ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ 'እግዚአብሔር ሁልጊዜ እና ሁሉንም ነገር ይቅር ይላል' ማለታቸው ተገለጸ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቀን፣ 'እግዚአብሔር ሁልጊዜ እና ሁሉንም ነገር ይቅር ይላል' አሉ!
ቅዱስ አባታችን የመጀመሪው የክርስቲያን ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ በዓልን አስመልክተው ባደረጉት አስተንትኖ ምእመናን ዛሬ በእምነታቸው ምክንያት በስደት ላይ ላሉ ሰዎች ፍላጎት ይኖሩ እና ይጸልዩ እንደሆነ ራሳቸውን እንዲጠይቁ ጋብዟል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ጌታ ሁል ጊዜ ወሰን በሌለው ምህረቱ ይቅር ይላል!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን የማጽናኛ ማሳሰቢያ ለምእመናን የተናገሩት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን ከተከበረበት የገና በዓል በመቀጠል በታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም የተከበረውን የቅዱስ ኢስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማዕት አመታዊ በዓል ላይ ካደረጉት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ በእለቱ ስርዓተ አምልኮ ላይ ተንተርሰው ባደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ነው።
ለገዳዮቹ ጸለየ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጀመሪያ አመለካከታቸውን ሲገልጹ እስጢፋኖስ ምንም ረዳት የሌለው፣ በዓመፅ እየተሰቃየ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እንደ እውነተኛ ነፃ ሰው፣ ገዳዮቹን እንኳን መውደዱን እና ነፍሱን እንደ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መስጠቱን እንደቀጠለ ነበር ብለዋል።
በዚህ መንገድ ቅዱስ አባታችን ያመሰገኑት ዲያቆን እስጢፋኖስ በሞቱ ጊዜም ቢሆን የጌታን የምሕረትና ፍቅር በመኮረጅ ‹‹የሰው ልጅ ሁሉ ይድኑ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ ምኞት ላለው ለእግዚአብሔር ምስክር ሆኖ ታየ። እናም ማንም እንዳይጠፋ ወደ እግዚአብሔር ጸለዬ" ብለዋል።
"ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ"
ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳሉት "ለልጆቹ ሁል ጊዜ መልካም እና መልካም ነገርን ለሚፈልግ፣ ለሚመኝ፣ ማንንም የማያገል፣ እነርሱን ለመፈለግ የማይታክት እና ካገኛቸው በኋላ ልጆቹን የሚቀበላቸው፣ የተሳሳቱ ወደርሱ ተጸጽተው ይመለሳሉ ዘንድ የሚጠባበቅ፣ የአባታችን የእግዚአብሔር ምስክር ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትንሽ ጊዜ ወስደው “እግዚአብሔር ይቅር ለማለት አይታክትም። ይህን አስታውሱ፡ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይቅር ይላል፣ እግዚአብሔርም ሁሉንም ነገር ይቅር ይላል" ያሉ ሲሆን “እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ዛሬም ቢሆን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በወንጌል ምክንያት አልፎ አልፎ እስከ ሞት ድረስ የሚሰደዱ ብዙ ወንዶችና ሴቶች አሉ” ብሏል።
"ስለ እስጢፋኖስ የተናገርነው ለእነርሱም ይሠራል" ሲሉ አፅንዖት ሰጥው የተናገሩ ሲሆን "ከድካም የተነሳ እንዲገደሉ አይፈቅዱም ወይም አንድን ርዕዮተ ዓለም ለመከላከል አይፈቅዱም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው የመዳን ስጦታ ተካፋይ እንዲሆኑ ለማድረግ ነብሳቸውን ይሰጣሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ ይህን የሚያደርጉት ለገዳዮቻቸው የሚጠቅም መሆኑንና እንደሚጸልዩላቸውም በመግጽ ነው ብለዋል።
ብጹዕ ክርስቲያን ደ ቼርጌ
የዘመናችን ሰማዕት የሆነው ብጹዕ ክርስቲያን ዘ ቼርጌ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ትቶልናል ያሉት ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. በ1996 ዓ.ም በአልጄሪያ ለአስር አመታት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በሰማዕትነት ከተገደሉት ሰባቱ የቲቢሪን መነኮሳት አንዱ ነበሩ ብለዋል።
የቲቢሪን ገዳም ከፍተኛ አለቃ የነበረው ብጹዕ ክርስቲያን ዘ ቼርጌ እና ሌሎች ስድስት መነኮሳት ወንድሞች ሉክ ዶቺየር፣ ክሪስቶፍ ሌብሬተን፣ ሚሼል ፍሉሪ፣ ብሩኖ ሌማርቻንድ፣ ሴለስቲን ሪንጊርድ፣ ፖል ፋቭሬ-ሚቪል፣ ሁሉም አንገታቸው ተቆርጦ እና ጭንቅላታቸው ከሁለት ወራት በኋላ ከቲቢሪን ብዙም ሳይርቅ ተገኝቷል፣ ነገር ግን በድን አካላቸው ፈጽሞ አልተገኘም፣ አስክሬናቸው እዚያ ባልታወቀ ሥፍራ ተቀብሮ ይሆናል የሚል ግምት እንዳለ ተናግረዋል።
ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን በተመለከተ ሲናገሩ ብፁዕ ክርስቲያን ዘ ቼርጌ ቀድም ሲል ማለትም መስዋዕትነት ከመቀበላቸው በፊት ቀድመው እንደ ገመቱት እና በጹሑፍ እንዳሰፈሩት ከሆነ ገዳያቸው በመጨረሻ ሰዓት የመጣ ጓደኛቸው እንደሚሆን ተንብየው እንደ ነበረ የታንገሩ ሲሆን በመንፈሳዊ ኑዛዜአቸው፣ ሞታቸውን እና መቃብራቸውን በተመለከተ ሲተነብዩ “የወደፊቱን ነፍሰ ገዳያቸውን '“የመጨረሻው ደቂቃ ጓደኛ'” ብለው ጠርተው ነበረ ሲሉ ተናግረዋል።
ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ጥያቄዎች
ይህን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት ጳጳሱ ምእመናን አንዳንድ ጥያቄዎችን እንዲያስቡ አበረታቷቸዋል።
"ሁሉም እግዚአብሔርን እንዲያውቁ እና ሁሉም እንዲድኑ ፍላጎት ይሰማኛልን? እኔ ደግሞ መከራ የሚያደርሱብኝን በጎነት እፈልጋለሁን?" እና በመጨረሻም "በእምነታቸው ምክንያት ለሚሰደዱ ብዙ ወንድሞች እና እህቶች ፍላጎት እጸልያለሁን?" ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም መዳን ደፋር የወንጌል ምስክሮች እንድንሆን የሰማዕታት ንግሥት የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት ከተማጸኑ በኋላ አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።