ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 'በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ' ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቺካጎ በሚገኘው በሎዮላ ዩኒቬርሲቲ ከላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በቀጥታ የዌቢናር መስመር በተዘጋጀው “በኤዥያ ፓሲፊክ ማዶ ድልድይ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ምንጊዜም በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ .... እና ሌሎች ስለሚያሰቃዩዋችሁ ለብ ያለ እምነት እንድትኖሩ ብትፈተኑ እንኳ ማንነታችሁን አጥብቃችሁ ያዙ፣ በስደት ጊዜ እንደ ነበሩት የክርስቲያን ሰማዕታት ጠንካሮች ሁኑ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ይህ መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእስያ ከመጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የሰጡት አስተያየት ነበር። ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም በሎዮላ ዩኒቨርሲቲ ቺካጎ እና በላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን በተዘጋጀው “በኤዥያ ፓስፊክ አቋራጭ ድልድይ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ዌቢናር ላይ ካስተላለፉት መልእክት የተወሰደ ነው።

ቅዱስ አባታችን በቀጥታ ስርጭት ተሳትፈዋል።

የሎዮላ ዩኒቨርሲቲ ቺካጎ ድልድዮችን የመገንባት ተነሳሽነት (Building Bridges Initiative (BBI) ተማሪዎችን ያማከለ እና በዩኒቨርሲቲዎች የተደራጀ ተከታታይ ዝግጅቶችን መጀመሩ ተገልጿል፣ ይህም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲኖዶሳዊ ጥሪ በመነሳሳት የተጀመረ ተነሳችነት ነው። የመጀመሪያው ስብስባ የተካሄደው እ.አ.አ በየካቲት 2022 ዓ.ም "ሰሜን-ደቡብን የምያገናኝ ድልድይ መገንባት” በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ሁለተኛው "በአፍሪካ ውስጥ ድልድዮችን መግንባት" በሚል መሪ ቃል በዚሁ አመት እ.አ.አ በህዳር ወር ላይ ተካሂዶ ነበር፥ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትን ተማሪዎችን ያሳተፈ ነበር። ይህ በሰኔ 13/2016 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ ተመሳሳይ ሞዴል የተከተለ ቢሆንም የጳጳሱን ተሳትፎ በደስታ ተቀብሏል።

በዚህ የቅርብ ጊዜ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከተሳተፉት መካከል ከአቴኔኦ ዴ ማኒላ ዩኒቨርሲቲ (ማኒላ፣ ፊሊፒንስ) የተውጣጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የተለያዩ ዘርፎችን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። የአውስትራሊያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ (ብሪዝበን፣ አውስትራሊያ)፥ ፉ ጄን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ (ታይፔ፣ ታይዋን)፥ የሶጋንግ ዩኒቨርሲቲ (ሴኡል፣ ደቡብ ኮሪያ)፥ ሶፊያ ዩኒቨርሲቲ (ቶኪዮ፣ ጃፓን)፥ ዩንቨርስቲዎች ሴናታን ዳርማ (ዮጊያካርታ፣ ኢንዶኔዥያ) በቀጥታ መስመር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎች እንደ ነበሩ ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጪው መክሰረም ወር ወደ እስያ እና ኦሺኒያ በሚያደርጓቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች ከሲንጋፖር፣ ከቲሞር ሌስቴ እና ከፓፑዋ ኒው ጊኒ አገሮች የተውጣጡ ተማሪዎች በስብሰባው ላይ ተሳትፈዋል። በተጋላጭነትዎ ውስጥ ሌሎች እንዲረዷችሁ ጠይቁ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቀጥታ መስመር በተካሄደው ስብሰባ ላይ በሥፓኒሽ ቋንቋ በበስብሰባው ላይ የተገኙትን ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጡ እና በተለያዩ ተግባራት የተነሳ በስብሰባው ላይ ዘግይተው በመድረሳቸው ቅዱስነታቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የተማሪዎቹ ቡድኖች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመተዋወቅ አስተያየቶችን አቅርበዋል፣ ቅዱስ አባታችንም በምላሹ ምክራቸውን፣ ስጋታቸውን እና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቅዱስ አባታችን ለመጀመሪያው ቡድን የህብረተሰቡ አባል የመሆናችንን ስሜት እና የእኛ 'መሆን' እንዴት በራሳችን እና በራሳችን ሰብአዊ ክብራችን ላይ ደህንነታችንን እንደሚያጎለብት ተናግሯል።

እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች "ከተጋላጭነት ያድነናል፣ ምክንያቱም ዛሬ ወጣቶች በጣም የተጋለጡ ናቸው። ሁልጊዜም ተጋላጭነትን ለማስወገድ ይህንን የባለቤትነት ስሜት መጠበቅ አለብን" ብለዋል።

"በጣም ተጋላጭ የሆናችሁበትን ቦታ ተመልከቱ እና አንድ ሰው እንዲረዳችሁ ጠይቁ” ብለዋ ቅዱስነታቸው።  

የሴቶች ታላቅነት ፈጽሞ ሊረሳ አይገባም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በአእምሮ ጤንነት፣ አድልዎ፣ መገለል እና ማንነት ላይ ተወያይተው ምስክርነት እንዲሰጡና እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

"የራሳችሁን ማንነት በማሳየት ላይ አተኩሩ" በማለት በቦታው የተገኙት ሁሉ፣ ሁል ጊዜ እርስ በርስ እንዲተባበሩና አንድነታቸውን አጥብቀው እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰውን ሰብአዊ ክብር የሚቀንሱትን ሁሉንም መገለሎች ወቅሰዋል። አንዳንድ ጊዜ ሴቶች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ይቆጠራሉ፣ ይህም ሁሉም ሰው እውነት እንዳልሆነ ያውቃል ያሉ ሲሆን "የሴቶች ታላቅነት መዘንጋት የለበትም። ሴቶች በአስተዋይነታቸው እና ማህበረሰቦችን በመገንባት ችሎታቸው ከወንዶች የተሻሉ ናቸው" ሲሉም ለሴቶች ልዩ ባህሪያትና ብቃቶች አድንቀዋል።

መገለል እና ማግለል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተማሪዎች ከሌሎች ጋር መቀራረብ እና ፍቅር እንዲያሳዩ እና ፈጽሞ እንዳይገለሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በፊሊፒንስ ያለውን ከፍተኛ የኤችአይቪ መጠን በመጥቀስ ስለሥርዓተ-ፆታ ያወሳው ተማሪ የተናገረውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማስታወስ፣ "ጤና አጠባበቅ ሁሉንም ሰው ለማከም እና ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፣ ያለ ማግለል" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም ውጤታማ ትምህርትን በተመለከተ ተወያይተዋል፣ በእርሳቸው አስተያየት "ልቦቻችንን፣ አእምሮዎቻችንን እና እጆቻችንን" "ማስተማር" እና "ማስተባበር" ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ወጣቶችን ማስተማር ያለብን በዚህ መንገድ ነው፣ ይህ ተለዋዋጭነት ፈጽሞ ሊረሳ እንደማይገባም ጠቁመዋል።

ከጸሎት እና ከሌሎች ጋር የተገናኙ ልቦች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለወጣት ክርስቲያኖች በኅብረተሰቡ ውስጥ መሳተፍ እና "መሆን" ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ አመልክተዋል፣ ከዚህ እውነታ አንፃር፣ በእምነታቸው እንዲጸኑ፣ ልባቸውንም ከጸሎት ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳስቧቸዋል።

ይህን ማድረጋችሁ በዚህ ረገድ የሚረዳችሁ እና ከሌሎች ጋር ሁል ጊዜ ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆኑ ያስችላችኋል ብለዋል።

የተበረዘ ክርስትናን እምቢ ማለት እና እምነትን አጥብቆ መያዝ

ቅዱስ አባታችን በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች ወጣቶች በእምነታቸው ምክንያት የሚዘባበቱበት ወይም የሚቃወሙበት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።

መገለል እንዳይኖር ሲያስጠነቅቁ "ሁልጊዜ በራሳችሁ እምነት እርግጠኛ ሁኑ" ሲሉ መክሯል፣ ይህም ወደ መጥፎ ልማዶች እና ችግሮች ሊመራ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ከዚህ በመነሳት ጳጳሱ በእምነት መማር እና እውነተኛ እና ሐቀኛ ክርስቲያኖች የመሆንን አስፈላጊነት አስምረውበታል።

“ነገሩ ይህ ነው፤ ክርስቲያኖች ገና ከጅምሩ ይሰደዱ ነበር” በማለት ይህ ክስተት አዲስ ነገር እንዳልሆነ እውነታውን አጉልቶ አሳይቷል።

"የተበረዘ፣ ለብ ያለ ክርስትና መኖሩ ፈታኝ ቢሆንም" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተናገሩ ሲሆን፣ ለእርሱ እጅ መስጠት አንችልም። ይልቁንም “ጠንካሮች መሆን አለብን፣ እናም በዚህ መልኩ በሰማዕትነት መኖር አለብን” ሲሉ ተማጽኗል።

የርዕዮተ ዓለም በሽታ

በመጨረሻም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያለፈውን አሳዛኝ ሁኔታ የበለጠ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለወደፊት ትምህርት እንዲወስዱ እና ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

"ርዕዮተ ዓለም በሽታ ነው" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁሉም ህዝቦች መግባባት እንዲፈጥሩ እና ከሌሎች ባህሎች ጋር ውይይት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

“ለጦርነትን አሻፈረኝ” በማለት አስፈላጊ ነው ሰላም እንዲሰፍን መንገድ ይከፍታክ ሲሉ ተናግረዋል፣  "ተስፋ በሌለው እና ተስፋ በቆረጠ አለም ውስጥ እሴቶቻችንን መማረክ አለብን" ሲሉም በቦታው የነበሩ ተማሪዎች ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን ከማቅረባቸው በፊት በዚህ ላይ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ ለተማሪዎቹ ለሰጡት አስተያየት በማመስገን በተለይም በመስከረም ወር መጀመሪያ ወደ ክልላቸው ለሚያደርጉት ጉዞ ሲዘጋጁ  አሁን ያደረጉት ውይይት እንደሚረዳቸው ገልፀውላቸዋል።

ድልድይ መገንባት በእያንዳንዳችን ይጀምራል

የተለያዩ የቫቲካን ጽ/ቤቶች የሲኖዶስ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት፣ የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ የምእመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት ጉዳዮችን የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽህፈት ቤት፣ የትምህርትና የባህል ጽህፈት ቤት እና የስብከተ ወንጌል ክፍል የመጀመሪያ የስብከተ ወንጌልና አዲስ ክፍልን ጨምሮ የተለያዩ የቫቲካን ጽ/ቤቶች ይህ ስብሰባ ይሳካ ዘንድ እገዛ አድርገዋል።

21 June 2024, 16:35