ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ሥልጣኔን ለመገንባት የሕይወትን ሕልውና ጠብቁ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእኩለ ቀን የመልአከ ሰላም ጸሎትን በመምራት በአዲስ ዓመት በዓል ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን “አስገራሚውን እና የገናን ደስታ” በማሰብ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት የዛሬውን ወንጌል አስታወሱ፣ መልአክት ለእረኞቹ በቤተልሔም በሚገኘው የእንስሣት ጋጣ እንዲሄዱ እና በእዚያ ሥፍራ አዳኝ፣ መጽሢሕ እና ጌታ የሆነውን ኢየሱስን እንዲጎበኙ" ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት እረኞቹ በስፍራው እንደ ተገኙ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል። ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ "ሁሉንም ሰው በሚያስደንቅ ሁኔታ ይሞላል" በማለት ገልጾታል፣ በገዛ ዓይናቸው ሕፃኑን ኢየሱስን እንዳዩት እና "ይህን ሁሉ የጠበቀች እና የምታሰላስል የማርያም ልብ" በእዚያ እንደሚገኝ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል እና እ.አ.አ በ2025 ዓ.ም አዲስ አመት ላይ በተጨማሪነት ታስቦ የዋለውን 58ኛውን የዓለም የሰላም ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ማለዳ ላይ በተከናወነው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"እግዚአብሔር ያድናል"
“እግዚአብሔር ያድናል” የሚለውን የኢየሱስን የዕብራይስጥ ትርጉም በማስታወስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ እንዴት በትክክል ጌታ እንደሚያደርገው እና ሕይወቱን ለእኛ በመስጠት ለመፈጸም ወደ ዓለም እንደመጣ" አብራርተዋል።
"እግዚአብሔር ስለ እኛ መወለድን መረጠ፡ ኢየሱስ የዘላለም ፍቅሩ መገለጥ ነው፣ እሱም ለዓለም ሰላምን ያመጣል" ብለዋል።
የማርያም ልብ
ከዚያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የማርያም ልብ "የአብ ምሕረትን ከሚገለጠው አዲስ ከተወለደው መሲሕ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ" አብራርቷል። ንጹሕ የሆነው የማርያም ልቧ፣ የመላእክት አለቃ ገብርኤልን አዋጅ ያዳመጠ ጆሮ፣ እና ለዮሴፍ የተሰጠ የሙሽሪት እጅ፣ እንዲሁም በኤልሳቤጥ እርጅና ወቅት ያጋጠማትን እቅፍ ያዳመጠ ጆሮ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለው የገለጹ ሲሆን "የማርያም ልብ አዲስ ከተወለደው ከልጇ ልብ ጋር ይስማማል" ሲሉ ገልጸዋል።
"በማርያም ልብ ውስጥ ለፍጥረት ሁሉ መዋጀት እና የመዳን ተስፋ ይመጣል" ብለዋል።
የእናት ልብ
እናቶች ሁል ጊዜ ልጆቻቸውን እንዴት በልባቸው እንደሚይዙ የተመለከቱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ የአዲስ ዓመት የሰላም ቀን በዓል ላይ እናቶችን በልዩ ሁኔታ ልናስታውሳቸው ይገባል ፣ “በልባቸው ደስ የሚላቸውን” እና “በመከራ የተሞላ ልብ”የተሸከሙ። ምክንያቱም ልጆቻቸው በግፍ፣ በትዕቢት፣ በጥላቻ ተወስደዋልና" ሲሉ ቅዱስነታቸው በሐዘኔታ እና በቁጭት ተናግሯል።
"ሰላም እንዴት መልካም ነገር ነው! እና የእናቶችን ልብ የሚሰብር ጦርነት እንዴት ኢሰብአዊ ነው!" ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።
የወንጌልን ደስታ መኖር
በማጠቃለያው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጀመሪያ የኢየሱስን መወለድ እያሰብን በዝምታ የመቆየት ችሎታችንን፣ አስደናቂውን የደግነት እና የድነት መልእክት በልባችን ለመንከባከብ እንዴት እንደምንጥር በመመልከት የራሳችንን፣ የውስጣችንን ተግባር እንድናከናውን ሐሳብ አቅርበዋል። እንዲሁም፣ በነፃነት የሰላም፣ የይቅርታ፣ የእርቅ ምልክቶችን በማቅረብ እንዲህ ያለውን ታላቅ ስጦታ እንዴት መመለስ እንደምንችል እንድናሰላስል መክሯል።
"የአምላክ እናት ቅድስት ማርያም የወንጌልን ደስታ በልባችን እንድናቆይ እና በአለም እንድንመሰክር እርሷ ትምራን" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠቃለዋል።