ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ዋና የሰላም ግንቢ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአውሮፓውያኑ 2024 ዓ. ም. ደከመኝ ሰለኝ ሳይሉ ያለማወላወል የሰላም እርምጃዎችን ወስደዋል። ሥፍር ቁጥር በሌላቸው ጥሪዎች እና አጋጣሚዎች፥ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ወንድማማችነትን እንዲያበረታቱ እና እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፤ እያንዳንዳችንም የሰላም መሣሪያዎች እንድንሆን ጋብዘውናል። ወደ ጎርጎሮሳውያኑ አዲስ ዓመት ሲገባ የኢዮቤልዩ ዓመት ጉዞን በሚያበራ ተስፋ፥ “ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋችን እና ወደ ሰላም መግቢያ በራችን ነው!” በማለት ያስተላለፉት መልዕክት በሁሉም ዘንድ በደንብ ይደመጣል።

 

31 December 2024, 12:20