ፈልግ

ፍይል፤ በሱድና የሚደርገው የእርስ በእርስ ግጭት ያስከተለው መዘዝ ፍይል፤ በሱድና የሚደርገው የእርስ በእርስ ግጭት ያስከተለው መዘዝ  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በግጭት እና በሐዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች ሁሉ ይጸልያሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በደቡብ ኮሪያ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ለተጎዱ እና በሕይወት ለተረፉ ሰዎች ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በዓለም ዙሪያ በጦርነት ምክንያት ለሚሰቃዩ ቤተሰቦች ያላቸውን ቅርበት ገልጸዋል ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ቤተሰብ በዓል ላይ በታኅሣሥ 20/ 2017 ዓ.ም ለምእመናንን ባደረጉት ንግግር ሃሳባቸውን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በቅሶ ላይ ላሉ እና በግጭት ለተጎዱ ቤተሰቦች አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ንግግር ያደረጉት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ እና በመገናኛ ብዙኃን እርሳኧቸውን ለሚከታተሉ ቤተሰቦች ልዩ ሰላምታ ያቀረቡ ሲሆን “ዛሬ በአዎርፕላን አደጋ ምክንያት ለቅሶ ላይ ለሚገኙት በደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ ብዙ ቤተሰቦች ጸሎት እንዲደረግ" ጥሪ አቅርበዋል።  

በደቡብ ኮሪያ አውሮፕላን ማረፊያ ሲያርፍ የነበረ አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ የ 177 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ለተረፉት እና ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች በጸሎት ከእናንተ ጋር እቀላቀላለሁ" ብለዋል።

በጦርነት ለሚሰቃዩ ቤተሰቦች የጸሎት ጥሪ አቅርበዋል።

እናም በድጋሚ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግጭት ለተጎዱ ሰዎች ሁሉ መቀራረብን እና ጸሎትን ጠይቀዋል፡- “በጦርነት ምክንያት ለሚሰቃዩ ቤተሰቦች እንጸልይላቸው፣ በጦርነት በምትታመሰው ዩክሬን፣ በፍልስጥኤም፣ በእስራኤል፣ በምያንማር፣ በሱዳን እና በሰሜን ኪቩ። በግጭት ለተጎዱ ቤተሰቦች ሁሉ እንጸልይላቸው” ብለዋል።

30 December 2024, 12:06