ፈልግ

የኮንጎ ሰማዕታት የኮንጎ ሰማዕታት  

ር.ሊ.ጳ. አዲስ ስመተ ብፁዕና ማዕረግ የተሰጣቸው ሰማዕታት የዕርቅና የሰላም ምሳሌ ይሁኑ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተገደሉትን አራት ሰማዕታት የሰላምና የዕርቅ ምሳሌ እንዲሆኑ የተማጸኑ ሲሆን ጦርነት በተነሳበት ቦታ ሁሉ የሰላም መንገዶች እንዲከፈቱ ቀጣይ ጸሎቶች እንዲደረጉ ቅዱስነታቸው ተማጽነዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአራት ቀሳውስት ሰማዕትነት "ለጌታ እና ለወንድሞች የተሰጠ የህይወት ዘውድ ታላቅ ስኬት ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእሁድ ቀን ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም በመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ማጠቃለያ ላይ ተናግረዋል።

የዛቬሪያን ሚስዮናውያን አባ ሉዊጂ ካራራ እና ወንድም ቪቶሪዮ ፋቺን ባራካ በመባል በሚታወቀው የኮንጎ ግዛት ውስጥ እ.አ.አ በህዳር 28 ቀን 1964 ዓ.ም በክዊሉ አመፅ ውስጥ በተሳተፉ ታጣቂዎች አማካይነት ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።  በዚያው ቀን አማፂያኑ ወደ ፊዚ ከተማ ተዛውረው የዛቬሪያን ሚስዮናዊያን ባልደረባ የሆኑትን አባ ጆቫኒ እና አባ አልበርት ጁበርት፣ የኮንጎ ተወላጅ ፈረንሳዊ ቄስ ጨምሮ ሁለቱንም ገደሏቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእሁድ እለት ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም የተደረገውን ስመተ ብጽዕና አጋጣሚ በመጠቀም አርአያነታቸው እና ምልጃቸው ለኮንጎ ህዝብ የሚጠቅም የእርቅ እና የሰላም መንገዶችን እንዲያጎለብት ጸልየዋል።

ጦርነት በሚካሄድበት ቦታ ሁሉ የሰላም መንገዶች ይከፈቱ

ቅዱስ አባታችንም ቀጣይ ጸሎቶችን ጠይቀዋል "በመካከለኛው ምስራቅ ፍልስጤም፣ እስራኤል ውስጥ የሰላም መንገዶች እንዲከፈቱ፥ እንዲሁም በተሰቃየችው ዩክሬን፣ በምያንማር እና በሁሉም የጦር ቀጠና ውስጥ" ሰላም ይሰፍን ዘንድ ተማጽነዋል።

ወደ ሰላም የሚወስዱት መንገዶች “ለውይይት እና ድርድር ቁርጠኝነት እና ከአመጽ ድርጊቶች እና ምላሾች በመታቀብ” እንዲታጀቡ ቅዱስነታቸው ጸሎት አቅርበዋል።

 

 

19 August 2024, 10:32