ፈልግ

2019.10.19 Congregazione per la dottrina della fede

ቫቲካን ስለ አስከሬን ማቃጠል ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷ ትገለጸ!

በቅድስት መንበር የእመንት ጉዳዮችን የሚመለከተው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በብፁዕ ካርዲናል ማትዮ ዙፒ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ሲሆን የአንድ ሟች ሰው አስክሬን ተቃጥሎ አመዱ በጋራ ቦታዎች እንደ አስከሬን ማስቀመጫ ባሉ ቦታዎች ማስቀመጥ ይቻል እንደሆነ እና ትንሽ የአመድ ክፍል ለሟች ጉልህ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ ይቻል እንደሆነ የምያመልክት ጥያቄ አቅርበው ነበር።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሊቀ ጳጳስ ማትዮ ዙፒ ለቀረቡት ጥያቄዎች የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት እንዳረጋገጠው “የተለያዩ ሰዎች አስክሬን ከተቃጠለ በኋላ አመዱን ለማከማቸትና ለመጠበቅ” የተቀደሰ ቦታ ማዘጋጀት እንደሚቻል ያረጋግጣል። የቦሎኛ ሊቀ ጳጳስ ማትዮ ዙፒ አስክሬናቸው የተቃጠለ አማኞች አስከሬን በተመለከተ ሁለት ጥያቄዎችን የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት አቅርበዋል። ለሁለተኛው ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ የቤተ ክርስቲያኒቱ ባለ ሥልጣናት የሟቹን አመድ ክፍል ለሟች ሰው ታሪክ ጉልህ በሆነ ቦታ ለማስቀመጥ የቤተሰብ አባላትን ጥያቄ ግምት ውስጥ ማስገባት እና መገምገም እንደሚችሉ ይናገራል። የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ምላሽ ሙሉ ቃል በቫቲካን ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል እዚያ ላይ መመልከት ይቻላል።

ካርዲናል ዙፒ ዘመዶቻቸው የሟች አስከሬን እንዲቃጠል የሚመርጡ እና ከዚያም አመዱን በተፈጥሮ ውስጥ ለመበተን የሚመርጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ጥያቄዎቹን አቅርበዋል። ጥያቄዎቹ አመድ ከመበተን ጋር ተያይዞ በቀነሰው ወጪ “ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች” በሚል ፍላጎት ጭምር ነው ሲሉ የመጡት ሲሉ አክለው ገልጸዋል። እናም "የማቆያ ጊዜ ካለፈ በኋላ በአመድ ላይ ምን እንደሚደረግ አመላካቾችን ለማቅረብ ባለው ፍላጎት" ከቤተሰብ አባላት ጥያቄ ጋር ለማዛመድ ብቻ ሳይሆን "በይበልጥም ከክርስቲያናዊ አዋጅ ጋር የሥጋ ትንሣኤና የሚገባው ክብር ማግኘቱ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ጥያቄ እንደ ሆነ ተናግረዋል።

ስለዚህ የመጀመሪያው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡- “የሟቹን አመድ መበተን የሚከለክለውን ቀኖናዊ ክልከላ ከግምት ውስጥ በማስገባት ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ሰዎች አስክሬን ተቃጥሎ አመድ ለመሰብሰብና ለመጠበቅ የተወሰነ እና ቋሚ የሆነ ቅዱስ ቦታ ማዘጋጀት ይቻላልን? የእያንዳንዱ ሰው ዝርዝር የስማቸው ትዝታ እንዳይጠፋ፣ ልክ እንደ ሬሳ ሣጥኖች ውስጥ እንደሚደረገው፣ የተቃጠለ የሟቹ አስክሬን አመድ በጥቅል ተከማችተው እንዲቆዩ ይደረጋል ወይ?” ሁለተኛው ጥያቄ “አንድ ቤተሰብ ከቤተሰባቸው አባላት የተወሰነውን አመድ ለሟች ታሪክ ትልቅ ቦታ ባለው ቦታ እንዲያስቀምጥ ሊፈቀድለት ይችላል ወይ?” የሚል ነበር።

የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ቪክቶር ፈርናንዴዝ በተፈረመ እና እ.አ.አ በታኅሳስ 9/2023 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጸደቀው ጽሁፍ የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ለሁለቱም ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ሰጥቷል።

በመጀመሪያ ደረጃ እ.አ.አ በ 2016 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ “Ad resurgendum cum Christo” (ከክርስቶስ ጋር ከሞት ለመነሳት) በተሰኘው ሐዋርያዊ መመሪያ (ቁጥር 5) መሠረት፣ “አመድ በተቀደሰ ስፍራ፣ ለምሳሌ የመቃብር ቦታ፣ ወይም ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተዘጋጀ ቦታ መቀመጥ አለበት፣ ይህም ሥፍራ በቤተክርስቲያን ኃላፊዎች መታወቅ አለበት” በማለት ይናገራል። የዚህ ምርጫ ምክንያቶችም “ከቤተሰባቸው ወይም ከክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ጸሎትና መታሰቢያ እንዳይገለሉ” እና “ምዕመናን እንዳይረሱ ወይም አስከሬናቸው ክብር እንዳያጣ መከላከል” እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል። አክብሮት ማጣት፣ እንዲሁም “ከማይስማሙ ወይም አጉል ድርጊቶች” መከላከል ያስፈልጋል።

 

ሰነዱ በመቀጠል “እምነታችን የሚነግረን አንድ ዓይነት ሥጋዊ ማንነት ይዘን እንደምንነሳ ነው፤ ይህም ቁስ አካል ቢለወጥም ከዚህ ዓለም ውሱንነቶች ነፃ ቢወጣም” በማለት ይገልጻል። ከዚህ አንጻር “ትንሣኤ ‘አሁን በምንኖርበት በዚህ ሥጋ’ ይሆናል። ነገር ግን ይህ ለውጥ “በአንድ ወቅት የሰውን ልጅ አካል ፈጥረው የነበሩትን ተመሳሳይ የቁስ አካላት ማገገምን አያመለክትም። ስለዚህ “ከሞት የተነሳው ሰው አካል ከመሞቱ በፊት የነበሩትን ተመሳሳይ ንጥረ ነገሮች ያቀፈ ብቻ አይደለም። ስለዚህ ይህ በቀላሉ ብቻ ስላልሆነ ትንሳኤ አካሉ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋ ወይም ቢበታተንም ሊከሰት ይችላል። ይህም የተቃጠሉ አስክሬኖች አመድ መያዣ ውስጥ የሟቾች አመድ አንድ ላይ የሚከማች እና ተለይተው የማይቀመጡበትን ምክንያት እንድንረዳ ይረዳናል።

የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት አፅንዖት መስጠቱን በመቀጠል “የሟቹ አስክሬን አመድ፣ በተጨማሪም የሰውዬው ታሪካዊ ጉዞ አካል ከሆኑት ቁስ ቅሪቶች የሚመጣ ነው—ስለዚህ ቤተክርስቲያን ስለ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት ልዩ እንክብካቤ እና ትጋት ታሳያለች። ይህ ትኩረት እና መታሰቢያ ለጸሎት ተስማሚ በሆነ በተቀደሰ ስፍራ የምንጠብቀው ለሟቹ አመድ የተቀደሰ አክብሮት እንዲኖረን ይመራናል…”

የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ለብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ጥያቄ ምልሽ ሲሠጥ እንዲህ በማለት ይመልሳል፣ “ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ሰዎች ሲሞቱ አስክሬናቸው ተቃጥሎ የሚቀረው አመድ ለመሰብሰብ እና ለማቆየት የተወሰነ እና ቋሚ የተቀደሰ ቦታ ሊመደብ ይችላል፣ ይህም የእያንዳንዱን ሰው ማንነት ላለማጣት እና የስማቸው ትዝታ ለማቆየት ጭምር ነው" ቤተክርስቲያኗ ስለዚህ የእያንዳንዱን ሟች ሰው ትውስታ ለመጠበቅ አመዱን ወደ አንድ የጋራ ቦታ የማስገባት እድልን አምናለች።

የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ለሁለተኛው ጥያቄ ሲመልስ፣ “የቤተ ክህነት ኃላፊዎች አሁን ያለውን የሲቪል የፍትሐ ብሔር ደንቦች በማክበር፣ የቤተሰቡን የዘመዶቻቸውን አመድ አነስተኛ ክፍል በአንድ ቦታ ላይ በተገቢው መንገድ እንዲያስቀምጡ ያቀረቡትን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊገመግም ይችላል። ለሟች ሰው ታሪክ ጠቃሚ ነው፣ ማንኛውም አይነት ፓንቴይስቲክ (ፓንቴይዝም እውነታ፣ አጽናፈ ሰማይ እና ተፈጥሮ ከመለኮትነት እና ከበላይ አካል ወይም አካል ጋር ተመሳሳይ ናቸው የሚለው የፍልስፍና ሃይማኖታዊ እምነት ነው)፣ ተፈጥሯዊ ወይም ኒሂሊስቲክ (ኒሂሊዝም በፍልስፍና ውስጥ ያለ አመለካከት ሲሆን በአጠቃላይ ተቀባይነት ያላቸውን ወይም የሰው ልጅ ሕልውና መሠረታዊ ገጽታዎችን እንደ እውቀት፣ ሥነ ምግባር ... ወዘተ የማይቀበል አስተምህሮ ነው) አለመግባባት የሟቹ አመድ በተቀደሰ ስፍራ ውስጥ እንዲቀመጥ እስካልተደረገ ድረስ አስቸጋሪ ይሆናል ማለት ነው ።

የቫቲካን መገናኛ ብዙኃን ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ምላሽ ሲሰጥ ጣልቃገብነት እና ግምገማ ቀኖናዊ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ጭምር እንደሆነ ቤተሰቡ ሁሉንም ጉዳዮች ግምት ውስጥ በማስገባት ምን ምርጫዎች ማድረግ እንዳለበት እንዲገነዘብ የሚረዳ መሆኑን አስረድተዋል።

አንዳንድ የሲቪል የፍትሐ ብሔር ሕጎች የሟቾችን አመድ መከፋፈል እንደሚከለክሉ የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ያብራራ ሲሆን ሁለተኛው ጥያቄ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ጳጳሳት ካደረጉት ውይይት የተነሳ ብፁዕ ካርዲናል ዙፒ ድምፅ ሰጥተዋል። የእምነት አስተምህሮ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት ምላሽ ከሲቪል እይታ ይልቅ ከሥነ-መለኮት አንጻር ያለውን ዕድል ግምት ውስጥ አስገብቷል፣ በኋላም በመልሱ ላይ ተብራርቷል።

13 December 2023, 15:32