ፈልግ

የብጹዕ አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላ ምስል የብጹዕ አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላ ምስል  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የብጹዕ አባ ቶሬስ ፈለግ ካህናትን በአገልግሎታቸው እንደሚደግፋቸው ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ኅዳር 1/2017 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን ጋር በመሆን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ባቀረቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ በስፔን ሲቪሌ ከተማ በተከናወነው መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ በካርዲናል ማርቼሎ ሰመራሮ ብጽዕናቸው የታወጀላቸውን የቅዱስ መስቀል ድጋፍ የገዳማውያት ማኅበር ተባባሪ መሥራች አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላን ለምሳሌነታቸው አወድሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን የስፔን ካኅን የነበሩትን አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላን ያስታወሰው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ አባ ሆሴ ቶሬስ ለተቸገሩት ሰዎች ታላቅ የበጎ አድራጎት ሥራን በመሥራት እንደ ካኅን እና መንፈሳዊ መሪ ለምስክርነት መብቃቱን አስታውሰዋል። በቅድስት መንበር የቅድስና ጉዳዮች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሃላፊ ካርዲናል ማርቼሎ ሰመራሮ በስፔን ሲቪሌ ከተማ ቅዳሜ ጥቅምት 30/2017 ዓ. ም. በተዘጋጀው መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው የአባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላ ብጽዕናን ይፋ አድርገዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቱን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር፥ የአባ ቶሬስ ፓዲላ ፈለግ ካህናትን በአገልግሎታቸው እንዲደግፋቸው በማለት ጸሎታቸውን አቅርበዋል። ብፁዕ ካርዲናል ማርቼሎ ሰመራሮ በሴቪል ካቴድራል በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፥ አባ ሆሴ ቶረስ ፓዲላ በታላቅ ለጋስነቱ ያቀረበውን ነፃ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በማስታወስ፥ በከተማው አስቸጋሪ እና ጥቂቶች እንኳ ለመግባት በማይደፍሩባቸው ሠፈሮች ውስጥ ችግረኞችን በመቅረብ ቀዳሚ የውስጣዊ ጥንካሬው ምንጭ የሆነውን ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ጠንካራ አንድነት በተጨባጭ ማሳየቱን አስታውሰዋል።

መጽሐፍት ቅዱሳዊ የሕይወት ምስክርነት
በቅድስት መንበር የቅድስና ጉዳዮች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሃላፊ ካርዲናል ማርቼሎ ሰመራሮ፥ በመስዋዕተ ቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት ላይ በተነበበው ምንባብ እና በስፔናዊው ካኅን አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላ መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ሲገልጹ፥ ከቤተ መቅደሱ ደጃፍ በታች የውሃ ጅረት መፈሰሱን በማስታወስ የዚህ ምስል ድርብ ትርጉም ሲያብራሩ፥ “ጥምቀት የተጠሙትን ሁሉ የሚያረካ እና የሚያድስ ውሃ ነው” ብለው፥ ይህ ትንቢታዊ ራእይ በቤተ መቅደሱ ቀኝ በኩል ስለሚፈስ ውኃ እንደሚናገር ገልጸው፥ ይህም ከተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ደም እና ውኃ የፈሰሰበትን ቦታ የሚያመለክት መሆኑን አስረድተዋል።

በድርጊት ላይ ማሰላሰል
እንዲህ ዓይነቱ ምስል ወራጅ ውሃ ሕይወትን የሚያመጣ፣ የሚያድስ እና ብዙ ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርግ መሆኑን ከብፁዕ አባ ሆሴ ቶሬስ ፓዲላ ሕይወት ጋር ማመሳሰል እፈልጋለሁ ያሉት ካርዲናል ማርቼሎ ሰመራሮ፥ “አባ ሆሴ ቶሬስ ዘወትር ታማኝ ካኅን ናቸው” ብለው፥ ራስን ሌሎች ለመስጠት የተዘጋጀ፣ በበጎ አድራጎት ሌሎችን ለመርዳት የተዘጋጀ፣ ሕይወቱን እና ድርጊቱን ያመሳሰል ካህን እንደ ነበር አስታውሰዋል።

ትምህርት፣ አስተንትኖ እና ተጨባጭ አገልግሎት

ካርዲናል ሰመራሮ በመቀጠልም፥ የብፁዕ አባ ሆሴ ቶሬስ ልዩ ስብዕና ሲገልጹ፥ ጸሎትን እና ትምህርትን አንድ ላይ በማጣመር ችሎታው ሁለት ሰዓት በጥናት ሦስት ሰዓት ደግሞ ባጠናው ነገር ላይ በማሰላሰል እንደሚያሳልፍ፥ ሆኖም ግን በዘመኑ እጅግ የተቸገሩትን ከማገልገል እንዳላገደው አስረድተዋል።

የሴቪሌ ከተማ የተሳሳተ ጎን

“የአባ ሆሴ ቶሬስ ሕይወት የድህነት ሕይወት ነበር” ያሉት ካርዲናል ሰመራሮ፥ የተቀደዱ ልብሶችን ለብሶ ችግረኞችን እና የታመሙ ሰዎችን ይቀርብ እንደ ነበር አስታውሰው፥ ብዙውን ጊዜ በተሳሳተ ጎኑ የሚታወቀውን እና ሴቪሌ ከተማን ለሁለት የሚከፍለው የጓቪር ወንዝ ወንጀል የተስፋፋበት እንደ ነበር አስታውሰዋል። ሆኖም አባ ሆሴ ቶሬስ ምንም ሳይፈራ ወደዚያ ሄዶ ድሆችን እና ችግረኞችን ያገለግል እንደ ነበር አስታውሰዋል።

የብፁዕ አባ ቶሬስ ምሳሌነት
ብፁዕ አባ ቶሬስ ፓዲላን ይህን ለመሰለ ሕይወት ያበቃቸውን መንፈሳዊ መመሪያቸውን ያስታወሱት ካርዲናል ሰመራሮ፥ “ኤል ሳንቴሮ” የሚል ቅጽል ስም እንዲሰጣቸው ከማድረጉ በላይ በእርሱ መሪነት የመስቀል እህቶች ተቋምን የመሠረተች ቅድስት አንጀላን እንደሚያጠቃልል አስረድተዋል።

ቅድስና ሰዎችን እንዴት እርስ በርስ እንደሚበረታታ
“ቅድስና ሰዎችን እርስ በርሳቸው ያበረታታቸዋል” በማለት ንግግራቸውን ያጠቃለሉት ካርዲናል ሰመራሮ፥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ንግግር በማረጋገጥ እንደተናገሩት፥ መለኮታዊ አንድነት በክርስቲያኖች መካከል ያለው ትስስር እና ፍቅር እንዲያንፀባርቅ የሚያደርግ፣ ራስ ወዳድነትን፣ ጭፍን ጥላቻንን ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍፍሎች በማስወገድ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የመሆኑ ተሞክሮ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

 


 

11 November 2024, 15:17