ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ተስፋችሁን በማያልቀው በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ አድርጉ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደምያደርጉ ይታወቃል። የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በእለቱ የጽንሰታ ማርያም አመታዊ በዓል ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ተስፋችሁን በማያልቀው በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ አድርጉ ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራን የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው እለት ስርዓተ አምልኮ ላይ የጽንሰታ ማርያም ዓመታዊ በዓል እያከበርን ሲሆን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት፣ እጅግ ውብ ጊዜዎች ስለሆኑት አንዱ ወንጌሉ ይነግረናል፣ ይህም የኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ መነገሩ ነው  (ሉቃስ 1፡26-38)፣ ማርያም ለሊቀ መላእክት ገብርኤል “እንዳልከው ይሁንልኝ” በማለት ቃል ሥጋ እንዲለብስ እሽታዋን ገለጸች። የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ትዕይንት እጅግ አስደናቂ እና ስሜትን የሚቀሰቅስ ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ልዑል፣ ሁሉን ቻይ የሆነው በመልአኩ በኩል ከናዝሬት አንዲት ወጣት ሴት ጋር ሲነጋገር ለእሱ የማዳን እቅድ ትብብርዋን ጠይቋል። ዛሬ የተወሰነ ጊዜ ካገኛችሁ የቅዱስ ሉቃስን ወንጌል ፈልጉ እና ይህን ትዕይንት አንብቡ። ጥሩ ስሜት እንደሚሰማችሁ  አረጋግጣለሁ፣ በጣም ጥሩ!

የሰማዩ አባት ጣት የሰውን ልጅ የሚነካበትን ሁኔታ በምያሳየው እና በሲስቲና ቻፕል ውስጥ በማይክል አንጄሎ ተስሎ የተቀመተው ስዕል የአዳም አፈጣጠር ትዕይንት ውስጥ እንደነበረው፣ ስለዚህ እዚያም ሰው እና መለኮት ተገናኙ፣ በቤዛችን መጀመሪያ ላይ፣ ድንግል ማርያም “እሺ” ባለችበት በተባረከች ቅጽበት፣ የሚያስደንቅ ጣፋጭ ጊዜ ይገናኛሉ። እሷ ከትንሽ ዳር ከተማ የመጣች ሴት ናት፣ እናም ለዘላለም ወደ ታሪክ ማእከል ትጠራለች-የሰው ልጅ እጣ ፈንታ በእሷ ምላሽ ላይ ይመሰረታል ፣ ይህም ፈገግታ እና እንደገና ተስፋ ሊያደርግ ይችላል ፣ ምክንያቱም እጣ ፈንታው በጥሩ እጆች ውስጥ ተቀምጧል። በመንፈስ ቅዱስ የተፀነሰውን አዳኝ ታመጣለች።

ስለዚህ ማርያም፣ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ሰላምታ እንዳላት፣ “ጸጋ የሞላባት” (ሉቃ.1፡28)፣ ንጽህት፣ የሆነች፣ ሙሉ በሙሉ ራሷን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሰጠች፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር የሆነች፣ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር የተማመነች ናት። ፈቃዱን የሚቃወም፣ እውነትንና ምፅዋትን የሚቃወም ምንም ነገር በእሷ ውስጥ የለም። ትውልዶች ሁሉ የሚያመሰግናት ብጽዕት እርሷ ናት። እኛም ደስ ይበለን ምክንያቱም ንጽዕት የሆነችው እርሷ አዳኛችን የሆነውን ኢየሱስን ስለሰጠችን!

ወንድሞች እና እህቶች፣ እናም ይህን ምስጢር በማሰላሰል እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን፡ በእኛ ጊዜ፣ በጦርነቶች በተጎሳቆለው፣ አለምን ለመቆጣጠር እና ለመግዛት ከፍተኛ ጥረት በሚደረግበት ጊዜ ተስፋዬን የት አደርጋለው? በጥንካሬዬ፣ በገንዘቤ፣ በኃያላን ጓደኞቼ ላይ ነው ወይ? ተስፋዬን እዚያ አደርጋለሁ? ወይስ ወሰን በሌለው የእግዚአብሔር ምሕረት ላይ? እናም በመገናኛ ብዙኃን እና በይነመረብ ላይ የሚንሸራሸሩ ብዙ የውሸት አንጸባራቂ ሞዴሎች ፊት ለፊት ፣ ደስታዬን የት ነው የምፈልገው? የልቤ ሀብት የት አለ? እግዚአብሔር በነጻነት ስለሚወደኝ፣ ፍቅሩ ሁል ጊዜ የሚቀድመኝ እና ወደ እሱ ንስሐ ገብቼ ስመለስ ይቅር ሊለኝ ዝግጁ ነውን? በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ በዚያ ላይ ተስፋ አለኝ ወይ? ወይንስ ራሴን እና ፈቃዴን ለማረጋገጥ እየሞከርኩ ነው?

ወንድሞች እና እህቶች፣ የኢዮቤልዩ ቅዱስ በር መክፈቻ ሲቃረብ፣ የልባችንን እና የአዕምሮአችንን በሮች ለጌታ እንክፈት። ከንጽህተ ማርያም ተወለደ፡ አማላጅነቷን ማርያምን እንማፀናለን፥ እናም ምክሬን እሰጣችኋለሁ። ዛሬ ጥሩ ኑዛዜ ለማድረግ ለመወሰን ጥሩ ቀን ነው። ዛሬ፣ በዚህ ሳምንት፣ እስከሚቀጥለው እሁድ ድረስ መሄድ ካልቻላችሁ ልባችሁን ክፈቱ እና ጌታ ሁሉንም ነገር፣ ሁሉንም ነገር ይቅር ይላል። ስለዚህ በማርያም እጅ የበለጠ ደስተኞች እንሆናለን።

09 December 2024, 11:19

መልኣኩ ገብርኤል ማሪያምን አበሰራት የሚለው የቀርብ ጊዜ ጸሎት

ሁሉንም ያንብቡ >
Prev
January 2025
SuMoTuWeThFrSa
   1234
567891011
12131415161718
19202122232425
262728293031 
Next
February 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728