ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ካህናት በሕይወት ጉዞ ብቻቸውን መጓዝ የለባቸውም ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ማለዳ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም በቫቲካን በተካሄደው የቀሳውስት ምልአተ ጉባኤ ተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተው በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሲሆን፥ የካህናት የሕነጻ ትምህርት (የሴሚናሪ)፣ ጥሪን ማሳደግ እና ቋሚ ዲያቆናት ላይ አተኩረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወንድማማች ግንኙነት አውታር ውስጥ የሚኖሩትን ካህናት አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተውበታል፣ ምክንያቱም በሕይወት ጉዞ "ብቻንን እንድንጓዝ የተፈለገን አይደለንም" ያሉ ሲሆን እና ብዙ ውጣ ውረዶችን በመጋፈጥ አብዛኛው ካህናት ለሚሰሩት ልግስና ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
የጳጳሱ ምስጋና
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዓለም ዙሪያ ላሉ ካህናትና ዲያቆናት ምስጋናቸውን በመግለጽ ለታዳሚው ተሳታፊዎች በፍቅር ሰላምታ ሰጥተዋል።
"ከደብተራዊነት እና ከመንፈሳዊ ዓለማዊነት አደጋዎች እንድትጠበቁ ብዙ ጊዜ አስጠንቅቄአለሁ፣ ነገር ግን አብዛኞቹ ካህናት ራሳቸውን በታላቅ ልግስና እና እምነት ለቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሚጠቅሙ፣ ብዙ ድካምና አንዳንዴም ሸክም እንደሚሸከሙ በሚገባ አውቃለሁ። ፈታኝ የሆኑ የሐዋርያዊ እንክብካቤ እና የመንፈሳዊ ችግሮች በመጋፈጥ ጭምር” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
የዘረዐ ክህነት ትምህርት በቂ አይደለም
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የዘረዓ ክህነት ቆይታን የሚመለክቱ ጉዳዮችን በምልአተ ጉባኤው ላይ የተብራሩትን ሦስት ጭብጦች ላይ አትኩረው ተናግረዋ።
በተለይ አሁን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ በየጊዜው በሚለዋወጠው ዓለም ውስጥ ይህ የሴሚናሪ ወይም የዘረዓ ክህነት የሕነጻ ትምህርት ቀጣይነት ያለው መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥው ተናግረዋል።
"የተጠራነው በሴሚናሪ ውስጥ የተማርነውን የሕነጻ ትምህርት እንድናጠናክር፣ እንድናገናዝብ እና እንድናዳብር ነው" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን እነዚህን ነገሮች በሕይወት መተግበር ደግሞ የዘመናችን አዳዲስ ጉዳዮችን በበቂ ሁኔታ ለመፍታት” የረዳናል ብለዋል።
ብቸኝነት
ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ብዙ ቀሳውስትን ያጋጠመው የብቸኝነት ጉዳይ መሠረታዊ ነጥብ እንደ ሆነም ተቁመዋል።
“ይህ ጉዞ ብቻችንን እንዳናደርግ የታሰበ አይደለም” ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ ብዙ ካህናት “በባለቤትነት ስሜት” የተወከለ “የሕይወት መስመር” እንደሌላቸው ጠቁመዋል።
"ጠንካራ የወንድማማችነት ግንኙነቶችን መዘርጋት ቀጣይነት ያለው የሕነጻ ወይም የሴሚናሪ ሕይወት ትምህርት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው… ካህናት 'ቤታቸው ውስጥ' እንደሆኑ እንዲሰማቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው። እናንተ እንደ የቅድስት መንበር የቀሳውስት ጽሕፈት ቤት አለምአቀፍ አውታረ መረብን መዘርጋት ጀምራችኋል፣ ይህ እንዲቀጥል እና በአለም ዙሪያ ፍሬ እንዲያፈራ የተቻለውን ሁሉ እንድታደርጉ እለምናችኋለሁ” ማለታቸው ተገልጿል።
የጥሪ ማሽቆልቆል
የክህነት እና የተቀደሰ ሕይወት ጥሪ ማሽቆልቆል “ለእግዚአብሔር ሕዝብ ትልቅ ፈተናዎች አንዱ ነው” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።
ቀውሱ በትዳር ጥሪም ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድርም አክለዋል። በዚህም ምክንያት፣ በቅርቡ ለዓለም የጥሪ የጸሎተ ቀን ያስተላለፉት መልእክቶች ትኩረቱን “ሁሉንም ክርስቲያናዊ ጥሪዎች ለማካተት” በተለይም የተጠመቁትን ሁሉ አንድ የሚያደርግ “የደቀ መዝሙርነት ጥሪ” ትኩረት እንዳሳበ አስረድተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “እራሳችንን ከእዚህ ጉዳይ ማሸሽ አንችልም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ቋሚ ዲያቆናትን የተመለከቱ ጉዳዮች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል የምልአተ ጉባኤውን ሦስተኛውን ጭብጥ፡- “የተወሰነው ማንነቱ” ዛሬ ብዙ ጊዜ ጥያቄ የሚያስነሳው የቋሚ ዲያቆናት ጉዳይ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደው ሲኖዶስ የመጀመርያው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አስተፃምሮ ወይም ጠቅለል ያለ ሪፖርት ባቀረበው አስተያየት በተለይ በዲያቆናት አገልግሎት እና ለድሆች በሚደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት ምጽዋት ላይ በማተኮር በዚህ አገልግሎት ላይ ለሚደረገው ነጸብራቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጳጳሱ ጋብዘዋል።
"ከእነዚህ ነጸብራቆች እና እድገቶች ጋር አብሮ መሄድ በቅድስት መንበር የቀሳውስትን ጉዳዮች የሚከታተለው ጽሕፈት ቤት በጣም አስፈላጊ ተግባር ነው። ለዚህም እንድትሰሩ እና ሁሉንም አስፈላጊ ሀብቶች እንድታንቀሳቅሱ እመክራችኋለሁ" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን ተሳታፊዎቹ ወደ ሥራ በመጋበዝ አጠናቅቀው "የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደ ክርስቶስ ልብ የሚያስቡ ካህናት እንዲኖራቸው" በመጋበዝ የመንፈሳዊ ጥሪዎች ሁሉ ተምሳሌት የሆነችው ማርያም በጉዟቸው እንድታጀባቸው ከተማጸኑ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።