ፈልግ

በኮንጎ ጎማ ግዛት ውስጥ ለሰላም ጸሎት ሲደረግ የምያሳይ ምስል በኮንጎ ጎማ ግዛት ውስጥ ለሰላም ጸሎት ሲደረግ የምያሳይ ምስል   (ANSA)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በግጭት በሚሰቃዩ ሀገራት ውስጥ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በሱዳን፣ ዩክሬን፣ ምያንማር እና ቅድስት ሀገር ባሉ ግጭቶች እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙ አገራት የሰላም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስ አባታችን ጦርነትና በግጭት በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የሰላም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። እንዲሁም ለሚሰቃዩ ሕዝቦች መቀራረብ ይፈጠር ዘንድ ረቡዕ ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ነበር ይህንን ጥሪ ያስተጋቡት።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስፍራው ለተገኙት ምዕመናን ባደረጉት ንግግር በጦርነት የምትታመሰውን የዩክሬይንን ታላቅ መከራ በማስታወስ ምእመናን ሁሉ የተቸገረውን ሕዝብ እንዳይረሱ አሳስበዋል።

"ሰማዕት የሆነችውን ዩክሬንን እንዳንረሳ" በማለት አበክሮ የገለጹት ቅዱስነታቸው "ምያንማርን፣ ሱዳንን፣ ሰሜን ኪቩን እና በጦርነት ላይ ያሉ ብዙ አገሮችን አንርሳ" ሲሉ አሳስቧል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም በቅድስት ሀገር በጦርነት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጸልየዋል፣ "ለሰላም እንጸልይ" ሲሉም አክለዋል።

ቅዱስ አባታችን ለፖላንድ ምዕመናን ባቀረቡት ሰላምታ የሰላም ስጦታ እንዲሰጣቸው ጸልየዋል።

ክርስቲያኖች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው በሰላም እንዲኖሩ በማሳሰብ፣ “በጦርነትና መለያየት የምትታወቀው ዓለማችን ከምንጊዜውም በላይ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ያስፈልጋታል” ሲሉ በምሬት ተናግሯል።

"ከቤተሰቦቻችሁ እና ከስራ ቦታችሁ ጀምሮ ፍቅርን፣ ሰላምን እና መልካምነትን በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ አስፍኑ" ሲሉ አሳስቧል።

በአሁኑ ጊዜ በርካታ ፖላንዳውያን ወደ እመቤታችን ያስና ጎራ ቤተ መቅደስ የሚደርጉትን መንፈሳዊ ንግደት በማስታወስ፣ ምልጃዋ “ዓለም የሚሻውን የሰላም ስጦታ ያምጣ” በማለት ጸሎታቸውን ቅዱስ አባታችን ያቀረቡ ሲሆን ከምንጊዜውም በላይ ሰላም ስለሚያስፈልገን የሰላም ንግሥት ይሆነችውን እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልንማጸናት ይገባል ብለዋል።

እምነት ወደፊት እንዲራመድ ለካቴኪስቶች እንጸልይ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ መታሰቢያ የሚከበርበት ወቅት መሆኑን አስታውሰው፣ አንዳንዴም 'የካቴክስቶች ጳጳስ' እየተባሉ ይጠሩ እንደነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።  

ቅዱስ አባታችን ምእመናን "ዛሬ ለካቴኪስቶች እንዲጸልዩ" ሲጋብዟቸው "ብዙ ሥራ የሚሰሩትን ካቴኪስቶችን እናስባለን እና በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች እምነትን ወደፊት ለማራመድ የመጀመሪያዎቹ ናቸው" በማለት አመስግነዋል፣ "ጌታ ደፋር ያደርጋቸዋል" እና "ወደ ፊት እንዲራመዱ እንጸልይ" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

 

23 August 2024, 15:40