ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጆ ባይደን ጋር እ.አ.አ 2021 ዓ.ም በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጆ ባይደን ጋር እ.አ.አ 2021 ዓ.ም በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከጆ ባይደን ጋር በስልክ ተነጋገሩ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስክስ እና ተሰናባቹ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት በስልክ ተነጋገሩ። "ሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋት እና የእምነት ነፃነትን ለማስጠበቅ" ለምያደርጉት ጥረት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን አመስግነዋል። የአሜሪካው ተሰናባች ፕሬዚዳንት የሆኑት ጆ ባይደን በጥር ወር ቫቲካንን እንዲጎበኙ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያቀረቡላቸውን ጥሪ እና ግብዣ ተቀብለዋል። በኅዳር 29/2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባደረጉት የመላከ እግዚአብሔር ጸሎት ማብቂያ ላይ ባስተላለፉት መልእክት በዩናይትድ ስቴትስ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እስረኞች እጣ ፈንታ እንደ ሚያሳስባቸው እና የሞት ፍርድ በሌላ ቅጣት እንዲለወጥ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና የአሜሪካው ተሰናባች ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በታህሳስ 10/2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በስልክ መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን ውይይቱ የተካሄደው ፕሬዝዳንት ባይደን የስልጣን ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ እና በቅርብ አመታት ውስጥ ከተናገሩት ወይም ከተገናኙት ብዙ ጊዜዎች መካከል የመጨረሻው ነው።

ሁለቱ መሪዎች በበዓል ሰሞን በዓለም ዙሪያ ሰላምን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች ላይ መወያየታቸውን የዋይት ሀውስ መግለጫ አስታውቋል። መግለጫው ባይደን “የሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር እና የሃይማኖት ነፃነቶችን ለማስጠበቅ ላደረጉት ጥረት ጨምሮ ዓለም አቀፍ ስቃይን ለመቅረፍ ሊቀ ጳጳሱ ላደረጉት ቀጣይ ቅስቀሳ አመስግነዋል" በማለት ገልጾታል።

ፕሬዝዳንቱ "በተጨማሪም በሚቀጥለው ወር ቫቲካን እንዲጎበኙ በብፁዕ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ግብዣ የቀረበላቸውን ጥሪ በአክብሮት ተቀብለዋል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል። እ.ኤ.አ ጥር 20/2025 ዓ.ም ከዋይት ሀውስ ከመውጣታቸው በፊት ይህ የቫቲካን ጉብኝት የመጨረሻቸው ይሆናል፣ በምትካቸው ዶናልድ ትራምፕ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ እንደ ሚፈጹም ይጠበቃል።

የሞት ፍርደኛ ለሆኑ ሰዎች የጳጳሱ የይግባኝ ጥሪ

በተለይ ከሊቀ ጳጳሱ ልብ ጋር በጣም ከሚቀራረቡ ጉዳዮች አንዱ በሞት ፍርደኞች ላይ የሚገኙ የእስረኞች እጣ ፈንታ ነው። ይህ ርዕሰ ጉዳይ ምንጊዜም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስፈላጊ ሆኖ ቆይቷል፣ እ.አ.አ በ2018 የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አንቀጽ 2267 በማሻሻያ ላይ የሞት ቅጣት በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት እንደሌለው በድጋሚ እንዲያረጋግጥ አድርገዋል - ምክንያቱም፣ አንድ ሰው ከባድ ወንጀል ቢሰራም እንኳን የሰው ልጅ የሕይወት ክብር ሳይገረሰስ እንዳለ ሊቆይ ይገባል በሚል አስተምህሮ እንዲለወጥ አድርገዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በመስከረም ወር 2022 ዓ.ም ይፋ ባደረጉት ወርሃዊ የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ፍትህን የማያመጣ፣ ነገር ግን በቀልን የሚያበረታታ እርምጃ “እቢይ” ሊባል ይገባል ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል ።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ፣ የኢዮቤልዮውን የተስፋ እና የምሕረት ጊዜ በመጠባበቅ እንደገና ጉዳዩን አጉልቶ አሳይቷል—በኢዮቤልዩ ዓመት ይፋ ባደረጉት ቡል ወይ ይፋዊ ሰንድ ላይ ቅዱስነታቸው እንደጻፉት ከሆነ የሞት ፍርድ በሌላ ዓይነት ፍርድ እንደሚለወጥ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ለድሆች አገሮች የውጭ ዕዳ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞት ቅጣትን ማስወገድ፣ በአሁኑ ወቅት ከ50 በላይ ሀገራት የሞት ቅጣት ማስቀጠላቸውን ቅዱስነታቸው እንደ ምያሳስባቸው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሞት ቅጣትን "ከክርስትና እምነት ጋር የሚጻረር ድርጊት" እና "የይቅርታ እና የመልሶ ማቋቋም ተስፋን ሙሉ በሙሉ የምያጠፋ" ሲሉ ገልጸዋል።

በታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማሕበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የጽንሰተ ማርያም አመታዊ በዓል ሲከበር ቅዱስ አባታችን ምእመናን “በዩናይትድ ስቴትስ በሞት ፍርድ ላሉ እስረኞች እንዲጸልዩ” ጥሪ አቅርበዋል " ፍርዳቸው እንዲቀለበስ፣ እንዲቀየር እንጸልይ። እነዚህን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን እናስብ እና ከሞት የሚያድናቸው ጸጋውን ጌታን እንለምነው" ማለታቸው ይታወሳል።

የአሜሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት አቤቱታ

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን ቃል ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በአሜሪካ ላሉ ካቶሊኮች በሙሉ አፋጣኝ ጥሪ አቅርቧል፣ በአሁኑ ወቅት በፌዴራል ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አርባ ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ ወደ የዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀየር ፕሬዝደንት ባይደንን እንዲጠይቁ አሳስቧል።

የካቶሊክ ቅስቀሳ አውታረ መረብ

ቀደም ሲል በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሞት ቅጣት እንዲወገድ የሚደግፈው የካቶሊክ እንቅስቃሴ ኔትወርክ  ብሔራዊ የካቶሊክ ድርጅት በአሁኑ ጊዜ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙትን 40 ሰዎች ቅጣቱን ለማቃለል የምያስችል ዘመቻ ከፍቷል።

እንደ ሥራ አስፈፃሚው ዳይሬክተሩ ክሪሳን ቫላንኮርት መርፊ አገላለጽ ፕሬዚዳንት ባይደን - አስቀድሞ እ.አ.አ በሰኔ 2021 በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተወሰነው የሞት ቅጣት ላይ ተሰናባችሁ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጊዜያዊ እገዳ መጣላቸው የሚታወስ ሲሆን መጪው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሞት ፍርድን ለመቀየር ቃል ገብተዋል - ይህ የካቶሊክን ትምህርተ ክርስቶስን አስተምህሮን ለመቀበል እና ይህ ህይወት ለማዳን ልዩ እና የመጨረሻ እድል ነው። ይህን ማድረግ ከኢዮቤልዩ የመጀመሪያ ወር ጋር የሚገጣጠም ሲሆን የፕሬዚዳንቱ የመጨረሻ ጊዜን ያመለክታል።

 

20 December 2024, 14:39