ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የሴቶች ድምፅ 'የጋራ ጥቅምን' ለማስከበር የሚያበረክተው ብዙ ነገር አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድስት መንበር የሕይወት ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ለተሳተፉ ተሳታፊዎች መልእክት የጋራ ጥቅምን በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን "የቤተክርስቲያኗ ማኅበራዊ አስተምህሮዎች አንዱ የሆነውን የጋራ ጥቅም ማስታወስ ትልቅ ጠቀሜታ አለው" ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጳጳሳዊ የሕይወት አካዳሚ አዘጋጅነት እና በቫቲካን እ.አ.አ ከኅዳር 14 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ - “በጋራ ጥቅም ላይ የሚደረግ ውይይት፡ ንድፈ ሐሳብ እና አሠራር” በሚል አርዕስት በላኩት መልእክት በዚህ ሐሳብ ላይ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ ውይይት በመጀመሪያ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መልእክት በማንበብ የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ሊቀ ጳጳስ ቪንቼንዞ ፓግሊያ የተካሄደ ሲሆን በመቀጠልም በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የኢኖቬሽን እና ሕዝባዊ እሴት በሚል አርዕስት የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ማሪያና ማዙዙካቶ ንግግር አድርገዋል።

ውይይቱ ከጤና፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከብዝሃ ህይወት፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከውሃ እንዲሁም ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የወደፊት እጣ ፈንታ ጋር ተያይዞ ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮቻችን በአስቸኳይ በሚገባ የተነደፈ እርምጃ ለመፍጠር እንዴት እንደሚያግዝ ውይይቱ እንደሚረዳም ተገልጿል።

የጋራ ጥቅምን ማስተዋወቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ለተሰብሳቢዎቹን ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበዋል፣ በጋራ ጥቅም መሪ ሃሳብ ላይ ባለው ሰፊ አስተያየት ውስጥ ይህ ስብሰባ በተለይ ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነ ጠቁመዋል ።

የመጀመሪያው በጳጳሳዊ የሕይወት አካዳሚ ያስተዋወቀው ነው ብሏል።

"በእያንዳንዱ አውድ እና ሁኔታ የሰውን ልጅ ህይወት ለመጠበቅ በእውነት ከፈለግን የህይወት መሪ ሃሳቦችን፣ የስነ-ሕይወት ስነ-ምግባር ክርክሮች ውስጥ እንኳን እነዚህ ክስተቶች በሚከሰቱባቸው ማህበራዊ እና ባህላዊ አውዶች ውስጥ ማስቀመጥን ችላ ልንል አንችልም" የሚለው ነው።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በተወሰኑ ገጽታዎች ወይም አፍታዎች ብቻ የተገደበ የሕይወት ጥበቃ እና ሁሉንም ነባራዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ገጽታዎች ከግምት ውስጥ ያላስገባ ጥበቃ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፥ "ከእውነተኛ ሰዎች ይልቅ ረቂቅ መርሆዎች የሚጠበቁበት" ይህንን መከላከል ይገባናል ብለዋል።

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ጥቅምን እና ፍትህን ማሳደድ "የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ጥበቃ ማዕከላዊ እና አስፈላጊ ገጽታዎች ናቸው" ብለዋል፣ በተለይም "እጅግ በጣም ደካማ እና ጥበቃ የሌላቸው ከምንኖርበት አጠቃላይ ስነ-ምህዳር አንጻር ጥንቃቄ ሊደረግላቸው የሚገባ ብዙ የማሕበረሰብ ክፍሎች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

የህብረተሰብ ፍላጎቶች

ለማጉላት የፈለኩት ሁለተኛው ነጥብ በዝግጅቱ ላይ የተለያየ ኃላፊነትና ልምድ ያላቸው ሁለት ሴቶች እንደሚገኙበት ነው በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በማኅበረሰቡም ሆነ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሴቶችን ድምጽ ማዳመጥ አለብን" ሲሉ ተማጽነዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል “ስለ ሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሰፊ እና ጥበባዊ ነጸብራቅ ለማዳበር የተለያዩ የእውቀት ዓይነቶች በማፍለቅ ልንተባበር እንፈልጋለን" ብለዋል።

እናም "የዓለም ባህሎች ፍላጎቶቻቸውን እና ሀብቶቻቸውን እንዲያበረክቱ የሚያስችላቸው እውነተኛ አስተዋጾ እንፈልጋለን" ብሏል።

በዚህ መንገድ ብቻ ነው “ክፍት ዓለምን ማሰብ እና ማፍለቅ የምንችለው፣” በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በጣሊያነኛ ቋንቋ "ፍራቴሊ ቱቲ" (ሁላችንም ወድማማቾች ነን) በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት በምዕራፍ 3 ላይ ስለ ሰው ልጆች ወንድማማችነት የሚገልጹ ማበረቻቻዎችን አቅርበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን ጳጳሳዊ መልእክት በመጥቀስ ዓለም አቀፋዊ ወንድማማችነት በተወሰነ መልኩ “የግል፣ የጋራ ጥቅምን የመረዳት ሞቅ ያለ መንገድ ነው” በማለት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን ታሪኮች እና ሰዎች የሚገናኙበት ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የቤተክርስቲያን የማህበራዊ ትምህርት የማዕዘን ድንጋይ

በተጨማሪም፣ የጋራ ጥቅሙ፣ “ከሁሉም በላይ”፣ “በወንድማማችነት ተቀባይነትንና እውነትንና ፍትሕን በጋራ የመሻት ተግባር” መሆኑን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመልእክታቸው ገልጸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ዓለማችን በብዙ ግጭቶችና መከፋፈሎች በተዘበራረቀበት በአሁኑ ወቅት፣ ከግለሰባዊ ጥቅም ባለፈ የቤተክርስቲያንን ማህበራዊ ትምህር ትመመልከት ባለመቻላቸው ምክንያት ነው” ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።

በተጨማሪም “ይህን ጭብጥ በፖለቲካዊ ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ ውጤታማ መመሪያ ይሆን ዘንድ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ውስጥ የሚያቅፉ እና የሚያዳብሩ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ንድፈ ሐሳቦች ያስፈልጉናል” እና “ብዙውን ጊዜ በቃላት የሚጠራ ምድብ ብቻ ነው፣ በተግባር ግን ችላ ይባላል ሲሉ ወቅሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን በመስጠት እና እንዲጸልዩላቸው ከጋበዙ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

15 November 2024, 14:59