ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
Scherzo (Allegro) - Finale (Allegro)
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በሕጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝበዛ ልንቃወም ይገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለሚገኙ ምዕመናን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደምያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም ያደረጉት የምትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ "በአብ እጅግ የተወደደ" በሚል አርዕስት ባደረጉት አስተምህሮ በሕጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝበዛ ልንቃወም ይገባል ማለታቸው ተገልጿል።

በእለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል

ኢየሱስ ሕፃናትን እንደ ባረከ

እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም አይተው ገሠጹአቸው። ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ተዉአቸው፤ አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና። እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አለ (ሉቃስ 18፡15-17)።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡርና ክቡራን የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፍዳችሁ!

ይህንን እና የሚቀጥለውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለህፃናት፣ በተገቢው የገና ጊዜ አውድ ውስጥ ለማከናወን እፈልጋለሁ። በተለይ በህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ላይ እናሰላስላለን። በእርግጥም ዛሬ ዓይናችንን ወደ ማርስ ወይም ወደ ምናባዊ ዓለማት ማዞር እንፈልጋለን፣ ነገር ግን በዳርቻው ላይ የቀረውን እና የተበዘበዘ ወይም የተበደለውን ልጅ አይን ለማየት እንታገላለን። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚያመነጨው እና የብዙ ፕላኔቶች ህልውናዎችን የሚያቅድ ምዕተ-ዓመት ባለበት ወቅት ገና የተዋረደ፣ የተበዘበዘ፣ የሚሞት የቆሰለ የልጅነት መቅሰፍት ከዕቁብ አልተቆጠረም።

በመጀመሪያ ራሳችንን እንጠይቅ፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ልጆች ምን መልእክት ይሰጡናል? በብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዛት የሚገኘው ያህዌህ (ከስድስት ሺህ ስምንት መቶ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል) ከሚለው መለኮታዊ ስም በኋላ የሚገኘው ቃል ቤን “ልጅ” የሚለው ቃል አምስት ሺህ ጊዜ ያህል ጊዜ ተጠቅሶ እንደሚገኝ ማስተዋል ያስገርማል። " እነሆ፥ ልጆች የጌታ ስጦታ ናቸው፥ የማሕጸንም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው" (መዝ 127፡3) ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ይህ ስጦታ ሁልጊዜ በአክብሮት አይያዝም። የደስታ ዝማሬ በሚሰማበት፣ የተጎጂዎች ጩኸትም በሚሰማበት የታሪክ ጎዳናዎች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ይመራናል። ለምሳሌ የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ እናነባለን:- “ጡት የሚጠባው የሕፃን ምላስ ከጥም የተነሣ ወደ ትናጋው ተጣበቀ፥ ሕፃናት እንጀራ ለመኑ፥ የሚቈርስላቸውም የለም (4፡4)። እና ነቢዩ ናሆም በጥንቷ በቴቤስ እና በነነዌ የተፈጸሙትን ነገሮች በማስታወስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ልጆቿም በየመንገዱ ጥግ ተፈጠፈጡ” (3፡10) በማለት ጽፏል። ዛሬ ስንት ህጻናት በረሃብና በድህነት እየሞቱ ወይም በቦምብ እየተደበደቡ እንዳሉ አስቡት።

የቤተልሔም ሕፃናትን የገደለው የሄሮድስ የዓመፅ ማዕበል ገና በተወለደው በኢየሱስ ላይ እንኳ ፈነዳ። በታሪክ ውስጥ በሌላ መልኩ የሚደጋገም አሳዛኝ አስከፊ ክስተት ነው። እና እዚህ፣ ለኢየሱስ እና ለወላጆቹ፣ ዛሬም በብዙ ሰዎች ላይ እንደሚደረገው በባዕድ ሀገር ስደተኞች የመሆን ቅዠት ነው (ማቴ. 2፡13-18)። አውሎ ነፋሱ ካለፈ በኋላ፣ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ናዝሬት ተብሎ በማይጠራ መንደር ውስጥ አደገ። የአናጺውን ሙያ ከህጋዊ አባቱ ከዮሴፍ ይማራል (ማር. 6:3፤ ማቴ 13:55)። በዚህ መንገድ “ሕፃኑ አደገ በጥበብም ተሞልቶ አደገ። የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ” (ሉቃስ 2፡40)።

በአደባባይ ህይወቱ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከመንደር ወደ መንደር እየሰበከ ሄደ። አንድ ቀን አንዳንድ እናቶች ወደ እርሱ ቀርበው እንዲባርክ ልጆቻቸውን አቀረቡለት፣ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው። ስለዚህ ኢየሱስ ሕጻናት እንደ ተራ ነገር የሚቆጠሩበትን ወግ በመጣስ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ አትከልክሏቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና" ስለዚህም ትንንሾቹን ለአዋቂዎች አርአያ አድርጎ ይጠቁማል። ደግሞም “እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም" (ሉቃስ 18፡16-17) በማለት አክሎም ተናግሯል።

በተመሳሳይ ምንባብ፣ ኢየሱስ ሕፃን ጠርቶ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አስቀመጣቸው እና “ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም” (ማቴ 18፡3) ብሏል። “በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ ላይ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር” (ማቴ 18፡6) ይላል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ልጆችን ችላ እንዲሉ ወይም እንዲንገላቱ፣  መብታቸው እንዲነፈግ መፍቀድ የለባቸውም፣ እንዲወደዱ እና እንዲጠበቁ መትጋት ግን ይኖርባቸዋል።  ክርስቲያኖች በልጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ወይም ብዝበዛዎች አጥብቀው የመከላከል እና የማውገዝ ግዴታ አለባቸው።

ዛሬ በተለይ ለአስገዳጅ ሥራ የተዳረጉ ሕፃናት በጣም ብዙ ናቸው። ነገር ግን ፈገግ የማይል እና ህልም የሌለው ልጅ ችሎታውን ማወቅ ወይም ማሳደግ አይችልም። በየትኛውም የአለም ክፍል ህይወትን በማያከብር ኢኮኖሚ የሚበዘብዙ ልጆች አሉ፥ ይህን ማድረግ ትልቁን የተስፋ እና የፍቅር አቅማችንን የሚበላ ኢኮኖሚ መገንባት ማለት ነው። ነገር ግን ልጆች በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላቸው፥ እና ልጅን የሚጎዳ ሁሉ በእሱ ተጠያቂ ይሆናል።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እራሳቸውን እንደ እግዚአብሔር ልጆች አድርገው የሚቆጥሩ እና በተለይም ወንጌልን ለሌሎች ለማድረስ የተላኩ ሰዎች በግዴለሽነት ሊቆዩ አይችሉም። ታናናሽ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከመወደድና ከመጠበቅ ባሻገር የልጅነት ጊዜያቸውን፣ ሕልማቸውን፣ የብዝበዛ ሰለባዎች እና መገለል ሰለባ መሆናቸውን መቀበል አይችሉም።

ጌታ አእምሯችንን እና ልባችንን ለእንክብካቤ እና ርህራሄ እንዲከፍት እንለምነው፣ እናም በዓለም ላይ ላሉ ወንድ እና ሴት ልጆች ሁሉ በእድሜ፣ በጥበብ እና በጸጋ እንዲያድጉ (ሉቃ. 2፡52)፣ ፍቅርን መቀበል እና መስጠት የሚችሉ ያድርጋቸው።

08 Jan 2025, 11:29

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >
Prev
April 2025
SuMoTuWeThFrSa
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930   
Next
May 2025
SuMoTuWeThFrSa
    123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031