ፈልግ

 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በምያንማር ያለው ሁከት እንዲቆም እና ለሰላም ልባዊ ውይይት እንዲደረግ ጸለዩ! ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በምያንማር ያለው ሁከት እንዲቆም እና ለሰላም ልባዊ ውይይት እንዲደረግ ጸለዩ!  (AFP or licensors)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በምያንማር ያለው ሁከት እንዲቆም እና ለሰላም ልባዊ ውይይት እንዲደረግ ጸለዩ!

በእሁዱ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ሥርዓተ አምልኮ ላይ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ አድርገው ካበቁ እና የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በጦርነት ለሚማቅቁ አገሮች ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተለይም በማያንማር (በርማ) ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ስቃይ በማስታወስ “በተለይም ለችግር የተጋለጡት ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ ታማሚዎች፣ ሮሂንጋዎችን ጨምሮ ስደተኞች” ጸሎት እንዲደረግ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል። ሁሉም ሰው ዩክሬንን፣ ፍልስጤምን፣ እስራኤልን፣ ሊባኖስን እና ሱዳንን እንዲያስታውስ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእሁድ እለት ባስተላለፉት መልእክት ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰላምን ለማስፈን ውይይት እና ሁሉን አቀፍ መሆን እንዴት አስፈላጊ እርምጃዎች እንደሆኑ አስታውሰዋል። በግጭት መዘዝ የሚሰቃዩትን ለማሰብ በድጋሚ በአደባባይ የተሰበሰቡትን ምእመናን ጋብዟል። እ.አ.አ በህዳር 25 ቀን 1920 ዓ.ም የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የስራ ማቆም አድማ የሚከበርባትን ሀገር ምያንማርን የሚበጣጥስ መሆኑን ጠቅሷል።

"በነገው እለት ምያንማር ሀገሪቱን የነጻነት ጎዳና ላይ ያቆመውን የመጀመርያውን የተማሪዎች ተቃውሞ ለማሰብ እና ዛሬም ለውጤት እንዲበቃ የሚታገለውን ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ጊዜ ለማሰብ ብሄራዊ በአል ታከብራለች። ለመላው ምያንማር ህዝብ ሀዘኔን እገልፃለሁ በተለይም በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ለሚሰቃዩት በተለይም በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ህጻናት፣ አዛውንቶች፣ በሽተኞች፣ ስደተኞች፣ ሮሂንጋዎችን ጨምሮ። ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ የሚችል ቅን እና ሁሉንም ያካተተ ውይይት እንዲጀምሩ ልባዊ ጥሪ አቀርባለሁ" ሲሉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዩክሬን፣ ፍልስጤም፣ እስራኤል፣ ሊባኖስና ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ሰው በትጋት መጸለይን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

25 November 2024, 10:49