ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ከተደራጁት የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች መሪዎች ጋር ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ከተደራጁት የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች መሪዎች ጋር  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ በአሜሪካ የተደራጁ የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች መሪዎችን በቫቲካን ተቀብለው አነጋገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን የተደራጁ የማኅበረሰቦች መሪዎች ጋር በቫቲካን ተገናኝተዋል። የልዩ ልዩ ማኅበረሰቦች መሪዎች ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በቅድስት ማርታ የጳጳሳት መኖሪያ ውስጥ ረቡዕ ነሐሴ 22/2016 ዓ. ም. በተገት ወቅት ኅብረቱ ያመጣውን ዕድገት በሪፖርት ለቅዱስነታቸው አቅርበው ምክረ ሃሳብ ከተቀበሉ በኋላ በሚቀጥሉት እርምጃዎች ላይ ለመወያየት እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ካህናትን እና ምእመናንን ጨምሮ ወደ 20 የሚጠጉ አባላት አዲሱን የልዩ ልዩ ማኅበረሰቦች ትሥሥርን የሚገልጽ ሠነድንም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያቀረቡ ሲሆን፥ ዓላማውም በአገራቸው ከሚገኙ ብጹዓን ጳጳሳት ጋር በመሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮን ተግባራዊ ለማድረግ ግንባር ቀደም ሆነው ለመቀጠል እና በወንጌል የታገዘ ሕይወትን ለመኖር ያለመ እንደሆነ ታውቋል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የነበራቸው ቆይታ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከእንግዶቹ ጋር በተሰበሰቡ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት፥ መሪዎቹ የሲኖዶሳዊነት ድልድይ በመገንባት ሕዝቦቻቸው መልካም ሕይወት እንዲኖራቸው እንዲያደርጉ አበረታትተዋል።

በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን አስተባባሪ አቶ ጆርጌ ሞንቲኤል ከቅዱስነታቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ እንደተናገሩት፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሰዎችን የመደራጀት ችሎታ በእጅጉ እንደሚያደንቁ እና “የሕዝብ ሃብት ራሱን የማደራጀት አቅም ነው” ማለታቸውን ገልጸዋል። በማከልም የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ “ፖለቲካ ትልቁ የበጎ አድራጎት መግለጫ ነው” ያሉትን ማስታወሳቸውን ተናግረዋል።

በቴክሳስ ከቅዱስ አንጦንዮስ ሀገረ ስብከት የመጡት አቶ ማርያ ጉዋዳሉፕ ቫልዴዝ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የነበራቸውን ቆይታ በማስታወስ እንደተናገሩት፥ “ቅዱስነታቸው ግዴለሽነትን አስወግደን ወደ ፊት መጓዝ እንድንቀጥል አበረታተውናል” ብለዋል። በምዕራባዊ ደቡብ የአሜሪካ ግዛት የኢንደስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን አባል የሆኑት ወ/ሮ ኤልዛቤጥ ቫልዴዝ በበኩላቸው፥ የማኅበረሰቦቹ ትሥሥር አብያተ ክርስቲያናትን፣ ማኅበራትን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ካቶሊክ ምዕመናን በአብላጫነት የሚገኙበትን፣ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን፣ ምኩራቦችን እና መስጊዶችን ያቀፈ መሆኑን አስታውሰዋል።

በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን ተወካዮች ረቡዕ ጠዋት ቀደም ብለው የላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጸሐፊ ከሆኑት ከኤሚልስ ኩዳ ጋር ተገናኝተው ለጋራ ጥቅም ሲባል በደቡብ እና በሰሜን አሜሪካ መካከል ግንኙነቶችን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ ላይ በማተኮር ተወያይተዋል።

ወደ ቤተ ክርስቲያን የተደራጁ ማኅበረሰቦች የሚወስድ መንገድ
የቤተ ክርስቲያን የተደራጁ ማህበረሰቦች ኅብረት የማኅበረሰቦችን ልምድ በሁለቱም የአሜሪካ ንፍቀ ክበብ መካከል ለመለዋወጥ በሚል ዓላማ በላቲን አሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት (CELAM) የተቋቋመ ሲሆን፥ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2021 ዓ. ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚሽን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንችስኮስ ጋር በሮም በተሰበሰቡበት ወቅት እንደ ነበር ይታወሳል።

ከስብሰባው በኋላ በካሊፎርኒያ የሳን ሆሴ ጳጳስ አቡነ ካንቱ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባቀረቡት ሃሳብ የላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ ከሚገኘው የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን ጋር ግንኙነት መፍጠሩ ይታወሳል።

ከበርካታ ምናባዊ እና በአካል ከተደረጉ ስብሰባዎች በኋላ በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን እና አዲስ የተደራጁ ማኅበረሰቦች በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ መካከል በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መሪነት እና ድጋፍ ኅብረት መፈጠሩ ይታወሳል። በዚህ መሠረት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2022 ዓ. ም. ለኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን አባላት የቪዲዮ መልዕክት መላካቸው ሲታወስ፥ እንዲሁም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2022 እና 2023 ዓ. ም. ፋውዴሽኑ በሮም ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ሁለት ስብሰባዎችን ማድረጉ ይታወሳል።

የተደራጁ የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች መጀመሪያዎቹ ደረጃዎች
ከማኅበርሰቡ የተገለሉ ስደተኛ ሠራተኞችን ችግር በተመለከተ በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ ለገጠሙት ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠት የላቲን አሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሥር ከሚገኝ የፍትህ እና የሰላም መምሪያ ጋር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2023 ዓ. ም. የመጀመሪያውን ምናባዊ ስብሰባ አደርገዋል።

በመቀጠልም በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች የማኅበረሰቦች መሪዎች፥ “ፖለቲካ እና የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አስተምህሮ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የመጀመሪያውን ሴሚናር ከየካቲት 19-20/2024 ዓ. ም. በቴክሳስ ሳን አንቶኒዮ ሀገረ ስብከት ተካሂዶ እንደ ነበር ይታወሳል።ሁለተኛው ስብሰባ በቦይነስ አይረስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከነሐሴ 4-10/2024 ዓ. ም. ድረስ የምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ማኅበረሰቦች መሪዎች የተካሄደ ስብሰባ እንደ ነበር ይታወሳል።

ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ባደረገው አዲስ ስብሰባ፣ በምዕራባዊ ደቡብ አሜሪካ የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ፋውንዴሽን በላቲን አሜሪካ ጳጳሳዊ ኮሚሽን ውስጥ የሚገኙ ቢሮዎችን በመጋበዝ በከተማ ውስጥ ከተደራጁ ማኅበረሰቦች ጋር በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ግንኙነትን ለመፍጠር የሚያስችል ስብሰባ ማድርጉም ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአካል የተሳተፉበት እና በመላው አሜሪካ በሚገኙ ተማሪዎች መካከል የዩኒቨርሲቲ ግንኝነቶችን በመገንባት የተጀመረው ይህ ተነሳሽነት፣ በሁለቱም አህጉራት መካከል ያለውን ትስስር በማጎልበት በተደራጁ ማኅበረሰቦች መካከል ሁለተኛ ድልድይ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2025 ዓ. ም. ሁለት አዳዲስ ስብሰባዎች ሊካሄዱ የታቀደ ሲሆን፥ አንዱ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሌላው በአውሮፓ ውስጥ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የተደራጁ ማኅበረሰቦች ማን ናቸው?
የተደራጁ ማኅበረሰቦች የሚባሉት በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የተሰደዱ የከተማ ማኅበረሰብ ሠራተኞች ማኅበራት ሲሆኑ፥ እነዚህ ማኅበረሰቦች በሙሉ ከካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጋር በመሆን የቤተ ክርስቲያኗን ማኅበራዊ አስተምህሮ ለመመሥረት እና ለመተግበር መሪነትን የሚወስዱበት ሲሆን፥ ዓላማውም በወንጌል ላይ የተመሠረተ ጣዕም ያለው የሕይወት የአኗኗር ዘይቤን ለማረጋገጥ የቆመ እንደሆነ ታውቋል።

እነዚህ ማኅበረሰቦች በፖለቲካ ፓርቲነት፣ በኢኮኖሚ ዘርፍ ወይም በአካዳሚክ ርዕዮተ ዓለም ፕሮጄክቶች የሚመሩ ታዋቂ ድርጅቶች እንዳልሆኑ፣ ወይም መንግሥታዊ ካልሆኑ የግል ድርጅቶች የበጎ አድራጎት ድጎማዎችን ለመጠየቅ የተቋቋሙ ሳይሆን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ-ምዕዳናቸው ላይ እንደገለፁት “ከዝቅተኛ ደረጃ ተነስተው የተቋቋሙ የከተማ ማኅበረሰብ ድርጅቶች መሆናቸው ታውቋል።

የተደራጁ ማኅበረሰቦች የምንላቸው በቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ አስተምህሮ መሠረታዊ መርሆች ዙሪያ፥ በተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ከታወቁ ማኅበራዊ ዋስትናዎች ጋር እንደ ሥራ፣ ንፁህ ውሃ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የከተማ ውበት፣ ስፖርት፣ የሕዝብ ጤና እና የትምህርት ሁለንተናዊ ተደራሽነት፣ እንደ ቤተ-መጻሕፍት፣ የባህል ማዕከላት እና ክለቦች ያሉ ተቋማዊ የአንድነት መዋቅሮች፤ ከሀገር አቀፍ እና ከክልላዊ መንግሥታት ጋር በመሆን ተግባራቸውን እና ግዴታቸውን ለመወጣት እራሳቸውን የሚመሩ መዋቅሮች እንደሆኑ ታውቋል።

የድጋፍ መርህ ውጤታማ መግለጫ
በሌላ አነጋገር፥ የተደራጁ ማኅበረሰቦች የፖለቲካ እና የቤተ ክህነት ርዕሠ ጉዳይ የሆኑ የሕዝብ መሠረታዊ መርህ በመሆናቸው የካቶሊክ የበጎ አድራጎት መርህ ውጤታማ መግለጫዎች ሲሆን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ውድ አማዞን” ባሉት ሠነዳቸው እንደተናገሩት፥ ከማኅበራዊ አስተምህሮ የራቁ፥ ሕይወትን ከከፍታ ላይ ሆነው ለመመልከት ከተገነቡ የሕልም ተቋማት መርሆዎች የተለዩ ናቸው።

የከተማ ውስጥ የተደራጁ ማኅበረሰቦች የተመሠረቱት በጋራ ዕድገት አንድ ለመሆን በመወሰን ሲሆን፥ ከመንግሥት ጋር በቅርብ ለመወያየት እንዲያስችል ከብጹዓን ጳጳሶቻቸው፣ ከሕዝባዊ ፖሊሲ አውጪዎቻቸው እና ከፊስካል ፖሊሲዎቻቸው ጋር በመሆን ለሰዎች እና ለጋራ መኖሪያ ምድራችን እንክብካቤ የሚደራጁ ማኅበረሰቦች እንደሆኑ ታውቋል።

 

29 August 2024, 15:50