ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ ወደ ተራ የጊዜ ቅደም ተከተል እውነታዎች ሊቀንስ አይችልም
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐሙስ ኅዳር 12/2017 ዓ.ም ይፋ ባደረጉት መልእክት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጥናት በጥልቀት መታደስ እንዳለበት አሳስበዋል። ሴሚናሮች (የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች)፣ ቀሳውስት እና ምእመናን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስጥ የሚጫወተውን ታሪክ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።
ታሪክ እንደ የጋራ ትውስታ
በመልእክቱ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የታሪክን ጥቅም እንደ የጋራ ውርስ በማንፀባረቅ የቤተ ክርስቲያን ጥናት ቀኖችን እና ክስተቶችን ከማስታወስ ባለፈ ታሪክን በሚገባ የሚገልጽ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
እሱም “የጋራ ሕሊና ነበልባል በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ነው” ሲሉ የገለጹት ቅዱስነታቸ፣ ይህን በማድረግ፣ ምእመናን አሁን ያለውን ጊዜ በጠራ የአመለካከት ስሜት፣ በቤተክርስቲያኗ ለብዙ መቶ ዘመናት ባሳለፈችው የህይወት ልምድ ማሰስ ይችላሉ ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ስለ "Deconstructionism" (እምነትን ማፍረስ፣ እምነትን ማደስ፣ ሀይማኖታዊ መበስበስ ወይም በቀላሉ ማፍረስ በመባልም ይታወቃል፣ አማኞች እምነታቸውን እንደገና የሚመረምሩበት እና እምነታቸውን የሚጠራጠሩበት ሂደት ነው) ተናግረዋል፣ እሱም በዛሬው ባህል እያደገ የመጣ አዝማሚያ ነው ብለዋል።
ዲኮንስትራክሽን (ዲኮንስትራክሽን) ጥሎልን ልያልፍ የሚችለው አንድ ነገር፣ “ወሰን የለሽ ፍጆታን እና ባዶ ግለሰባዊነትን መግለጽ ነው” ሲሉ ጽፏል።
እነዚህ ዝንባሌዎች፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት ከሆነ፣ ብዙውን ጊዜ “ኃይላችንን በሌለበት ዓለም ላይ እንድናባክን የሚገፋፋን የዓይነ ስውርነት ዓይነት፣ የውሸት ችግሮችን የሚያነሳና በቂ መፍትሔ ወደሌለው የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያዞር” ይመስላል ሲሉ ገልጸዋል።
ቤተክርስቲያን በሁሉም ጉድለቶቿ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ቤተክርስቲያኗን ከሰብአዊነት እስከ ከሥር መሰረቷ እየተቋረጠች መታለች ብሎ ማሰብ አደገኛ እንደ ሆነ አስጠንቅቀዋል።
ለቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ፍቅር፣ ጳጳሱ አጥብቀው የገለጹት፣ በእውነተኛነቷ ላይ የተመሰረተ እንጂ የታሰበ ፍጹምነት አይደለም ያሉ ሲሆን ከውድቀቷ የመማር ጥንካሬን በማጉላት ቤተክርስቲያንን በእውነት እንዳለች የመውደድን አስፈላጊነት አሳስበዋል።
"በጣም ጨለማ ጊዜዋ ውስጥ እንኳን ጥልቅ ማንነቷን የምታውቅ ቤተክርስቲያን የምትኖርበትን ፍጽምና የጎደለውን እና የቆሰለውን አለም መረዳት ትችላለች" ብሏል። "ፈውስንና መታደስን ለዓለም ለማምጣት በምታደርገው ጥረት፣ አንዳንድ ጊዜ ባይሳካላትም እራሷን ለመፈወስ እና ለማደስ የምትጥርበትን መንገድ ትጠቀማለች" ሲሉ ጽፈዋል።
ትውስታ እና እርቅ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ታሪክን የመጠበቅን አስፈላጊነት ሲናገሩ "ባህልን ሰርዙ" እና አሁን ያለውን አስተሳሰቦች ለማጽደቅ ያለፈውን የሚያዛባ ታሪካዊ ትረካዎች ማስወገድ የገባል ከሚለው አስተሳሰብ መነጠል እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል።
ይልቁንም፣ ቀጥለው፣ ሁለቱንም የሰው ልጅ ጨለማ ምዕራፎች እና ልዩ የጸጋ ጊዜዎችን በመገንዘብ ከታሪክ ጋር ሚዛናዊ ግንኙነት ያስፈልገናል ያሉት ቅዱስነታቸው ትውስታ "የእድገት እንቅፋት ሳይሆን የፍትህ እና የወንድማማችነት መሰረት ነው" ሲል አሳስቧል።
የታሪክ ጥናቶች ተሃድሶ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው መገባደጃ አካባቢ የቤተክርስቲያኒቱን ታሪክ ለማጥናት ብዙ ጉዳዮችን አንስተዋል።
የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ወደ የጊዜ ቅደም ተከተላቸው እውነታዎች የሚቀንሱ አቀራረቦችን ተችተዋል፣ እና ጥልቅ ስሜት የተሞላበት የታሪክ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ሴሚናሪስቶች (የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች) በጥንቶቹ ክርስቲያናዊ ጽሑፎች ላይ በጥልቀት እንዲሳተፉ በማሳሰብ በዋና ምንጮች ላይ የበለጠ ትኩረት እንዲደረግ ጠይቋል።
“የሚያስፈልገው የግል እና የጋራ ጥረት፣ ለወንጌል ቁርጠኝነት ለሚተጉ እና ገለልተኛ ወይም የመከነ አቋም ያልመረጡትን ማገዝ ነው” ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለተገለሉ ወገኖች ድምጽ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሰማዕትነት
በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ስላለው የሰማዕትነት ማዕከላዊነት በማሰላሰል፣ ቤተክርስቲያን በስደት እና በመከራ ጊዜያት ታላቅ ውበቷን እንዳገኘች ለምእመናን በማሳሰብ ለክርስቶስ የሰጠችው ምስክርነት በደመቀ ሁኔታ ደምቆ ታይቶ ነበር ብለዋል።
"ቤተክርስቲያኗ ራሷም እንደተጠቀመች እና አሁንም በጠላቶቿ እና በአሳዳጆችዋ ተቃውሞ እየተጠቀመች እንደሆነ ትገነዘባለች" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስረድተዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጻፏቸውን መልእክቶች በማጠቃለል ታሪክን የማጥናት አስፈላጊነትን በማጉላት ምእመናንን "ጥናት ሐሜት አይደለም" ሲሉ አሳስበዋል።
እውነተኛ ጥናት ጥልቅ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና የባህል ሸማቾችን ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችን ለመቋቋም ድፍረትን ይጠይቃል ሲል ተናግሯል።