ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ  በቲሞር ሌስቴ ከወጣቶች ጋር ሲገናኙ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቲሞር ሌስቴ ከወጣቶች ጋር ሲገናኙ  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “እያንዳንዳችሁ ዓለምን መለወጥ ትችላላችሁ” ሲሉ ለተማሪዎች ተናገሩ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ለሚገኙ ወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት፥ እያንዳንዳቸው አዲስ ነገር ወደ ዓለም ማምጣት እንደሚችሉ ገለጹ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የጣሊያን ክርስቲያን ሠራተኛ ማኅበር “A.C.L.I” ሮም ውስጥ ካለው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ተማሪዎችን ከሥራው ዓለም ጋር ለማስተዋወቅ የሚረዳ ዝግጅት ማክሰኞ ታኅሳስ 8/2017 ዓ. ም. ማቅረቡ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለተማሪዎቹ በላኩት መልዕክት “ዓለም ለእናንተ ፊቷን ከፍታለች” ብለው፥ ወደ ዝግጅቱ ሥፍራ ስትደርሱ ብዙ መሆናችሁ ሊያዘናጋችሁ ቢችልም ነገር ግን አስተዋጽዖአችሁ ይጎድላል” ሲሉ ተናግረዋል። እያንዳንዳችሁ ወደ ዓለም አዲስ ነገር እንደምታመጡ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው፥ ለዓለም በምታበረክቷቸው ሥራ በእውነት ሁሉም ነገር ሊለወጥ ይችላል” ብለዋል።

ኃይል እና ልብ
በቅርቡ “እርሱ ወደደን” በሚል አርዕስት ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሠነድ ላይ ያሰላሰሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ የዚህ ሐዋርያዊ ሠነድ ጽንሰ-ሐሳብ ዛሬ ለሠራተኞች ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ጠይቀዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክታቸውን በመቀጠል፥ በተለምዶ ልብን ከፍቅር እና ከጓደኝነት ጋር እንደምናያይዝ ገልጸው፥ “በእውነቱ ልባችንን ከእኛ ጋር ይዘን መጽሐፍ ቅዱስን ለማገልገል እና ለውሳኔ ሰጭነት የምንጠቀመው በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል” ብለዋል። ይህን መልዕክት የምጽፍላችሁ ወደ ሥራው ዓለም ስትገቡ በሚጠብቃችሁ ነገር ልትደነቁ ትችላላችሁ” ብለዋል።

“በእነዚህ ሁኔታዎች መካከል በሰላም እና በነጻነት ለመኖር ልባችሁን መጠበቅ ተማሩ” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንንችስኮስ ተማሪዎችን አሳስበዋል። በማከልም ወደሚያዋርዷችሁ፣ ወደሚያስቸግሯችሁ ጥያቄዎች እና እውነተኛነታችሁን ወደሚያሳጡ ጥያቄዎች አትመልሱ” በማለት መክረዋል።

ከመርሆቻችሁ ጋር መጣበቅ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “አንድ ሰው ለዓለም አስተዋፅዖ ለማበርከት ከፈለገ በሁሉም ነገር ደህና መሆን የለበትም” ሲሉ አሳስበዋል።

“ማኅበራዊ ክብርን ለማግኘት ወይም ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ የማታምኑ ምሳሌዎችን አትከተሉ” በማለት አሳስበው፥ “ክፉ መንፈስ ከሕልማችን እንድንርቅ በማድረግ ወደ ብቸኝነት በመምራት ከሥራው ዓለም እንድንወጣ ያደርገናል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለተማሪዎቹ ያስተላለፉትን መልዕክት ሲያጠቃሉ፥ “የጋራ መኖሪያ ምድራችንን መልሰን ለመገንባት እና ወንድማማችነትን ለማደስ አንድ ላይ በመሥራት የመገናኛ መረቦችን መገንባት ያስፈልጋል” በማለት ግብዣቸውን አቅርበዋል።

 

17 December 2024, 16:40