ውሳኔዎችን እንዳይወስኑ ቅዱስ አባታችን አስጠንቅቀዋል።

የ AI ዓላማ የሰውን ክብር ማሳደግ አለበት።

የ AIን (የሰው ሰራሽ አብርኾት) እውነተኛ ዓላማ መመርመራቸውን እንዲቀጥሉ የስብሰባውን አዘጋጆች ሲያበረታቷቸው፡- “የሰውን ልጅ ፍላጎት ለማርካት፣ የሰዎችን ደህንነት እና ሁለንተናዊ እድገት ለማሻሻል ያገለግላል ወይ?” ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ወይንስ "በሰው ልጅ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ቢኖሩም የጥቂት የቴክኖሎጂ ግዙፍ አካላትን ለማበልጸግ እና ለማሳደግ ያገለግላል?" ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ጥያቄ አንስተዋል አክለውም ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ነው ብለዋል።

የሰው ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ፊት ላይ የሚጫወት በመሆኑ፣ “በአእምሮ፣ በልብ እና በእጅ አዲስ መንገድ ለማሰብ እና ለመስራት እድሉ እንዳያመልጠን” ሲሉ ተናግሯል፣ በሰው ልጅ ክብር ላይ ያተኮረ ውቅር" ያስፈልጋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል፣ ይህ ለውይይት የሚቀርብ መሆን የለበትም ሲሉ አስምረው ተናግረዋል።

ማበረታቻ እና ቅስቀሳ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ‘የቼንቲስሙስ አኑስ’ ፋውንዴሽን በዚህ ረገድ ያለውን ቁርጠኝነት “በድፍረት እንዲቀጥል” ሲያበረታቱ፣ በተለይም በፋውንዴሽኑ እና በካቶሊክ የምርምር ዩኒቨርስቲዎች ስልታዊ እና ስትራቴጂካዊ ትብብር (SACRU) መካከል ሁለተኛውን የጋራ የምርምር ፕሮጀክት መጀመሩን አድንቀዋል።

24 June 2024, 14:22