ፈልግ

የኢዩቤልዩ በር የአከፋፈት ሥራዓት የኢዩቤልዩ በር የአከፋፈት ሥራዓት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ኢዮቤልዩ፣ በጸጋ የተሞላ ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኘት እድል ይፈጥራል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለጣሊያኑ "ኢል ሜሰንጄሮ" ለተሰኘው ዕለታዊ ጋዜጣ በኢዮቤልዩ ላይ የሰጡትን አስተያየት አሳትሟል። በእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ውስጥ "ዮቤል" የሚባል የአውራ በግ ቀንድ ድምፅ በየመንደሩ ያስተጋባል፣ ይህም በሙሴ ሕግ የተደነገገውን ልዩ ዓመት የሚያመለክት ነው (ዘሌዋዊያን 25)።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ኢዮቤልዩ፣ የመታደስ ጊዜ

የኢዮቤልዩ ዓመት የመቤዠት እና የመታደስ ጊዜ ነበር፣ ዛሬም ቢሆን በሚያስደንቅ ሁኔታ ጠቃሚ በሆኑ ልማዶች እየተመሰለ ያለ ዝግጅት ሲሆን በዚያ አመት መሬት ሳይታረስ ይቀራል ወይም አይታረስም፣ ለሰዎች መሬት የእግዚአብሔር እንደሆነ እና የሰው ልጅ መሬትን ከመበዝበዝ ይልቅ መሬትን እንዲከባከበው በአደራ የተሰጠ ስጦታ መሆኑን የሚገልጽ ነው። ማህበራዊ ፍትህን ለመመለስ ጥረት እና እዳ ስረዛ የሚደረግበት ወቅት ነው፣ ይህ አሰራር በየሃምሳ አመት ይከሰት ነበር። ባሪያዎች ነፃ ይውጡ፣ ከጭቆናና ከአድልዎ የፀዳውን የሰው ልጅ ማኅበረሰብ ህልምን በማጎልበት - እግዚአብሔር በጋራ ጉዞ ላይ ሕዝቡን ወደ አንድ ቤተሰብ ያቋቋመበትን ዘፀአትን የሚያስታውስ ራዕይ ነው።

የተስፋ ጉዞ

በናዝሬት ምኩራብ አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት፣ ኢየሱስ የኢዮቤልዩን ጽንሰ ሃሳብ ተቀብሎ አዲስ እና የመጨረሻ ትርጉም ሰጠው። በምድር ላይ ራሱን እንደ እግዚአብሔር ፊት ገለጠ፣ ድሆችን እንዲቤዥ፣ ምርኮኞችን ነፃ እንዲያወጣ፣ እና የአብን ርህራሄ ለቆሰሉት፣ ለወደቁት እና ተስፋ ለሌላቸው እንዲገልጥ ተላከ።

ኢየሱስ የመጣው የሰውን ልጅ ከማንኛውም ዓይነት ባርነት ነፃ ለማውጣት፣ የዕውሮችን ዓይን ሊያበራ እና የተጨቆኑትን ነፃ ሊያወጣ ነው (ሉቃስ 4፡18-19)። የእርሱ መሲሃዊ ተልእኮ የኢዮቤልዩን ጠቀሜታ አስፋፍቷል፣ ሁሉንም አይነት የሰው ልጆች ጭቆና መፍታት የተልዕኮ አካል ነው። በኃጢአት ለታሰሩት፣ የመፈታት እና ተስፋ በመቁረጥ ነፃነትን የሚሰጥ የጸጋ ጊዜ ሆነ። በተጨማሪም አምላክን እንዳንገናኝ እና ሌሎችን እንዳንገነዘብ የሚከለክለንን ውስጣዊ ዓይነ ስውርነት ለመፈወስ እንደ ግብዣ ሆኖ አገልግሏል። ከሁሉም በላይ፣ ጌታን የመገናኘት ደስታን አነቃቃ፣ ይህም ሰዎች የህይወትን ጉዞ በአዲስ ተስፋ እንዲቀጥሉ አስችሏቸዋል።

ኢየሱስን በመገናኘት ያለውን ደስታ እንደገና ማግኘት

ከ13 ክፍለ ዘመን ጀምሮ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቦኒፋስ ስምንተኛ የመጀመሪያውን ኢዮቤልዩ ቡል ወይም አዋጅ ሲያወጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ነጋዲያን ወደ ሮም ከተማ ተጉዘዋል። የእነርሱ ውጫዊ ጉዞ የመታደስ ውስጣዊ ፍላጎትን ያሳያል፣ የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን—ፈተናዎች እና ትግሎች ቢኖሩም—ከቅዱስ ወንጌል ተስፋ ጋር ለማስማማት የምያስችል አጋጣሚ ነው። በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ የማይጠፋ የደስታ እና የፍላጎት ጥማት አለ። በህይወት ውስጥ እርግጠኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሰዎች አለመተማመንን፣ ጥርጣሬን እና ተስፋ መቁረጥን ለማሸነፍ ይፈልጋሉ። ተስፋችን ክርስቶስ ለዚህ ውስጣዊ ናፍቆት ምላሽ ይሰጣል፣ እርሱን የመገናኘትን ደስታ እንደገና እንድናገኝ ይጋብዘናል። ይህ ገጠመኝ ራሱን ይለውጣል እና ህይወትን ያድሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደጻፉት፡ “የክርስትና ሕይወት ተስፋን ለመመገብ እና ለማጠናከር ልዩ ጊዜዎችን የሚፈልግ ጉዞ ነው፣ ግቡን እንድንመለከት ከሚረዳን ጠቃሚ ጓደኛ ጋር የመገናኘት ሂደት ነው፤ እርሱም ከጌታ ኢየሱስ ጋር መገናኘት ነው” ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

ቅዱሱ በር፡ ወደ አዲስ ሕይወት መሸጋገሪያ

ኢዮቤልዩ ከእነዚህ ጉልህ ወቅቶች አንዱ ነው። በገና ዋዜማ የቅዱስ በር መከፈቱ የጉዞውን - መንፈሳዊ መታደስ - እና ከክርስቶስ ጋር በመገናኘት የቀረበውን አዲስ ህይወት እንድንቀበል የቀረበልንን ግብዣ ያሳያል። በ13 ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ የቤተክርስቲያን ኢዮቤልዩ ወቅት እንዳደረገችው እንደገና፣ ሮም ከአለም ዙሪያ የሚመጡ ምዕመናንን ትቀበላለች። በእነዚያ የመጀመሪያዎቹ ቀናት፣ ከሰሜን የመጡ መንፈሳዊ ነጋዲያን ስለ ዘለዓለማዊቷ ከተማ የመጀመሪያ እይታቸውን ለማየት ከሞንቴ ማሪዮ ሲወጡ፣ ሌሎች ደግሞ ከደቡብ ደርሰው የሮም ከተማን ለሁለት አቋርጦ የሚሄደው ቲብራይዶስ ወንዝ ላይ በትናንሽ ጀልባዎች እያቆራረጡ ይመጡ ነበር። ሁሉም ወደ ቅዱሱ በር ለመድረስ እና በሩ ላይ ለመርገጥ ከፍተኛ ጉጉትን ነበራቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እያንዳንዱ ኢዮቤልዩ ከሮማ ውበት ጋር በመንፈሳዊ ነጋዲያን ደረጃዎች ስብስብ ተለይቶ ይታወቃል።

ሮም፣ እንግዳ ተቀባይ እና እንግዳ አስተናጋጅ ከተማ

ለኢዮቤልዩ በዓል መንገዶችን ለማሻሻል፣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሳደግ፣ ቅርሶችን ለማደስ እና ከተማዋን ለማዘመን ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ነው። ነገር ግን፣ ከከተማው ዝግጅት ባሻገር፣ ኢዮቤልዩ ሮምን ልዩ የሆነ ጥሪን እንድትቀበል ጠርቷታል። ከተማዋ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የእንግዳ ተቀባይነት ቦታ እንድትሆን ተጋብዛለች፥ የልዩነት እና የውይይት መፍለቂያ፣ የአለም ቀለሞች እንደ ሞዛይክ የሚሰባሰቡባት የመድብለ ባህላዊ ማዕከል እንድትሆን ተጋብዛለች።

ሮም የዘላለም መንፈስን ልትይዝ ትችላለች። የመንከባከብ ህልም ይህ ነው፡- ሮም የክርስቲያናዊ ቅርሶቿን ውበት ለዓለም ትገልጣለች—በስነ ጥበቧ ግርማ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ ለእንግዳ ተቀባይነትና ወንድማማችነት ባለው ቁርጠኝነት ጭምር። ዝማሬውን እያስተጋባ የዚህች ከተማ ሁሉም ልብ እና ጎዳና ሁሉ በደስታ ይጩኽ

" የማትሞት የሰማዕታት እና የቅዱሳን ከተማ ሮም… ሀይልም ሆነ ሽብር አይበረታም ፣ ግን እውነት እና ፍቅር ይነግሳሉ።

 

18 December 2024, 15:41