ብፁዕ ካርዲናል ክሬዬስኪ ሰላም እንዲያብብ ዓለም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይስገድ አሉ!
በካርዲናል ኮንራድ ክሬዬስኪ
ወደ ቅድስት ሀገር በእምነትና በጸሎት ተጉዤ ወደ እነዚህ ቦታዎች ጦርነት ወደ ሚካሄድበት፣ ጥላቻና በቀል፣ አንዱ ሌላውን የሚገድልበት፣ የውሃ፣ የምግብና የመብራት እጦት ወዳለበት ስፍራ ሄጄ ነበር። ለኛ ቅዱሳን በሆኑ ቀናቶች በተከበረው በገና በዓል ወቅት እንኳን ጦርነትና ግድያ አላቆሙም - በዩክሬን እንዳለው ሁኔታ ሁሉ በጋዛ ሰርጥ እንዲሁ እየሆነ ነው ብለዋል።
ወደዚች ምድር የደረስኩት በአለም ላይ ካሉት እጅግ የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች ወደ ሚገኙበት ስፍራ ነው፣የሄድኩትም በእምነት እና ጸሎት ተራራን በሚያንቀሳቅስ እና ግጭቶችን የሚያስወግድ የጸሎት መንፈስ ነበር ... ግን ለምን እንዲህ አይሆንም?
ኢየሱስ ወደሚኖርባቸው ቦታዎች ሁሉ ሄጄ ነበር። ወደ ናዝሬት፣ ወደ ቤተ ልሔም፣ ወደተሰቀለበት፣ ወደተገደለበት፣ እና ከሙታን ወደ ተነሳበት ሥፍራ ሁሉ ሄጄ ነበር። ስለዚህ “ጌታ ሆይ፣ ለምን ሰላም የለም? አንተ ግን ሰላም ትፈልጋለህ” ብዬ ጠየቅሁ። “ጌታ ሆይ ከክፉ ነገር ሁሉ አድነን በዘመናችንም ሰላምን ስጠን” በሚለው በዚህ ጸሎት ላይ ሁል ጊዜ አሰላስላለሁ። ታዲያ ለምን በዘመናችን ሰላም አትሰጠንም?
ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስንገባ እንዴት መስገድ እንዳለብን ብዙ አስቤ ነበር፣ ወደ እዚያ ለመግባት ጀርባችንን በደንብ ማጠፍ አለብን፣ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት በቤተልሔም እንኳ መስገድ፣ መስገድ አለብን።
ስለዚህ ምናልባት ዓለም ለእግዚአብሔር መስገድ አቁማ በወንጌል አመክንዮ መኖር ያቆመው የዓለምን አስተሳሰብ ስለለመደች ይመስለኛል።
ምናልባት እኛ ሰዎች እራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስቀምጠናል እና ለማዘዝ እና ለመኮነን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ያለ ምህረት፣ ያለ ፍቅር እናደርጋለን። ለዛም ሊሆን ይችላል ሰላም የማይኖረው - ምክንያቱም እኛ ለእግዚአብሔር አንሰግድም፣ ምክንያቱም ከእርሱ የድህንነት ምሥጢር በፊት መስገድ እንታክታለን።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የአብሮነት ምልክት እንዲሆኑ ኮንራድ ክሬዬስኪ ወደ ቅድስት ሀገር ላኩ
ረቡዕ ታኅሳስ 17/2016 ዓ.ም የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ በዓል ነበር፣ ወደ ኢየሱስ መቃብር ቀርቦ ሊገባ ሰገደ ሥጋውም በዚያ እንደሌለ፥ መነሣቱን ለማየት።
ዛሬ ግን አንሰግድም፤ ምንም እንኳን የእግዚአብሔርን ምሥጢር ለመረዳት፣ ፍቅሩንና ምሕረቱን ለመረዳት፣ እንደ ኢየሱስ ትምህርት አመክንዮ ለመኖር፣ በዚህ በቅድስት አገር ያሉት በሮች ይህን ማድረግ እንዳለብን ቢነግሩንም። እንደ ወንጌል አመክንዮ ለኢየሱስ መስገድ ይኖርብናል።
በእነዚህ ቀናት በቅድስት ሀገር ስለኖርኩ እና የእግዚአብሔርን ምስጢር ለመረዳት ስለጀመረ ጌታን አመሰግናለሁ። የአባታችን ጸሎት፣ ኢየሱስ ያስተማረን ጸሎት፣ “ጌታ ሆይ፣ ፈቃድህ ትሁን እንጂ የእኔ አይደለም፣ ምክንያቱም የእኔ ፈቃድ ባለበት፣ ጦርነቶች አሉ፣ ብዙ ሞት አለ” ይላል።
"መንግስትህ ትምጣ" የኛ ሳይሆን የኛ የጥፋት መንግስት ነው። "ስምህ ይቀደስ" የኔ አይደለም፣ ስሜ ሲቀደስ ለሌሎች አደገኛ ነኝ።
ከአባታችን ጸሎት በኋላ ካህኑ "አቤቱ ከክፉ አድነን በዘመናችንም ሰላምን ስጠን" ይላል። ተስፋዬ በእውነት በሰዎች ልብ ውስጥ ሰላም እንዲያብብ ነው።