ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የካንታሊሱ የቅዱስ ፊሊክስ እህቶች እና የእመቤታችን ኪዳነምህረት ሴት ልጆች የደናግላን ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የካንታሊሱ የቅዱስ ፊሊክስ እህቶች እና የእመቤታችን ኪዳነምህረት ሴት ልጆች የደናግላን ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመነኮሳት፡- እናንተ የጌታ መሣሪያዎች ናችሁ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካንታሊሱ የቅዱስ ፊሊክስ እህቶች እና የእመቤታችን ኪዳነምህረት ሴት ልጆች የደናግላን ማሕበር እራሳቸውን ለጌታ እንዲያስገዙ፣ ሁል ጊዜ ፈቃዱን እንዲያከብሩ እና ሁል ጊዜ በልግስና እንዲሰጡ ጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"እኛ ሁላችንም በእግዚአብሔር ጥበበኛ እጅ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች ነን!" ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአጠቃላይ የስብሰባ ምዕራፋቸውን ምክንያት በማድረግ ሐሙስ ዕለት ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ቫቲካንን ለጎበኙት የካንታሊሱ ቅዱስ ፊሊክስ እህቶች እና የእመቤታችን ኪዳነ ምሕረት ሴት ልጆች ደናግላን ማሕበር ባደረጉት ንግግር ነበር ይህንን የተናገሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእግዚአብሔር እና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ላደረጉት ጉብኝት አድናቆታቸውን በመግለጽ ውይይቱን ጀመሩ።

“አገልግሎት በእናንተ ማሕበር የምሥረታ ሕይወት ውስጥ አንድ የተለመደ አካል ነው፣ ይህም በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በተመሳሳይ ታሪካዊ ወቅት፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆንም” ብሏል።

ቅዱስ አባታችን የየማሕበራቸውን መሥራሳቾች ሕይወት ለማስታወስ ትንሽ ጊዜ ወስደዋል።

መጀመሪያ ላይ ሶፊያ ካሚላ ትሩዝኮቭስካ፣ በኋላ ላይ እህት አንጄላ ማሪያ ተብላ የምትጠራው፣ በዋርሶ የቅዱስ ፊሊክስ የካንታሊስ እህትማማቾችን ማሕበር እንደመሰረተች ተናግሯል፣ “በጦርነት በተቸገረ ፖላንድ ውስጥ፣ ህጻናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ወጣቶችን ለማገልገል ሲሉ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

በዚሁ ወቅት፣ በጣሊያን ሳቮና፣ ቤኔዴታ ሮስሴሎ የምትባል ሌላ ወጣት ሴት፣ በኋላም እህት ማሪያ ጁሴፓ በመባል ትታወቅ የነበረች፣ በጳጳሷ መሪነት ድሆችን እና ሕፃናትን ማገልገል መጀመሯን አስታውሰዋል። ወጣት ሴቶች የእመቤታችን ኪዳነምህረት ሴት ልጆችን ማሕበር እንደ እንደመሰረተች ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

እግዚአብሔር በእነሱ በኩል እንደሚሰራ ለእህቶች በማሳሰብ “ከትንሽነታችን ውስጥ የሚቀዳውን ጌታ ማን ሊያስብ ይችላል” ሲሉ በመገረም ቅዱስነታቸው ተናግረዋል። "ጌታ ከትንሿ 'አዎ' ምን እንደሚያወጣ መገመት የሚችል ማን ነው?" ሲሉ በድጋሚ ጥያቄ አንስተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን በማሰብ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ያላቸውን ታማኝነት በታማኝነት እና በመንፈስ ቅዱስ ተግባር ላይ እንዲጸኑ አበረታቷቸዋል።

“ራሳችሁን ለእርሱ አስገዙ፣ እናም ሁሉንም ነገር ሁል ጊዜ በልግስና ስጡ” ሲሉ ጳጳሱ አሳስበዋል።

07 June 2024, 11:33