ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
የማታ ጸሎት በላቲን ቋንቋ
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በመዝናኛ ማዕከሉ የቀረበውን የሰርከስ ትርኢት ሲመለከቱ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በመዝናኛ ማዕከሉ የቀረበውን የሰርከስ ትርኢት ሲመለከቱ  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሰርከስ ትርኢት አዘጋጆች ለሕዝቡ ለሚሰጡት ደስታ ምስጋናቸውን አቀረቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በኦስቲያ ሊዶ (በደቡብ ምዕራብ ሮም) የሚገኘውን የሉና ፓርክ ጎብኝተዋል። ቅዱስነታቸው በመዝናኛ ፓርኩ ውስጥ የሚኖሩ የካርኒቫል እና የሰርከስ ትርኢቶች ረዳት አዘጋጆችን እህት ጄኔቪዬቭ እና እህት ሐና አሜሊያን ለሐዋርያዊ እንክብካቤያቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ከሮም በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኘውን ታሪካዊ የመዝናኛ ፓርክ ረቡዕ ሐምሌ 24/2016 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ጎብኝተው ከማዕከሉ ሠራተኞች እና ለማዕከሉ ሐዋርያዊ እንክብካቤ ከሚሰጡት ጋር ተገናኝተዋል። ቅዱስናታቸው ወደ ሥፍራው ሲደርሱ ለማዕከሉ ያላቸውን መልካም ምኞታቸውን እና ድጋፋቸውን ገልጸው፥ ወደ መዝናኛ ማዕከሉ ለሚመጡት በርካታ ሰዎች ለሚሰጡት ደስታ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

የእመቤታችን ቅዱስ ሐውልት ቡራኬ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ መዝናኛ ማዕከሉ ከደረሱ በኋላ በቅጥር ውስጥ "እመቤታችን ጠባቂያችን እንድትሆን እንፈልጋለን” የሚል ጽሑፍ በሚኝበት የእመቤታችን ቅዱስ ሐውልት ፊት ቆመው ጸሎታቸውን አድርሰዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሉና ፓርክን በመኪና ሲጎበኙት
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሉና ፓርክን በመኪና ሲጎበኙት

እህት ጄኔቪ መልካም አቀባበል
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአገርሩ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በዘጠኝ ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ላይ ወደ መዝናኛ ሥፍራው ሲደርሱ በኢየሱስ ታናናሽ እህቶች ማኅበር ከ56 ዓመታት በላይ የቆዩት ፈረንሳዊ እህት ጄኔቪዬ ጄኒንግሮስ አብረው ከሚያገለግሉት እህት ሐና አሚሊያ ጋር ለቅዱስነታቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የተዘጋጀ አጭር የመዝናኛ ትርኢት
ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የተዘጋጀ አጭር የመዝናኛ ትርኢት

የኢየሱስ ታናናሽ እህቶች ለምንኩስና ሕይወት ያነሳሳቸው ቅዱስ ቻርለስ ደ ፉካውልድ ሕይወት እና ምስክሮች ሲሆን የእርሱ ፍላጎትም ድሃ የሆኑ ወንድሞቹን እና እህቶቹን ማገልገል እንደነበር ይታወቃል”” እህት ጄኔቪዬ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የተገነኙ ሲሆን ለዓመታት ስትረዳቸው ከቆዩት የተለያዩ ቡድኖች ጋር የቅዱስነታቸውን የረቡዕ ጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከተከታተሉ በኋላ በማጠቃለያው ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ፍራንችስኮስ ጋር ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በሥፍራው ከነበሩት ሌሎች ከሰዎች ጋርም ተገናኝተዋል
እህት ጄኔቪዬቭ በአካባቢው ከሚገኝ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰላም ንግሥት ቁምስና መሪ ካህን ከሆኑት ከአባ ጆቫኒ ቪንቼንዞ ፓታኔ ጋር በመሆን ባደረጉት መስተንግዶ ላይ ባሰሙት ንግግር የቅዱስነታቸው ጉብኝት ታላቅ ደስታ እንዳጎናጸፋቸው ገልጸዋል።

ቀጥሎም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቦታው ለነበሩት የከረሜላ እና የመቁጠሪያ ስጦታ ካደሉ በኋላ ባሰሙት አጭር ንግግር፥ የማዕከሉ ሠራተኞች ወደ መዝናኛው ሥፍራ ለሚመጡት በርካታ ሰዎች ደስታ በመስጠት ለሚያደርጉት ዕርዳታ ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሥፍራው ከነበሩት ቢተሰቦች ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሥፍራው ከነበሩት ቢተሰቦች ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል
በሉና የመዝናኛ ፓርክ የሚገኝ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐውልት
በሉና የመዝናኛ ፓርክ የሚገኝ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐውልት
01 Aug 2024, 22:07
Prev
February 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728 
Next
March 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031