የማርቼዲስ ቤንዝ ካፓኒ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ስጦታ ሰጠ!

እ.ኤ.አ. በ 2025 ዓ.ም የሚከበረውን የኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማርቼዲስ ቤንዝ ካፓኒ በስጦታ መልክ ያቀረበው መኪና ከዚህ ቀደም ያለተመረተ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ፣ የአረንጓዴ አሻራን የምያንጸባርቅ የኤልክትሪክ መኪና ሲሆን በተለይ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ፍላጎቶች የተዘጋጀ መኪና መሆኑም በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

አሁን በቫቲካን አዲስ የጳጳስ መኪና (ፖፓ ሞቢሌ) አለ። በታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም  የመርቼዲስ ቤንዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኦላ ካሌኒየስ እና ሌሎች የቡድን አባላት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓይነቱ አዲስ  የኤሌክትሪክ መኪና በእንግሊዜኛው G-Class ደረጃ ያለው ስጦታ ሰጡ።

አቶ ካሌኒየስ ይህንን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን መኪና በስጦታ ለቅዱስነታቸው ባቀረቡበት ወቅት ይህ ልምምድ  “ለእኛ ታላቅ ክብር ነው፣ ለሁሉም የቅዱስ አባታችን ፍላጎቶች ትኩረት የሰጠ ነው” ሲሉ ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚካሄደው በሚቀጥለው የጳጳሱ ዝግጅት ላይ በዚህ የጳጳስ መኪና ወይም ፖፓ ሞቢሌ በመባል በሚታወቀው መኪና በተለይም በኢዮቤልዩ አመት ለእርሳቸው በተዘጋጀው በዚህ የጳጳስ መኪና በመጠቀም እንደ ሚንቀሳቀሱ ተገልጿል።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጥያቄ መሰረት ተሽከርካሪውን ያመረቱት የካፓኒው የሰራተኞች ቡድን በሙሉ በስጦታው ርክክቡ ወቅት በስፍራው ተገኝተዋል።

የመቶ አመት ልምድ

ለ100 ዓመታት ያህል ማርቼዲስ ከቫቲካን ጋር ‘የጳጳስ መኪና’ ፓፓ ሞቢሌ እየተባለ የሚጠራውን በማቅረብ ሠርቷል። የመጀመሪያው መኪና እ.አ.አ በ1930 ዓ.ም ለጳጳስ ፒየስ 11ኛ የተሰጠው የመጀምሪያው የማርቼዲ ቤንዝ መኪና ነበር። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአሁኑ ፖፓ ሞቢሌ (የጳጳስ መኪና) ተብሎ የሚጠራው እርሳቸው ዘወትር ረብዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሲመጡ ይጠቀሙበት የነበረው የቀድሞ መኪና በእንግሊዘኛው G-Class በመባል የሚታወቅ በቤንዚን የሚሰራ የማርቼዲስ መኪና ነበር።

ለአረንጓዴው ጳጳስ አረንጓዴ መኪና

ከተለያዩ የማርቼዲስ ካፓኒዎች የተወጣጡ ልዕቅ የባለሙያዎች ቡድን ከቫቲካን ተወካዮች ጋር ለአንድ አመት ያህል ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍላጎት የተዘጋጀ መኪና ለመሥራት አበክረው ሰርተዋል።

እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ቫቲካን ሁሉንም ተሽከርካሪዎቿን ከልቀት ነፃ የሆኑ የኤሌክትርክ መኪናዎችን ለመጠቀም ስላቀደች ከማርቼዲስ ካፓኒ ጋር የምትጋራው ግብ ከዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ ዜሮ ልቀት ነበር።

የማርቼዲስ ቤንዝ ዋና ስራ አስፈፃሚው "ወደ ዜሮ ልቀት እየተጓዝን ነው፣ እናም ብዙ የኤሌክትሪክ ምርቶችን እያስጀመርን ነው" ብለዋል። "በዚህ አመት የኤሌክትሪክ ጂ-ሞዴል መኮኖችን መስራት አስጀመርን" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

ይህ መኪና በተለይ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በልዩ መልክ የተሠራ ልዩ መኪና ነው። የጂ-ሞዴል መኪኖች በሚመረቱበት በግራዝ ፋብሪካ ውስጥ በልማት ክፍል ውስጥ የሚሠሩት አቶ ፒተር ዞተር "ከመጀመሪያው ተሽከርካሪ ጋር ሲነፃፀሩ ከመሠረቱ አንፃር ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፣ ስለዚህ መነሻው የተለየ ነበር" ሲሉ ገልጿል።

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ መኪና

አዲሱ የኤሌክትሪክ መኪና የሚሽከረከር መቀመጫ እና በእጅ ባለሙያዎች የተሰሩ የመኪናው ክፍልን ያካትታል።በተጨማሪም መኪናው ሪዶታ (በአስቸጋሪ መንገዶች ላይ የመኪናን ጉልበት ለመጨመር የሚረዳ ኃይል) ያለው ሲሆን በተለይ ለዝቅተኛ ፍጥነት የተነደፈ፣ የጳጳሱ መኪና ብዙ ጊዜ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ጥቅም ላይ የሚውል እንዲሆን ተደርጎ የተመረተ ነው።

አቶ ዞተር ተሽከርካሪውን “ሁሉም ገፅታዎች ያሉት ልዩ ሥራ” በማለት ገልፀውና “ለጉዞው የሚያስፈልጋቸውን ምቾት ለቅዱስ አባታችን እንደሚሰጥ” ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። የጳጳሱ አዲስ እና የተሻሻለው መኪናም እሳቸውን ከከባቢ አየር ለመከላከል ሊከፈት እና ሊዘጋ የሚችል ጣሪያ አለው። የቀኝ ጎን የኋላ በር በሚሽከረከሩ ማጠፊያዎች ላይ የተገነባ ነው።

ሆኖም እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም የፖፓ ሞቢሌ መኪና ዘመናዊ ገጽታዎች ያሉት ቢሆንም አሁንም ቢሆን ይህ መኪና ባህላዊ የሆኑ ገጽታዎችን እንዲላበስ ተደርጎ የተሰራ ነው። ከቀደምቶቹ ጋር ተመሳሳይ፣ መኪናው ነጭ እና ታርጋው SCV 1 (የቫቲካን ከተማ ግዛት) የተለጠፈበት ነው።

 

05 December 2024, 15:41