ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ድሆችን በደስታ ልብ እንርዳ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጳጳሳዊ የሚሲዮናውያን ሥራ በጎ አድራጊዎች ቡድን ባደረጉት ንግግር “በኅብረተሰቡ ጥግ የሚኖሩትን” መደገፍ ያለውን ደስታ አጽንኦት ሰጥተዋል። አሁን በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩት የቪዬትናም ተወላጅ ልኡካን ቡድን በሮም መንፈሳዊ ንግደት እያደረገ ሲሆን ታኅሣሥ 10/2017 ሐሙስ እለት በቫቲካን በኮንቼስቶሪ አዳራሽ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢየሱስን በሁሉም ቦታ ማወጅ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ መጪው የቅዱስ በር መክፈቻ እና የኢዮቤልዩ ዓመት መጀመሪያ ሲናገሩ ይህ የተቀደሰ ጊዜ "ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እውነተኛ እና ግላዊ ግንኙነቶች" እንዲኖረን ዕድል እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል ። "ተስፋ በፍጹም አያሳፍረንም" የተሰኘውን የጳጳሱን ሰነድ በመጥቀስ ኢየሱስ “ሁልጊዜ በሁሉም ቦታ እና ለሁሉም ተስፋችን” መሰበክ እንዳለበት ለቡድኑ አሳስቧቸዋል።
የቤተክርስቲያንን የሚስዮናዊነት ስራ መደገፍ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የዓለም አቀፉን ቤተክርስቲያን የሚስዮናውያን እና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ለመደገፍ” ያላቸውን ቁርጠኝነት በማመስገን በቦታው የተገኙትን ስለለምያደርጉት ጥረት አምሰግነዋል። እነዚህ ጥረቶች የወንጌልን መልእክት “በዓለም ዙሪያ ላሉ ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን” ለማድረስ የሚረዱ ተጨባጭ የእምነት መግለጫዎች መሆናቸውን ተናግሯል።
ደስተኛ እርዳታ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ዘመን ላይ በማሰላሰል ሰዎች “እርስ በርስ የሚደጋገፉበትን” ማህበረሰብ አስታውሰዋል። ዛሬም ቢሆን ክርስቲያኖች "ከመካከላችን ትንሹን እንድንከባከብ ለጌታ ትእዛዝ ምላሽ እንዲሰጡ" ተጠርተዋል ብሏል። የተቸገሩትን እንዲረዷቸው “ደስተኛ ልባቸውና ፈገግታ ያላቸው” በማለት አበረታቷቸዋል።
እምነት ለልገሳ ያነሳሳል
በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ አሜሪካ የተሰደዱትን የብዙ የቬትናም ካቶሊኮችን “ጽኑ እምነት” አወድሰዋል። ከቅድመ አያቶቻቸው ሳይቀር "ክርስቲያን ማህበረሰቦችን ለመደገፍ" ያላቸውን ፍላጎት የሚያነሳሳ "ውድ የመነሳሳት ምንጭ" እንደሆነ ገልጿል።