ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለወጣቶቹ የቪዲዮ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለወጣቶቹ የቪዲዮ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ወጣቶች በጉዞ ወቅት ሳይቆሙ በድፍረት እና በደስታ ወደ ፊት እንዲራመዱ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከመስከረም 22/2017 ዓ. ም. ጀምሮ በሲኖዶሳዊነት ላይ ሲካሄድ በቆየው የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ጉባኤውን ለተሳፉ ወጣቶች መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ለወጣቶቹ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፥ የክርስትና ሕይወታቸውን በድፍረት ወደፊት እንዲራመዱ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ በሲኖዶሳዊነት ላይ ከመስከረም 22/2017 ዓ. ም. ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶሱ 16ኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ሊገባደድ በተቃረበበት ወቅት በጉባኤው ሲሳተፉ ለቆዩ ወጣቶች የቪዲዮ መልዕክታቸውን ረቡዕ ጥቅምት 13/2017 ዓ. ም. ልከዋል።

ቅዱስነታቸው በቪዲዮ መልዕክታቸው ወጣቶችን ከወራጅ ውሃ ጋር በማወዳደር እንደተናገሩት፥ “የወንዝ ውሃ ሲፈስ እንጂ ሲቆም ወይም ሲረጋ መጥፎ ይሆናል” ብለዋል። “የረጋ ውኃ በትንንሽ ፍጥረታት እንደሚበከል ሁሉ የደከመው ወጣት በጉዞው መካከል ሊወድቅ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ታዲያ ይህን ለማስቀረት ወጣቶች ሳይቆሙ በድፍረት እና በደስታ ወደ ፊት መጓዝን መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሲኖዶስ ጉባኤን የተሳተፉ ወጣቶች
ከመስከረም 22/2017 ዓ. ም. ጀምሮ ሲካሄድ በሰነበተው 16ኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከብጹዓን ካርዲናሎች እስከ የነገረ-መለኮት ምሁራን፣ ፕሮፌሰሮች እና የኮሌጅ ተማሪዎች ድረስ ከተለያዩ የሕይወት ልምዶች የተወጣጡ እና ድምጽ መስጠት የሚችሉ ጠቅላላ የጉባኤው ተሳታፊዎች 368 ሲሆኑ

ከእነዚህ ውስጥ 272 ጳጳሳት፥ ሌሎች 96ቱ ደግሞ ጳጳሳት ያልሆኑ እና ጥቂት የማይባሉ ምዕመናን ጉባኤውን ተሳትፈዋል። ከምዕመናኑ መካከልም ሁለቱ በ20ዎቹ መጀመሪያ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

 

24 October 2024, 17:11