ፈልግ

በቫቲካን 16ኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ በቫቲካን 16ኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ  (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ችላ የተባሉ እና ተገቢ ዋጋ ያልተሰጣቸውን ሴቶች አዳምጡ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁለት ካርዲናሎች እና ሦስት ሴት የነገረ መለኮት ሊቃውንት የጻፉት “ሴቶች እና በሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው አገልግሎት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን መጽሐፍ መቅድም መጻፋቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሴቶች፣ መንፈሳዊ አገልጋዮች፣ ሲኖዶሳዊነት፣ የጥቃት ሰለባዎች፡ እነዚህ ሁሉ የቤተክርስቲያን ስሜታዊ የሆኑ ጭብጦች በመግቢያው መቅድም ላይ ይገኛሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሴቶች እና በሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው አገልግሎት” በሚል ርዕስ ለተዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ መቅድም ጽፈዋል።

መጽሐፉ በሶስት ሴት የነገረ-መለኮት ምሁራን እና በሁለት ካርዲናሎች ትብብር የተጻፈ ነው። የነገረ መለኮት ሊቃውንቶቹ የሳሌዢያን ማሕበር አባል የሆኑ እህት ሊንዳ ፖቸር፣ በሮም በሚገኘው አክሲሉም የነገረ-ክርስቶስ (የክርስቶሎጂ) እና የነገረ-ማርያም (ማሪዮሎጂ) ፕሮፌሰር (መግቢያውን የጻፉ) ናቸው። በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እና የአንግሊካን ሕብረት ዋና ጸሐፊ ጆ ቢ ዌልስ፣ እና ጁሊቫ ዲ ቤራዲኖ፣ ከቬሮና ሀገረ ስብከት የተገኘውና የኦርዶ ቨርጂንየም ማሕበር አባል፣ የሥርዓተ አምልኮ መምህር፣ የመንፈሳዊ ትምህርት እና የሱባኤ አዘጋጅ የሆኑት ይገኙበታል።  

ከእነሱ ጎን ለጎን የሉክሰምበርግ ሊቀ ጳጳስ ዣን ክላውድ ሆሌሪች እና የሲኖዶሱ ዋና ጸኃፊ እና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ጥበቃ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ካርዲናል ሴያን ፓትሪክ ኦማሌይ ይገኙበታል።

በደራሲዎች መካከል የተደረገ ውይይት

መጽሐፉ እ.አ.አ በየካቲት 5/2024 ዓ.ም በሚታወቀው ስብሰባ ላይ በሊቀ ጳጳሱ እና በካርዲናሎች ጉባኤ መካከል በተደረገው እውነተኛ ውይይት ላይ በመመርኮዝ በደራሲዎች መካከል "ሥነ-ጽሑፋዊ" ውይይት የተደረገበት ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሴት የነገረ መለኮት ሊቃውንት በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ በጳጳሱ ተጋብዘው ነበር፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደሚገልጹት በቤተክርስቲያን ውስጥ “የሴቶች ሚና” በሚል መሪ ቃል በስብሰባው ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

እ.አ.አ በሐምሌ 9 የታተመው አዲሱ መጽሃፍ ቀደም ሲል በእህት ሊንዳ ፖቸር እና በሌሎች ደራሲዎች “ቤተክርስትያንን ከተባዕታዊ መንፈስ ማላቀቅ” (በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት የሚታየውን የወንዶችን ተሳትፎ በመቀነስ ሴቶችን በእኩልነት መንፈስ ማሳተፍ) በሚል ርዕስ የሰሩትን ስራ ተከትሎ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዓለም አቀፉ የሥነ መለኮት ኮሚሽን ጋር በተገናኙበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ቃል ነበር።

የቤተ ክህነት አገልግሎት፡ ጠቃሚ እና ረቂቅ ርዕስ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሙሉ በሙሉ በሐምሌ 04/2016 ዓ.ም “ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ” በተባለው ጋዜጣ ላይ በታተመው መቅድም ላይ፣ “እውነታው ከሐሳቦች የበለጠ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዋና ሐሳብ በመነሳት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ይህ መርህ የእህት ፖቸርን የካርዲናሎች ምክር ቤት መርሃ ግብር በቤተክርስቲያን የሴቶች ጭብጥ ላይ በመመራት የተደረገውን ለውጥ በተመለከተ የተሰማቸውን እርካታ ገልጸዋል፣ በተለይም በቤ ተክርስቲያኗ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጠቃሚ እና ጥንቃቄ የተሞላበት የአገልግሎት ርዕስ በተመለከተ ማለት ነው።

የመጎሳቆል አሳዛኝ ክስተት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት የመጎሳቆል ቀውሱ የተሾሙ አገልጋዮችን ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለውን ሰፋ ያለ የሥልጣን አላግባብ መጠቀምን የሚወክል፣ ምዕመናንና ሴቶችን ጭምር የሚጎዳ የሃይማኖት አባቶችን ፊት ለፊት መጋፈጥ አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የሴቶችን ደስታና ስቃይ ማዳመጥ ራሳችንን ለእውነት የምንገልጽበት መንገድ ነው” ብለዋል። “ያለ ፍርድና ጭፍን ጥላቻ በማዳመጥ፣ በብዙ ቦታዎችና ሁኔታዎች በትክክል እንደሚሰቃዩ እንገነዘባለን። ቦታ እና እድል ነበራቸው። ብዙ ጊዜ የሚሠቃዩት ሴቶች ብዙውን ጊዜ በጣም ቅርብ የሆኑት፣ በጣም የሚገኙ፣ የተዘጋጁ እና አምላክንና መንግሥቱን ለማገልገል የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ አክለው ጸፈዋል።

በሃሳቦች መሠዊያ ላይ እውነታውን መስዋዕት ማድረግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለዚህ በዘመናዊው ዘመን ቤተክርስቲያን ራሷ ብዙ ጊዜ በተደናቀፈችበት “ወጥመድ” ውስጥ እንዳንወድቅ ከሃሳቦች ይልቅ እውነታውን እንድንመለከት ይጋብዙናል፣ ማለትም “ከአስተያየቶች የበለጠ አስፈላጊ ታማኝነትን ከግምት ውስጥ የማስገባት” ወጥመድ በመሸጋር ለእውነታው ትኩረት ስጡ" ሲሉ ተናግረዋል።

"እውነታው ግን ሁል ጊዜ ከሃሳቡ ይበልጣል፣ እናም የእኛ ስነ-መለኮት ግልጽ እና ግልጽ በሆኑ ሀሳቦች ወጥመድ ውስጥ ሲወድቅ፣ በሃሳቡ መሠዊያ ላይ ያለውን እውነታ ወይም ከፊል መስዋእት በማድረግ ወደ “Procrustean bed” (በዘፈቀደ እና ምናልባትም ያለ ርህራሄ - አንድን ሰው ወይም አንድ ነገር ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ እቅድ ወይም ንድፍ ሐስብ ውስጥ እንዲገባ ማስገደድ የሚያመልክት ምሳሌ ነው) መቀየሩ የማይቀር ነው" በማለት ቅዱስነታቸው በመቅድም ጽሑፋቸው አክለው ገልጸዋል።

“ሴቶች እና በሲኖዶሳዊው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው አገልግሎት” የሚለው ጥራዝ ትሩፋቱ “ከሃሳቡ የሚጀምር ሳይሆን እውነታውን ከማዳመጥ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ የሴቶችን ልምድ በጥበብ የተረጎመ ነው” የሚል ነው።

በሲኖዶሱ “Instrumentum Laboris” (የድርጊት መርሃ ግብር) ውስጥ የሴቶች ሚና

የሴቶች ሚና ጉዳይም በቅርቡ በታተመው መጽሐፍ መቅድም ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን በጥቅምት ወር ለሚካሄደው የሲኖዶስ ጉባኤ በቅርቡ በታተመው በላቲን ቋንቋ “Instrumentum Laboris” (የድርጊት መርሃ ግብር) ላይ ተብራርቷል። ሰነዱ ለሴቶች ስጦታዎች እና ጥሪዎች የበለጠ እውቅና የማግኘት አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ይሰጣል፣ የአስተሳሰብ ለውጥ ወደ ተዛመደ፣ እርስ በርስ የሚደጋገፉ እና የተገላቢጦሽ አመለካከት ወንዶች እና ሴቶች በክርስቶስ እንደ እህትማማቾች፣ በቤተክርስቲያኗ ተልእኮ ውስጥ አንድ ሆነው እንዲኖሩ የሚጠይቅ ሰነድ ነው።

የሴቶችን የድቁና አገልግሎት በተመለከተ የሲኖዶሱ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች፥ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከተቋቋሙት የጥናት ቡድኖች መካከል አንዱ በሆነው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ በጥልቀት ወደ ሥነ መለኮት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ላይ ለማሰላሰል በሚደረገው ጉባኤ ላይ እንደማይታይ ጠቁመዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሴቶችን የድቁና አገልግሎት ጉዳይ ከሲኖዶሱ አጠቃላይ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በአገልጋይነት ማዕቀፍ ውስጥ የእምነት አስተምህሮት ለሚመለከተው ጽኃፈት ቤት አደራ ሰጥተዋል።

ይህ ጥረት በመጋቢት ወር በወጣው ጥናት ላይ በቀረበው ሰነድ ላይ እንደተገለጸው የሲኖዶስ ጉባኤው ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው "ለሴቶች አስተዋፅኦ የላቀ እውቅና እና አድናቆት እና የሐዋርያዊ አገልግሎት በሁሉም ዘርፍ የተሰጣቸው ኃላፊነት እንዲጨምር ለማድረግ ነው። የቤተክርስቲያን ህይወት እና ተልዕኮ ውስጥ የሴቶችን ሚና ከፍ ለማድረግ ይችላል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳ።

12 July 2024, 16:38