ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከቅድስት መንበር  የባሕልና ትምህርት ጽ/ቤት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከቅድስት መንበር የባሕልና ትምህርት ጽ/ቤት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የትምህርት ውድቀት ልጆችን የወደፊት ሕይወታቸውን የሚያሳጣ የባህል ዘር ማጥፋት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመጀመሪያ ጊዜ የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ያካሄደውን የቅድስት መንበር የባሕልና ትምህርት ጽ/ቤት አባላት እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ የትህምርት ገበታ ላይ የማይገኙና ትምህርት የማይከታተሉ 250 ሚሊዮን ሕፃናት የመርዳት “የሞራል ግዴታ አለባችው” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቫቲካን ከሚገኙት አዲስ የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ጽ/ቤት አንዱ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የመጀመሪያውን ምልአተ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ተገናኝተው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የካቶሊክ ትምህርት ጉባኤ እና የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤትን ካዋሃዱ በኋላ የባህል እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት እ.አ.አ በሰኔ ወር 2022 ዓ.ም ተመሠረተ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እርምጃው “የውይይት፣ መስተጋብር እና ፈጠራ ያለውን አቅም የሁለቱንም ውጤታማነት በሚያሳድግ መልኩ ለመጠቀም ነው” ብለዋል።

የጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቱ ተልእኮ አስፈላጊነትን በመድገም በግንኙነቱ ወቅት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በቀላሉ ውጤት የሚያስገኙ ትምህርታዊ ሞዴሎችን በዘፈቀደ ከመፍጠር እንዲጠበቁ አስጠንቅቋል።

"ዓለማችን ልፋት እና ድካምን ማቃለያ (አውቶሜሽን) አትፈልግም" ሲሉ የገጹት ቅዱስነታቸው "አዲስ የኮሪዮግራፈር ባለሙያዎች (የእርምጃዎችን ቅደም ተከተል የምያቀናብር እና ለተግባራዊነቱ ወይም ለአፈፃፀም የሚንቀሳቀስ ሰው፡-) ፣ ከቱባው ሰብዓዊ አቅም ወስዶ አዲስ ትርጓሜዎችን የምያቀርብ ሰው፣ አዲስ ማህበራዊ ገጣሚዎች ያስፈልጉታል" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

በእርግጥ "ምን እየጠበቅን ነው"?

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስኬትን ወይም ማስተዋወቅን የመጨረሻ ግብ ከማድረግ ይልቅ የቅድስት መንበር የትምህርት እና የባህል ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽፍት ቤት አባላትን “በጣም የተለየ ነገር እንዲያደርጉ” መክረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የትምህርት እና የባህል ተልዕኳቸውን እንዲመለከቱ "ሌሎች አእምሮአቸውን እንዲያሰፉ፣ በውስጣዊ ጥንካሬ እንዲሞሉ፣ ለአዳዲስ አማራጮች ቦታ እንዲሰጡ እና የተቀበሉትን ስጦታዎች እንዲያካፍሉ መጥራታቸው ነው” በማለት ተናግሯል።

የምንፈራበት ምክንያት የለም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቡድኑ እንዳይፈራ አበረታተዋል። ክርስቶስን እንደ መሪያቸው እና አጋራቸው አድርገው እንዲቆጥሩ ያሳሰቡ ሲሆን “የባህላዊ እና ትምህርታዊ ቅርስ ጠባቂዎች” ናችሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ፍልስፍናዊ፣ ሥነ-መለኮታዊ፣ ግጥማዊ እና ሳይንሳዊ ዳራ ከነሱ በፊት እንደ ቅዱስ አውግስጢኖስ እና ሞዛርት ከቀደሙት ታዋቂ ሰዎች ሥራ እና ጥናት ወደ ማርክ ሮትኮ እና ብሌዝ ፓስካል መጡ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጽሕፈት ቤቱ አባላት ይህን ልመና ለሁሉም ሰው እንዲያሰራጩ ኃላፊነት ሰጥተዋል፡- “ስለ ተስፋ መናገር አትርሱ!” ሲሉ አክለው ተናግረዋል፣ ከቃላት በላይ ግን እጃቸውን አስተባረው መሥራት እንዲጀምሩ አበረታቷቸዋል።

የባህል የዘር ማጥፋት እና ትምህርት

"በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን በታሪክ ከፍተኛው የተማሪዎች ቁጥር አላት" ሲሉ ጠቁሟል። ያም ሆኖ ወደ 250 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናትና ታዳጊዎች ትምህርት መከታተል አልቻሉም ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህን ኢፍትሐዊ ድርጊት አውግዘዋል።

"ልጆች ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ እንዲሆኑ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ባለማዘጋጀታችን የወደፊት ሕይወታቸውን ስንዘርፍ የባህል ዘር ማጥፋት ነው" ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ጥቅሞቻቸውን እና አደጋዎችን” እንዲገነዘቡ የቅድስት መንበር የትምህርት እና የባሕል ጽሕፈት ቤት አባላትን ያበረታቱ ሲሆን የቅርብ ጊዜ የሳይንስ እድገቶችን እና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በድጋሚ እንዲያጠኑ በመምከር ንግግራቸውን ደምድመዋል።

21 November 2024, 15:44