ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የኢዩቤሊዩ ቅዱስ በርን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስር ቤት ከፈቱ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ በሚገኘው ረቢቢያ በመባል በሚጠራው በአዲስ መልክ በተሰራው ማረምያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ቤተክርስቲያን በር፣ በታሕሳስ 15/2017 ዓ.ም የተጀመረውን እና ለመጪው አንድ አመት ያህል የሚቆየውን የኢዩቤሊዩ የምሕረት አመት ምክንያት በማድረግ በታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም የቅዱስ በር በማረምያ ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መክፈታቸው ተገልጿል፣ ለታራሚዎች መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሁለተኛ የከፈትኩት ቅዱስ በር እዚህ ማረሚያ ቤት እንዲሆን ፈልጌ ነበር” በማለት የተናገሩት ሲሆን ይህም እርሳቸው በቫቲካን የሚገኘውን ቤተክርስቲያን ቅዱስ በር በይፋ በታኅሣሥ 15/2017 አመሻሹ ላይ ከከፈቱ በኋላ በመቀጠል የተከናወነ ዝግጅት በመሆኑ የተነሳ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሮም ሪቢቢያ አዲስ በተሰራው ማረምያ ቤት ሲደርሱ የቅዱስ በር መክፈት አስፈላጊነት ተናገሩ። በእስር ቤቱ የጸሎት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ሁሉም ሰው "የልባቸውን በሮች ለመክፈት እና ተስፋ ፈጽሞ እንደማያሳፍር እንዲረዱ እድል እንዲያገኙ" እንደሚፈልጉ ገልጿል።
በሮችን እና ልቦችን ክፈቱ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅዱስ በር በኩል ከተጓዙ በኋላ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን መርተዋል ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስብከታቸው ላይ የጉብኝታቸውን ታሪካዊ ምክንያት በማንፀባረቅ “የኢዩቤሊዩ መክፈቻ ውብ ምልክት” ሲሉ ገልጸውታል። ነገር ግን በሮች ከመክፈት በላይ፣ ጳጳሱ በቦታው የነበሩት እስረኞች ልባቸውን እንዲከፍቱ አበረታቷቸዋል። ወንድማማችነት "የተከፈቱ ልቦችን ይጠይቃል" ብሏል።
ጳጳሱ በማከልም እንዳንኖር ከሚያደርጉን የተዘጉ፣ የደነደነ ልቦች መጠንቀቅ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ኢዮቤልዩ ልባችንን ለተስፋ “ለመክፈት” ጸጋ እንደሚሰጠን ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን በጣም አስቸጋሪ እና ፈታኝ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንኳን ተስፋ በፍጹም እንደ ማያሳፍረን ቅዱስነታቸው ገልጿል።
ተስፋ መልሕቅ ነው
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተስፋን በገመድ ታስሮ በባህር ዳርቻ ላይ ካለው መልህቅ ጋር አመሳስለውታል። “አንዳንድ ጊዜ ገመዱ ከባድ ነው፣ እና እጃችንን ይጎዳል” ሲሉ የገለጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት እንኳን የተስፋ መልህቅ ወደ ፊት እንድንሄድ ያደርገናል፣ ምክንያቱም ሁል ጊዜ ከፊታችን የሆነ ነገር አለ ሲሉ ተናግሯል።
በግማሽ የተዘጋ ልብ አይኑራችሁ
“የሰው ልብ በተዘጋ ጊዜ እንደ ድንጋይ ይጠነክራል። ርኅራኄን ይረሳዋል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስጠንቅቀዋል። “እንዴት ማደረግ እንዳለበት ሁሉም ሰው ያውቃል” ሲሉ በማበረታታት በቦታው የነበሩት እስረኞች ለተስፋ ክፍት እንዲሆኑ መክሯቸዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተጨማሪም ልባቸው የተዘጋ ወይም ግማሽ የተዘጋ መሆኑን ሁሉም ሰው እንደሚያውቅ አስረድተው የከፈቱት ቅዱስ በር “የልባችን ደጅ ምልክት ነው” በማለት ለተሰበሰቡት በማሳሰብ ደምድመዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሁሉ በእውነት እንደሚጸልዩላቸው በመናገር ታራሚዎቹም በበኩላቸው ለቅዱንስተቻው ጸሎት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።