ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበር ጥሪ አቀረቡ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በዩክሬን ያለውን የሃይማኖት ነፃነት አስመልክተው የዩክሬይን ፓርላማ በቅርቡ ከሞስኮ ፓትርያርክ ጋር ግንኙነት ያለው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለማገድ ያሳለፈውን ውሳኔ በማጣቀስ ሥጋታቸውን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል....
"በዩክሬን እና በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ የተካሄደውን ውጊያ በሀዘን መንፈስ ሆኜ መከታተሌን እቀጥላለሁ። እናም በቅርቡ ዩክሬን ስላፀደቀቻቸው ህጎች በማሰብ ፣ የሚጸልዩ ሰዎች ነፃነት እንዳይጎዳ እፈራለሁ ፣ ምክንያቱም በእውነት የሚጸልዩ ሁል ጊዜ ስለ ሁሉም ይጸልያሉ። ሰው በጸሎት ምክንያት ክፉ አያደርግም። አንድ ሰው በወገኖቹ ላይ ክፉ ነገር ቢያደርግ በደለኛ ይሆናል፥ ነገር ግን ስለጸለየ ክፋት ሊሠራ አይችልም። ስለዚህ መጸለይ የሚፈልጉ እንደ ቤተ ክርስቲያናቸው በሚቆጥሩት ውስጥ እንዲጸልዩ ይፈቀድላቸው። እባካችሁ የትኛውም የክርስቲያን ቤተክርስቲያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አይፍረስ። አብያተ ክርስቲያናት መነካት የለባቸውም!”
የኪዬቭ ውሳኔ
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 20/2024 ዓ.ም በኪየቭ በአብላጫ ድምጽ የወጣው ረቂቅ ህግ ለሚመለከታቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በተላለፈው መልእክት ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ዘጠኝ ወራትን ብቻ ይሰጣል ፣ይህ እርምጃ ከሞስኮ ፓትርያርክ ቤተክርስቲያን ፈጣን ምላሽ የተሰጠው ሲሆን ይህም “በአለም አቀፍ ደረጃ ግልጽ ጥሰት ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል ። በሃይማኖታዊ ነፃነት መስክ የታወቁ ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ ውሳኔ ነው ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።
ስለ ሰላም ጸሎቶች
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፍልስጤምን፣ እስራኤልን፣ ምያንማርን እና በእነርሱ ምክንያት እና በጦርነት ሰበብ የሚሠቃዩትን የዓለም ክፍሎች በመጥቀስ ጦርነት እንዲያበቃ ሁሉም እንዲጸልይ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። "ህዝቡ ሰላም እየጠየቀ ነው! ጌታ ለሁላችንም ሰላም እንዲሰጠን እንፀልይ" ሲሉ አፅንዖት ሰጥው ከተናገሩ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠቃለዋል።