ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ህይወትን እንድንከባከብና እ.አ.አ 2025ን ለማርያም አደራ እንድንሰጥ ጋብዘዋል

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች በታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም (2025) አዲስ አመት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። በዚህ እለት የቅድስተ ቅዱሳን እና የአምላክ እናት የሆነችው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ በዓለ ከአዲስ አመት ጋር መሳ ለመሳ ሆኖ መከበሩ ይታወሳል።የዚህ በዓል ዋዜማ የማታ ጸሎት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ተከናውኖ ካበቃ በኋላ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መሪነት መስዋዕተ ቅዳሴ መከናወኑ ይታወሳል። በእለቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅዱሳን ሁል ቅድስት የሆነችው የአምላክ እናት ክብረ በዓል ዋዜማ ላይ እንደ ተናገሩት ማርያም “በገና በዓል ምሥጢር ውስጥ ተመልሰን እንድንገባ ታደረጋናለች፣ ወደ ኢየሱስ ትመራናለች ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.ኤ.አ. 2025 ዓ.ም የሚጀመረውን የአዲስ አመት ምክንያት በማድረግ እና

በእለቱ "ቅድስት ማርያም የአምላክ እናት" መሆኗ በሚታሰብበት በዓል ዋዜማ ላይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ "እንደ እናት" የሚል ጭብጥ ያዘለ ስብከት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን "እንደ እናት" ማርያም እኛን ወደ ልጇ እንድንሄድ ትጠቁማለች እና ወደ ኢየሱስ ትመራናላች ብለዋል።

የገና ምስጢር

የዛሬው በዓል፣ “በገና ምሥጢር አንድ ጊዜ ተመልሰን እንድንገባ ያደረገናል" በማለት በሁለተኛው ንባብ የተቃኘው ምሥጢር፣ ቅዱስ ጳውሎስ “እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” ሲል ነግሮናል። እነዚህ ቃላት “ዛሬ በልባችን ያስተጋቡ” እና “መድኃኒታችን ኢየሱስ ሥጋ ሆኖ በሥጋ ድካም እንደተገለጠ ያስታውሰናል ብለዋል።

ኢየሱስ ከሴት መወለዱን ያስታውሰናል “እግዚአብሔር በእውነት ሰው የሆነው በሰው ማኅፀን ነው” - እግዚአብሔር “ግልጽ ያልሆነ ሃይማኖታዊ ስሜት ወይም ጊዜያዊ ስሜት” ሳይሆን “ፊትና ስም ያለው እና የሚጠራን” መሆኑን ያሳየናል፣ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር" መታከት የለብንም ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ ኢየሱስ “ከእኛ አንዱ ነው፣ እና ስለዚህ ሊያድነን ይችላል" ብለዋል።

የቅዱስ ጳውሎስም ቃል “በሥጋ ድካም ስለተገለጠው ስለ ክርስቶስ ሰውነት ሲናገር የኢየሱስ ትንሽ ሕፃን ሆኖ በድንግል ማርያም በኩል መምጣት አምላክ ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንደሚመርጥ ያሳያል:- “በትህትና እና በስውር” ሲሉ ተናግረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ ኢየሱስ “የእግዚአብሔርን ፍቅር በሰውነቱ ውበት ገለጠ፣ በመካከላችን እየኖረ፣ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን በማካፈል… በሰውነቱ ደካማነት እና ለደካሞች እና ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ባለው አሳቢነት፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ፊት ያሳየናል” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ውድ የሆነውን የሕይወትን ስጦታ” ለመጠበቅ “እንደ እርሷ” እንድንማር ተስፋ በማድረግ ይህንን አዲስ ዓመት የአምላክ እናት ለሆነችው ለማርያም አደራ እንድንሰጥ ጋብዘውናል።

ለሰው ሕይወት ሁሉ ሙሉ ዋጋ መስጠት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል በዚህ የዓለም የሰላም ቀን “ከእናት ልበ-ማርያም የሚፈልቀውን ጥሪ ሁላችንም እንድንቀበል እንጋበዛለን፤ ሕይወትን እንድን ከባከብ፣ ለሕይወት ሙሉ ዋጋ እንድንሰጥ፣ የሁሉንም ሰው የሕይወት ክብር እንዲመለስ ትጋብዘናለች" ያሉ ሲሆን ‘ከሴት መወለድ’ የሰላም ባህልን ለመገንባት መሠረቱ ይህ ነውና" ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

“ከመፀነስ እስከ ተፈጥሯዊ ሞት ድረስ የሰውን ሕይወት ክብር ለማክበር ጽኑ ቁርጠኝነት እንዲኖረን” የቀረበበት ምክንያት ይህ ነው ብሏል።

“ይህን አዲስ ኢዮቤልዩ ዓመት ለማርያም አደራ እንስጥ” በማለት ቅዱስ አባታችን ንግግራቸውን ደምድመዋል። “ጥያቄዎቻችንን፣ ጭንቀታችንን፣ መከራችንን፣ ደስታችንን እና በልባችን ውስጥ የምንሸከመውን ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሷ አደራ እንስጥ። ተስፋ እንደገና እንዲወለድ እና በመጨረሻም ለአለም ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን ዓለምን ሁሉ ለእርሷ በአደራ እንስጥ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

02 January 2025, 14:53