ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በገና በዓል ሰሞን 'በሁሉም የጦር ግንባሮች' የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አደረጉ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ እለት ኅዳር 29/2017 ዓ.ም እንደ ተናገሩት ከገና በፊት ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርስ በቀጥታ ለፖለቲካ መሪዎች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተማጽነዋል።
"ቢያንስ ቢያን በገና በዓል አከባበር ወቅት በሁሉም የጦር ግንባሮች ላይ የተኩስ አቁም እንዲደርስ መንግስታትን እና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ እማፀናለሁ" ሲሉ በብስራተ ገብርኤል ፀሎት ወቅት ተናግሯል።
"በገና በዓል አከባበር ወቅት በሁሉም የጦር ግንባሮች ላይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርስ መንግስታትን እና አለም አቀፉን ማህበረሰብን እጠይቃለሁ" ብለዋል።
ቅዱስነታቸው የተናገሩት ቃል ሁሉም በጎ ፈቃድ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች በጦርነት በሚታመሱት ሀገራት ዓለም አቀፍ ሰላም እንዲሰፍን በጸሎት እንዲተባበሩ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ ነበር።
"በሚሰቃየው ዩክሬን፣ በመካከለኛው ምስራቅ - ፍልስጤም፣ እስራኤል፣ ሊባኖስ እና አሁን በሶሪያ - በምያንማር፣ በሱዳን እና ሰዎች በጦርነት እና በዓመፅ በሚሰቃዩበት ቦታዎች ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን መጸለይን እንቀጥል" ሲሉ ጳጳሱ ተማጽነዋል።
በጦርነት ላይ ያሉ አገሮች
እ.አ.አ በጥቅምት 7/2023 ዓ.ም ሃማስ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት በኋላ ከ40,300 በላይ ሰዎች በተገደሉበት እና በአጎራባች ሊባኖስ የእስራኤል ጥቃቶች ባለፉት ወራት ተባብሰው በተገኙበት በጋዛ ውስጥ ብጥብጥ መቀጠሉን የሚታወቅ ሲሆን፣ ዩክሬን በቅርቡ 1,000 ቀናት ሙሉ የሩሲያ ወረራ ከደረሰበት አሳዛኝ ክስተት በኋላ፥ እ.አ.አ በ 2021 ዓ.ም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተወገደ በኋላ የእርስ በርስ ጦርነት በሚካሄድባት ምያንማር፣ በሱዳን ከሚያዝያ ወር 2023 ዓ.ም ጀምሮ በጦር ኃይሉ እና በወታደራዊ አማፂያን መካከል በተደረገው ጦርነት ከ60,000 በላይ ሰዎችን ገድሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም ዋና ከተማዋን ደማስቆን ያዝን ከሚሉ አማፂያን ጋር ላለፉት 14 ዓመታት የዘለቀው ግጭት በሶሪያ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ ጠቅሰዋል።