ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሕይወት ሙላት ለማግኘት የበጎ አድራጎት መንገድ እንድንከተል ያበረታታሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምእመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሐምሌ 28/2016 ዓ.ም በአደረጉት አስተንትኖ የሕይወት ሙላት ለማግኘት የበጎ አድራጎት መንገድ መከተል ያስፈልጋል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደምከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው እለት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል በአምስት ትንንሽ የገብስ እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣዎች አምስት ሺ ሰው ኢየሱስ ከመገበ በኋላ እርሱን የሚሹት ሰዎች ስለ ተፈጸመው ነገር እንዲያሰላስሉ በመጋበዝ የቃሉን ትርጉም እንዲረዱ (ዮሐ. 6፡24-35) ትቶዋቸው ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ስለሄደው ኢየሱስ ያናገራል።

በአንድ ለጋስ ወጣት የተሰጠውን ትንሽ ዓሣ እና የገብስ ቂጣ በልተው ከጠገቡ በኋላ ነበር ኢየሱስን ለመፈለግ የወጡት (ዮሐ. 6፡1-13)። ምልክቱ ግልጽ ነበር፡ ሁሉም ያለውን ለሌላው ቢሰጥ፣ በእግዚአብሔር እርዳታ፣ በትንሽም ቢሆን ሁሉም ሰው የሆነ ነገር ሊኖረው ይችላል። ይህን አንርሳ፡ አንድ ሰው ያለውን ለሌላው ቢሰጥ፣ በእግዚአብሔር እርዳታ፣ በትንሽም ቢሆን ሁሉም ሰው የሆነ ነገር ሊኖረው ይችላል።

ሕዝቡ አልተረዱም፡ ኢየሱስን እንደ አስማተኛ አድርገው በመቁጠር ሳቱ እና ተአምሩን እንደ አስማት ይደግማል ብለው ተስፋ አድርገው ሊፈልጉት ተመለሱ (6፡26)።

በጉዟቸው ውስጥ የልምዳቸው ዋና ተዋናዮች ነበሩ፣ ነገር ግን ፋይዳው አልገባቸውም ነበር፡ ትኩረታቸው በዳቦና በዓሣ ላይ ብቻ ያተኮረ ሲሆን ይህም ወዲያውኑ በተጠናቀቀው ምግብ ላይ ነበር። ይህም አብ ረሃባቸውን ሲያረካ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር የገለጠላቸው መሳሪያ ብቻ መሆኑን አላስተዋሉም። አብስ ምን ገለጠላቸው? ለዘለአለም የሚዘልቅ የህይወት መንገድ እና ከየትኛውም መለኪያ በላይ የሚያረካ የእንጀራ ጣዕም። እውነተኛው እንጀራ፣ ባጭሩ፣ ሥጋ ለብሶ ሰው የሆነው ኢየሱስ ነበርና ነው (ዮሐ 6፡35)፣ እሱም ድኅነታችንን ሊካፈል የመጣው በእርሱ በኩል ከእግዚአብሔር እና ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር ሙሉ ኅብረት ወዳለበት ደስታ ሊመራን ነው (ዮሐ. 3፡16)።

ቁሳዊ ነገሮች ለሕይወት ሙላትን አይሰጡም። ወደፊት እንድንሄድ ይረዱናል እና አስፈላጊ ናቸው፣ ነገር ግን ህይወታችንን አያሟሉም። ያንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው (ዮሐ. 6፡35)። ይህ እንዲሆን ደግሞ የሚወስደው መንገድ የበጎ አድራጎት ስራ ነው፣ ለራሱ ምንም ነገር የማይዝ፣ ነገር ግን ሁሉንም ነገር የሚያጋራ፣ ፍቅር ሁሉንም ነገር ያካፍላል።

እና ይህ በእኛ ቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠር ነገር አይደለምን? እኛ ማየት እንችላለን። ልጆቻቸውን በጥሩ ሁኔታ ለማሳደግ እና ለወደፊት አንድ ነገር ለመተው ህይወታቸውን ሙሉ የሚታገሉ ወላጆችን እናስብ። ይህን መልእክት ሲረዱ እና ልጆቹ አመስጋኞች ሲሆኑ እና እንደ ወንድም እና እህቶች እርስ በርሳቸው ሲደጋገፉ ምንኛ ውብ ነው! በሌላ በኩል በውርስ ሲጣሉ እንዴት ያሳዝናል - ብዙ ጉዳዮችን አይቻለሁ እና ያሳዝናል - እና እርስ በእርሳቸው እየተጣሉ ምናልባትም ለዓመታት እንደገና አይነጋገሩም! የአባትና የእናት መልእክት፣ እጅግ ውድ ትሩፋታቸው፣ ገንዘብ አይደለም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳደረገው ለልጆቻቸው ያላቸውን ሁሉ የሚሰጧቸው ፍቅራቸው ነው በዚህ መንገድ ፍቅርን ያስተምሩናል።

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ፡ ከቁሳዊ ነገሮች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት አለኝ? የነርሱ ባሪያ ነኝ ወይስ በነጻነት ፍቅርን ለመስጠትና ለመቀበል እንደ መሣሪያ እጠቀማቸዋለሁ? እግዚአብሔርን፣ ወንድሞቼን እና እህቶቼን ለተቀበልኩት ስጦታዎች "አመሰግናለሁ" ማለት እችላለሁን? እና እነሱን ለሌሎች እንዴት ማካፈል እንዳለብኝ አውቃለሁ?

ለኢየሱስን ሙሉ ህይወቷን የሰጠች ማርያም ሁሉንም ነገር የፍቅር መሳሪያ እንድናደርግ እርሷ በአማልጅነቷ ትርዳን። 

05 August 2024, 10:10